Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ቅንአት

    ለጌታ አንድ ነገር በማድረግ የሚገለጽ ጽኑ ክርስቲያናዊ ቅንአት ሲኖር... በክርስቶስ የሚያምነው ነፍስ ስለ እርሱ ለመመስከር ከሚሰናከል ይልቅ የኒያግራ ፏፏቴ ቁልቁል ከመፍሰስ ቢገታ ይቀለዋል፡፡ Testimonies, vol. 2, p. 233.ChSAmh 316.6

    ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ የሚቀበል ማንኛውም ሰው ስኬታማ የhርስቲያን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ብቃት ማጎልበቻዎች እግዚአብሔርን የማገልገል ከፍተኛ ጉጉት ያድርበታል፡፡ ሰማይ ለእርሱ ያደረገለትን ነገር ሲያስብ ልቡ ወሰን በሌለው ፍቅርና ሩኅሩኅ የምስጋና ስሜት ይነካል፡፡ ችሎታውን ለአገልግሎት በማዋል ለእርሱ ያለውን ምስጋና ለማቅረብ ብርቱ ፍላጎት ያድርበታል፡፡ በዋጋ ለገዛው ክርስቶስ ያለውን ፍቅር ለማሳየት ስለሚናፍቅ አስቸጋሪውን፣ ውጣ ውረድ የበዛውንና መሥዋዕትነት የሚያስከፍለውን ሥራ የሥራት ምኞት ያድርበታል፡፡ The Ministry of Healing, p. 502.ChSAmh 317.1

    እንደ ማርታ ያሉት ትጉና ቀናኢ ሠራተኞች የሚሰማሩበት ሰፊ የአገልግሎት መስክ አለ፡፡ ነገር ግን መጀመሪያ እንደ ማርያም በየሱስ እግሮች ሥር መቀመጥ አለብን፡፡ ትጋታቸው፣ ቅልጥፍናቸውና ብርታታቸው በክርስቶስ ጸጋ ከተቀደሰ—ህይወታቸው ለመልካም ሥራ የማይበገር ኃይል ይሆናል፡፡The Desire of Ages, p. 525. በማይታክት ጽናትና በማይዋልል ቅንአት የጌታን ሥራ ወደፊት ይዘን እንገሰግስ ዘንድ እነሆ በስሙ ወደ አገልግሎቱ አምጥቶናል፡፡Testimonies, vol. 9, p. 25.ChSAmh 317.2

    ድግግሞሽ የበዛበትን ኃይማኖታዊ ሥራችንን ማቆም ይኖርብናል፡፡ ለዓለም እየሠራን ቢሆንም ነገር ግን በቂ እንቅስቃሴና ቅንአት እያሳየን አይደለም፡፡ ከዚህ የላቀ ጽናት ቢኖረን ሰዎች የመልእክታችንን እውነት አምነው መቀበል በቻሉ ነበር፡፡ ለእግዚአብሔር የምንሰጠው አንድ ዓይነት ድምጸት ያለው ተደጋጋሚ አገልግሎት—ጥልቅ፣ ጽኑና የተቀደሰ ቅንአት ለማየት የሚሻውን አብዛኛውን ከፍ ያለ የህብረተሰብ ክፍል ያርቃል፡፡-Testimonies, vol. 6, p. 417.ChSAmh 317.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents