Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 1—ለአገልግሎት የቀረበልን አምላካዊ ጥሪ

    በሰብዓዊ ወኪሎች ላይ መተማመን

    እግዚአብሔር ሰዎችን ለማዳን የጋለ ቅንአት ያላቸውን ሰብዓዊ ፍጡራን በሰዎች መካከል ተወካዮቹ አድርጎ ሾመ እንጂ ኃጢአት የማያውቁትን መላእክት አልመረጠም፡፡ ክርስቶስ ወደ ሰብዓዊው ፍጡር ለመድረስ ሲል ሰብዓዊውን ተፈጥሮ ወሰደ፡፡ ደኀንነትን ለዓለም ለማምጣት መለኮት ሰብዓዊውን ተፈጥሮ መውሰድ ነበረበት፡፡ “የማይመረመረውን የክርስቶስ ባለጠግነት” ይፋ አድርጎ የመግለጥ ቅዱስ ኃላፊነት እነሆ ለወንዶችና ሴቶች ተሰጥቶአል፡፡— The Acts of the Apostles, p. 134.ChSAmh 7.1

    አብልጦ ልብን ወደ ሚነካው ትዕይንት ይመልከቱ፡፡ ራሱ በመረጣቸው አሥራ ሁለት አገልጋዮች የተከበበው የሰማይ ንጉሥ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ተለየው አገልግሎት ሊያሰማራቸው እንደሆነ እናስተውል፡፡ እነዚህን ደካማ ፍጡራን ወኪሎቹ አድርጎ በመጠቀም በቃሉና በመንፈሱ አማካይነት ወደ ሁሉም በመድረስ የደኅንነት ባለቤት የሚሆኑበትን ንድፍ አወጣ፡፡-The Acts of the Apostles, p. 18. ChSAmh 7.2

    እግዚአብሔር “ሰዎች ወደ ኢዮጴ ልከህ ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንን አስመጣው” ብሎ በመናገር ለወንጌል አገልግሎትና ለቤተክርስቲያን መደራጀት ያለውን የከበረ ትኩረት ገለጸ፡፡ ወደ ቆርኔሌዎስ የተላከው መልአክ የመስቀሉን ታሪክ የመንገ ተልዕኮ አልተሰጠውም፡፡ መመስከር የሰብዓዊው ፍጡር ርዕሰ ጉዳይ እንደመሆኑ ቆርኔሌዎስን ጨምሮ ደካማና ለፈተና ተጋላጭ ለሆነው ሰብዓዊ ፍጡር ስለ ተሰቀለውና ከሞት ስለተነሳው አዳኝ ሊነግረው የሚገባ ሰው ነበር፡፡The Acts of the Apostles, p. 134. ChSAmh 8.1

    ወደ ፊልጶስ የተላከው መልአክ ራሱ ለኢትዮጵያዊው ሊመሰክርለት ቢችልም ነገር ግን ይህ እግዚአብሔር የሚሠራበት መንገድ አይደለም፡፡ ሰዎችለሰዎች ይሠሩ ዘንድ አምላካዊው ዕቅድ ነው፡፡The Acts of the Apostles, p. 109.ChSAmh 8.2

    “ነገር ግን ይህ እጅግ ታላቅ ኃይል ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ አለመሆኑን ለማሳየት፣ ይv የከበረ ነገር በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን” በማለት ሐዋርያው ይናገራል፡፡ እግዚአብሔር እቅዱ አይደለም እንጂ ኃጢአት የማያውቃቸውን መላእክቱን ተጠቅሞ አምላካዊውን እውነት ማወጅ ይችል ነበር፡፡ ሆኖም በድካም የተከበበውን ሰብዓዊ ፍጡር አምላካዊውን ንድፍ የሚተገብር የእርሱ መሣሪያ አድርጎ በመምረጡ በዋጋ ሊተመን የማይችል የከበረ ነገር በሸክላ ዕቃ ውስጥ ተቀመጠ፡፡ በሰዎች አማካይነት ለዓለም የቀረበው አምላካዊ ጸጋ የእግዚአብሔር ክብር በጽልመት የተዋጠው ኃጢአት ላይ እንዲያንጸባርቅ አደረገ፡፡ ሰብዓዊው ፍጡር በሚያበረክተው በፍቅር የተሞላ አገልግሎት ኃጢአተኛውንና ደኅንነት ያሚያሻውን ወገንለአገልግሎት የቀረበልን አምላካዊ ጥሪ ወደ መስቀሉ እያመላከተ ምስጋና፣ ክብርና ውዳሴ ከሁሉ በላይ ለሆነው ለእርሱ ብቻ ያቀርባል፡፡--The Acts of the Apostles, p. 330. ChSAmh 8.3

    አዳኙ የሰው ልጆች አማላጅ ለመሆን ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ እርሱ የጀመረውን ሥራ ተከታዮቹ ይገፉበት ዘንድ ዓላማው ነበር፡፡ ሰብዓዊ ወኪሎቹ በጨለማ ለተቀጡት ወገኖች የወንጌልን ብርሃን ለመፈንጠቅ የተለየ ፍላጎት ማሳየት የለባቸውምን? የእውነትን ብርሐን ተሸhመው እስከ ምድር ዳርቻ ለመጓዝ ጥቂት ፈቃደኞች ቢኖሩም ነገር ግን እውነትን የሚያውቅ ማንኛውም ነፍስ ሌሎችን ወደ እውነት የማምጣት መሻት እንዲኖረው እግዚአብሔር ይጠይቃል፡፡ ለመጥፋት በቋፍ ያሉ ነፍሳትን ለማዳን የሚያስችል የተለየ መሥዋዕትነት ለመክፈል ፈቃደኞች ሳንሆን ወደ እግዚአብሔር ከተማ ለመግባት የሚገባን ሆነን መቆጠር የምንችለው እንዴት ነው?--Testimonies, vol. 9, p. 103.ChSAmh 9.1

    ጌታ እውነትን የማወቅ መሻት ያላቸውን ሰዎች እውነትን ወደ ሚያወቁ ወገኖች በማምጣት በጥበቡ ይሠራል፡፡ ብርሃን የተቀበሉ በጨለማ ላሉት እንዲያስተላልፉ የሰማይ እቅድ ነው፡፡ ከታላቁ የጥበብ ምንጭ ብቃት ያገኘው ሰብዓዊ ፍጡር አእምሮንና ልብን የመለወጥ ኃይል ያለው የወንጌልበሥራ ላይ ያለ ወኪልና መሣሪያ ሆኖ ተበጀ፡፡--The Acts of the Apostles, p. 134.ChSAmh 9.2

    እግዚአብሔር ያለ እኛ አዥነት ኃጢአተኞችን የማዳን ዕቅዱን ከግብ ለማድረስ አያቅተውም፤ ነገር ግን እኛ የክርስቶስ ዓይነት ባህሪይ ለማዳበር እንድንችል በሥራው ተካፋይ መሆን ይገባናል፡፡ በእርሱ መሥዋዕትነት ነፍሳት ድነው በማየት ከሚገኘው ደስታ ተካፋዮች ለመሆንበማዳን ሥራው ተካፋይ መሆን ይገባል፡፡--The Desire of Ages, p. 142. ChSAmh 9.3

    ክርስቶስ በሰዎች መካከል ተወካዩ እንዲሆኑ የመረጣቸው-እንዲድኑ ከሚጥሩላቸው ሰዎች ጋር አንድ ዓይነት ባሕሪ የተላበሱትን፣ ቅንአት ያደረባቸውን ሰብዓዊ ፍጡራን እንጂ ያልወደቁ መላእክትን አይደለም፡፡ ክርስቶስ ሰብዓዊ ፍጡራንን ለመገናኘት ሲል ለበሰ፡፡ ለዓለም ደኅንነት ለማምጣት መለኮትንና ስለሚጠይቅ፤ መለኮት _ ሰብዓዊውን ተፈጥሮ መውሰድ አስፈለገው፡፡ በእግዚአብሔርና በሰብዓዊው ፍጡር መካከል የግንኙነት መስመር ይፈጠር ዘንድ መለኮት ሰብዓዊውን ተፈጥሮ መውሰድ አስፈለገው፡፡-The Desire of Ages, p. 296.ChSAmh 9.4

    ከሰው ጋር የመገናኛ መስመሩ ሰው ስለሆነ መላእክት የእኛን ትብብር ለማግኘት በከፍተኛ ጉጉት ይጠብቁናል፡፡ እኛ በሙሉ እምነት ራሳችንን ለክርስቶስ ስናስረክብ መላእhት በእኛ አንደበት የእግዚአብሔርን ፍቅር ለመግለጽ አብልጠው ይደሰታሉ፡፡—The Desire of Ages, p. 297.ChSAmh 10.1

    እግዚአብሔር ሰብዓዊ ወኪሎቹን ሳይጠቀም ሥራውን ወደ ፍጻሜ አያመጣም፡፡ ስለዚህ ከእርሱ ጋር እጅና ጓንት ሆነን መሥራታችን የግድ ይሆናል፡፡--Review and Herald, March 1, 1887.ChSAmh 10.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents