Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የቤተሰቡን አርማ መምረጥ

    የእግዚአብሔር የተመረጥን ሕዝቦች ነን በሚሉ ቤተሰቦች ላይ ሰይጣን አርማውን ሲተክል ጌታ አሳይቶኛል፡፡ ሆኖም በብርሐን እየተመላለሱ ያሉ በጠላት ጥቁር አርማና በደም በተነከረው የክርስቶስ መለያ (ትእዛዛት) መካከል ያለውን ልዩነት መለየት መቻል ይኖርባቸዋል፡፡-Testimonies, vol. 4, p. 200. ChSAmh 288.3

    ክርስቶስን እወደዋለሁ የሚሉ እርስዎ በሄዱበት ሁሉ የሱስ አብሮት እንዲሆን ይፍቀዱ፡፡ እንደ ጥንቶቹ የኃይማኖት አባቶች ድንኳንዎን በቀለሱበት ሁሉ ለጌታ መሠዊያ ያቁሙ፡፡ በዚህ ዙሪያ ጥልቅና ሰፊ ተሐድሶ ማካሄድ አስፈላጊ ነው፡፡--Testimonies, vol. 5, pp. 320, 321.ChSAmh 289.1

    ሰይጣን ሰዎችን ከእግዚአብሔር ለማራቅ ማንኛውንም ጥረት ያደርጋል፡፡ ኃይማኖትን ያስቀድም የነበረውን ሕይወት በንግድ ዓለም እንዲሰምጥ በማድረጉ ረገድ ስኬተኛ ነው፡፡ የሰዎች አእምሮ በንግድ ሥራ ሲወጠር በቂ ጊዜ ወስደው መጽሐፍ ቅዱሳቸውን አያነቡም፣ በምስጢር አይጸልዩም፣ በጠዋትና በምሽት የሚቃጠል የምስጋናና የውዳሴ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያው ላይ አያኖሩም:: Testimonies, vol. 5, p. 426.ChSAmh 289.2

    የቤተሰብ አምልኮ ጊዜ አስደሳችና የማይሰለች እንዲሆን ይደረግ፡፡-Testimonies, vol. 5, p. 335. ልጆች በማለዳ ተነስተው በቤተሰብ የአምልኮ ጊዜ እንዲገኙና ለጸሎት ሰዓት ልዩ አክብሮት እንዲኖራቸው ይማሩ፡፡-Testimonies, vol. 5, p. 424. ChSAmh 289.3

    ኃይማኖት ለልጆች መስህብነት እንዲኖረው ሆኖ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የቤተሰብ አምልኮ ጊዜ ከቀኑ ሰዓታት ሁሉ እጅግ አስደሳች ሆኖ ይቅረብ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጥሩ ሆኖ የተመረጠና ቀላል ይሁን፡፡ ልጆች መዝሙር በመዘመር ይካፈሉ፡፡ የሚቀርበው ጸሎት አጭርና ግልጽ ይሁን፡፡ Southern Watchman, June 13, 1905. ChSAmh 289.4

    በቤተሰብ የአምልኮ ክፍለ ጊዜ የእንግዶች መገኘት መልካም ነው፡፡ በመርኀ ግብሩ የሚቀርብ ጸሎት በእንግዶች ላይ መልካም ተጽእኖ ከማሳደር አልፎ ነፍስን ከጥፋት እስከ መታደግ ሊደርስ ይችላል፡፡ ጌታ “እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” በማለት ስለዚህ አገልግሎት ይናገራል፡፡-Testimonies, vol. 6, p. 347. ChSAmh 289.5

    ልጆች ለጸሎት ሰዓት ከበሬታና ቅድስና እንዲሰጡ ሊማሩ ይገባል፡፡ ለዕለቱ ሥራ ቤታችንን ለቅቀን ከመውጣታችን አስቀድሞ የቤተሰብ አባላት በአንድ እንዲሰባሰቡ በማድረግ አባት ወይም አባት ከሌለ እናት ቀኑን ሙሉ በቅድስና የሚጠብቃቸውን ጽኑ ጸሎት ልታደርግ ይገባል፡፡ የፈተናም ሆነ የአደጋ ስሜትሁሉንም በትሕትናና በቅን ልብ በመሠዊያው ላይ በእምነት በማኖር ለጌታ በጸሎት ያስረክቡ፡፡ ለእግዚአብሔር የተሰጡ ሕጻናትንአገልጋይ መላእክት ይጠብቋቸዋል፡፡ ጠዋትና ማታ በጽኑ ጸሎትና በትጉ እምነት ስለ ልጆቻቸው ጌታን መለመን የክርስቲያን ወላጆች ኃላፊነት ነው፡፡ ልጆች እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕይወት እንዴት መኖር እንዳለባቸው አስመልክቶ ወላጆች ልጆቻቸውን በከፍተኛ ትዕግሥት፣ ደግነትና ያለመታከት ሊያስተምሯቸው ይገባል፡፡ Testimonies, vol. 1, pp. 397-398. ChSAmh 290.1

    ‹‹የእግዚአብሔር ወዳጅ›› የነበረው አብርሃም ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠው ምሳሌ ትቶልናል፡፡ የአብርሃም ሕይወት በፀሎት የተሞላ ነበር፡፡ ድንኳኑን በሚተክልበት ቦታ ሁሉ በአቅራቢያው ለእግዚአብሔር መሠዊያ በማዘጋጀት አብረውት የሚሰፍሩ ሁሉ ማለዳና ምሽት ላይ ለፈጣሪ መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ያደርግ ነበር፡፡ ድንኳኑ ሲፈርስ መሠዊያው በነበረበት ቦታ ይቆያል፡፡ በቀጣዮቹ ዓመታት ከአብርሃም ትዕዛዝ የመጣላቸው የከነዓን ነዋሪዎች ነበሩ፡፡ ከእነርሱ መካከል ወደ መሠዊያው የመጣውን የሚያውቀው አብርሃም፤ ድንኳኑን ሲቀልስ፣ መሠዊያውን የሚያስተካክል ሲሆን በዚያም ሕያው እግዚአብሔርን ያመልካል፡፡-የኃይማኖት አባቶችና ነቢያት ገጽ 137 ChSAmh 290.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents