Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለእያንዳንዱ ሰው በግል የቀረበ ጥሪ

    ለእያንዳንዱ ክርስቲያን በግል የቀረበ ጥሪና በዓይነቱ ልዩ የሆነ ሥራ ተመድቦአል፡፡— Southern Watchman, Aug. 2, 1904. ChSAmh 10.3

    እያንዳንዱ ሰው በአምላካዊው የወይን ተክል ዙሪያ እንዲሠራ እግዚአብሔር ይጠይቀዋል፡፡ ለእርስዎ የተመደበውን የሥራ ድርሻ ወስደው በታማኝነት ይሥሩ፡፡Bible Echo, June 10, 1901, ChSAmh 10.4

    ለዚህ ዘመን የተሰጠን መልእክት ለሁሉም አገር፣ ሕዝብ፣ ብሔርና ቋንቋ በፍጥነት ይታወጅ ዘንድ እያንዳንዳችን ሕያው መልእክተኞች ሆነን ተጠርተናል፡፡Testimonies, vol. 6, p. 438. ChSAmh 10.5

    እያንዳንዱ እውነተኛ ደቀ መዝሙር ለእግዚአብሔር መንግሥት ወንጌላዊ ለመሆን ተወልዶአል፡፡ ከሕይወት ውሃ የጠጣ ሁሉ ራሱ ምንጭ ይሆናል፡፡ ተቀባዩ ሰጪ ይሆናል፡፡ በነፍስ ውስጥ የክርስቶስ ጸጋ ሁሉን ለማርካት እንደሚፈልቅና ለመጥፋት የተቃረቡትን ሁሉ ከሕይወት ውሃ ለመጠጣት ጉጉት እንዲያድርባቸው እንደሚያደርግ የምድረ በዳ ምንጭ ነው፡፡--The Desire of Ages, p. 195.ChSAmh 10.6

    እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ካመናቸው፣ ለዚህ ዘመን የሚሆን የእውነት ዕውቀት ከሰጣቸው ወገኖች አገልግሎት ይጠባበቃል፡፡ ሁሉም ለአገልግሎት ወደ ባዕድ ምድር መሄድ ባይችሉም ነገር ግን ሁሉም በቤተሰቦቻቸውና በጎረቤቶቻቸው መሃል አገልግሎት መስጠት ይችላሉ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 30. ChSAmh 11.1

    ክርስቶስ ከሰማያዊው ዙፋን በጥቂት ርቀት ላይ ሆኖ ታላቁን ተልዕኮ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፡፡ መላውን የወንጌል ሠራተኞች ጨምሮ በስሙ የሚያምኑትን ሁሉ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ” አላቸው፡፡ የእግዚአብሔር ኃይል አብሮአቸው ለመጓዝ እየተጠባበቃቸው ነበር፡፡Southern Watchman, Sept. 20, 1904.ChSAmh 11.2

    ነፍሳትን የመመለስ ሥራ የክርስቶስ ነኝ የሚል የማንኛውም ሰው የዕድሜ ልክ አገልግሎት ሊሆን ይገባል፡፡ እኛ ለተሰጠን የእግዚአብሔር ጸጋ፣ በላያችን ላንጸባረቀው የብርሐን ጸዳልና ለተገለጠልን የእውነት ውበትና ኃይል ለዚv ዓለም ባለ ዕዳዎች ነን፡፡--Testimonies, vol.4, p. 53.ChSAmh 11.3

    በቅንጅት መሠራት ያለባቸውን ሥራዎች በግለሰብ የመተካት አዝማሚያዎች በየስፍራው ይታያሉ፡፡ ሰብዓዊው ጥበብ ታላላቅ ቤተ ክርስቲያኖችንና ተቋማትን የማዋቀርና የማነጽ ሥራዎችን ወደ አንድ ወገን የማጠቃለል ዝንባሌ አለው፡፡ በርካቶች በበጎ ፈቃደኝነትና በርኅራኄ አገልግሎት በግል ተካፋይ መሆን ሲገባቸው ሥራውን ለተቋማትና ለድርጅቶች መተዋቸው ልባቸው እየቀዘቀዘ እንዲሄድ መንስኤ ይሆናል፡፡ ተቀብለው የማይሰጡና አርአያ መሆን የማይችሉ ይሆናሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ብሎም ለሰው ሊኖራቸው ይገባ የነበረ ፍቅር በድን ይሆናል፡፡ ክርስቶስ በውክልና ሳይሆን እያንዳንዱ በግል የሚሠራውን _ ሥራ ለተከታዮቹ ሰጥቶአል፡፡ ወንጌልን ለጠፉት መመስከር፣ የታመመውንና ድኻውን ማገልግል--ለኮሚቴዎች ወይም ለበጎ አድራጎት ተቋማት የተተወ ተግባር አይደለም፡፡ ኃላፊነትን በግል መወጣት፣ የግል ጥረት ማድረግና መሥዋዕትነት መክፈልወንጌል የሚጠይቃቸው ተግዳሮቶች ናቸው፡፡-The Ministry of Healing, p. 147. ChSAmh 11.4

    መለኮታዊውን የብርሃን ጸዳል የተቀበለ እያንዳንዱ ሰው የሕይወትን ብርሃን ለማያውቁ ብሩሁን ጎዳና የማብራት ኃላፊነት አለበት፡፡The Desire of Ages, p. 152. ChSAmh 12.1

    ለእያንዳንዱ ሰው የሥራ ድርሻ ስለተሰጠው አንዱ ሌላውን ተክቶ ሥራት አይችልም፡፡ ተልዕኮን በኃላፊነት መወጣት ለጠፋው ደስታ ሲያመጣቸል ማለት ደግሞ ክርስቶስ የሞተለትን በሐዘን ውስጥ እንደሚጥልእያንዳንዱ ሰው ችላ ሊለው ወይም ተወት ሊያደርገው የማይችል የከበረ ዋጋ ያለው ተልዕኮ ተሰጥቶታል፡፡-- Review and Herald, Dec. 12, 1893. ChSAmh 12.2

    ሁላችንም ከእግዚአብሔር ጋር አብረን ልንሠራ ይገባል፡፡ እጆቹን አጣጥፎ ከአገልጋዮች እንደ አንዱ የተቆጠረ ማንም የለም፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሕይወትና ብልጽግና በአባላት እንቅስቃሴ መወሰን እንደሚችል እያንዳንዱ ሰው በግል ሊሰማው ይገባል፡፡- Review and Herald, Feb. 15, 1887. ChSAmh 12.3

    በክርስቶስ ደኅንነት ያገኘ እያንዳንዱ ነፍስ የጠፉትን ለማዳን በስሙ እንዲሠራ ተጠርቶአል፡፡ ይህ ሥራ በእስራኤል ቸል ተብሎ ኖሮአል፡፡ ዛሬስ የክርስቶስ ተከታዮች ነን በሚሉ ተመሳሳይ ዕጣ አልገጠመው ይሆን?-- Christ’s Object Lessons, p. 191. ChSAmh 12.4

    ለእያንዳንዱ ሰው የተመደበ ሥራ _ አለ፡፡ _ እውነትን የሚያምን እያንዳንዱ ነፍስ በተመደበበት ስፍራ ቆሞ “እነሆኝ፤ እኔን ላከኝ” ይበል፡፡ ኢሳ. 6፡8-Testimonies, vol. 6, p. 49.ChSAmh 12.5

    ጌታችን የሱስ ክርስቶስን መሻት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ዳግም ምጽአቱን ማፋጠን ለእያንዳንዱ ክርስቲያን የተሰጠ ልዩ መብትና ጥቅም ነው፡፡Christ’s Object Lessons, p. 69. ChSAmh 13.1

    የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሁሉ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከክርስቶስ የምኅረት ዕቅድ ጋር አንድ በመሆን ዓለምን ለማዳን ከወረደው ከእርሱ ጋር የጠፉትን የሚፈልግና የሚያድን ሰንሰለት አድርጎ ራሱን ሊመለከት ይገባል፡፡The Ministry of Healing, p. 105.ChSAmh 13.2

    ሁሉም በየፊናው የሚሠራው አለው፡፡ ለክርስቶስ የሚሠራው ሥራ እንደሌለው አድርጎ ማንም አይሰማው፡፡ አዳኙ ራሱን ከእያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር ጋር አንድ አድርጎ ይመለከታል፡፡--The Ministry of Healing p 104. ChSAmh 13.3

    ከጌታ ጋር ሕብረት ፈጥረው የኪዳኑ አገልግሎት አካል የሆኑ--ነፍሳት የሚድኑበት ታላቅ ሥራ ተካፋይ ለመሆን የሚያስችላቸውን ውል ከእርሱ ጋር ፈጽመዋል፡፡-- Testimonies, vol. 7, p. 19. ChSAmh 13.4

    መከሩ እጅግ ብዙና ሰፊ እንደመሆኑ እያንዳንዱ የተቀደሰ ልብ የመለኮት መሣሪያ ሆኖ ለአገልግሎት ይወጣል፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 47. ChSAmh 13.5

    ሰዎች የአምላካዊውን ጸጋ ዓላማዎችና ምኅረት ከዳር ለማድረስ በእርሱ የተመደቡ፣ በእጁ ያሉ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር እንዲሠራ የተሰጠውን ድርሻ ለማከናወን የሚያስችለው፤ ለሚገኝበት ጊዜ አስፈላጊና የሚስማማ--በቂ መጠን ያለው ብርሃን ተሰጥቶታል፡፡-- The Great Controversy, p. 343. ChSAmh 13.6

    እያንዳንዱ ሰው እንደ ችሎታው ለእርሱ ይሠራ ዘንድ የአገልግሎት መንፈስ መላውን ቤተ ክርስቲያን ርስት አድርጎ እንዲወስድ እግዚአብሔር ለረጅም ጊዜ ሲጠባበቅ ኖሮአል፡፡The Acts of the Apostles, ገጽ 111. ChSAmh 13.7

    የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲያውጁ መጀመሪያ አስራ ሁለቱን በመቀጠል ሰባዎቹን ሲልክ እርሱ ያሳወቃቸውን ለሌሎች ማካፈል ተግባራቸው እንዲሆን እያስተማራቸው ነበር፡፡ በሥራዎቹ ሁሉ እያንዳንዳቸው በግለሰብ ደረጃ መመስከር እንዳለባቸው፣ ቁጥራቸው እየጨመረና እየተስፋፉ ሲሄድ በስተመጨረሻ እንዴት ዓለምን እንደሚያዳርሱ እያሰለጠናቸው ነበር፡፡The Acts of the Apostles, ገጽ 32.ChSAmh 13.8

    ይህ ተልዕኮ ወደ ስኬት እንዲገሰግስ የማድረጉ ኃላፊነት የወደቀው በተቀባው አገልጋይ ላይ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም ክርስቶስን የተቀበለ እያንዳንዱ ሰው ለባልንጀራው ደኅንነት እንዲሠራ ተጠርቶአል፡፡--The Acts of the Apostles, 18 110. ChSAmh 14.1

    እውነተኛው የቤተ hርስቲያን ጸባይ የሚለካው ከፍ ያለውን ሙያዊ ክህሎት ተጠቅማ በመሥራቷ ወይም በቤተ ክርስቲያን የባሕር መዝገብ ላይ ስማቸው በሰፈረ አባላቶቿ ሳይሆን ዓላማን ለማሳካት ተግተው ለጌታ በሚሠሩ ታማኞች ቁጥር ነው፡፡ ግላዊ ፍላጎትና ሁል ጊዜም በንቃት የተሞላ ጥረት--ስብከትና ኃይማኖታዊ አስተምህሮ ከሚያስገኘው የላቀ-በተጋድሎ ለተሞላው የክርስቶስ ሥራ ክንዋኔ ያስገኛል፡፡-Review and Herald, Sept. ገጽ 6, 1881 ChSAmh 14.2

    ቤተ ክርስቲያን ሲቋቋም መላው አባላት ምንጊዜም በወንጌል ተልዕኮ አገልግሎት ላይ በንቃት መሳተፍ ይኖርባቸዋል፡፡ እያንዳንዱን በአቅራቢያቸው የሚገኝ ቤተሰብ መጎብኘትና የሚገኝበትን መንፈሳዊ ሁናቴ ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡Testimonies, vol. 6, ገጽ 296. ChSAmh 14.3

    ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አባላት ወደ ባዕድ ምድር ተጉዘው እንዲያገለግሉ አልተጠሩም፤ ነገር ግን ብርሃንን ለምድር በመስጠቱ ታቅ ሥራ ሁሉም የየበኩላቸው ድርሻ አላቸው:: በተግዳሮቶች የተሞው የhርስቶስ ወንጌል ወደ ሌሎች የመሰራጨት ባሕሪ አለው፡ ራሳቸውን ስግብግብ በሆነው ሰብዓዊ ፍላጎት የከረቸሙ አንዳቸውም ቢሆኑ በእግዚአብሔር ቀን ይቅርታ ማግኘት አይችሉም፡፡ ለእያንዳንዱ አእምሮና እጅ የተዘጋጀ ሥራ አለ፡፡ ለተለያዩ አእምሮዎችና ችሎታዎች እንዲስማሙ ሆነው የተዘጋጁ በአያሌ አማራጮች የተሞሉ ሥራዎች አሉ፡፡ Historical Sketches, ገጽ 290-291. ChSAmh 14.4

    የተቀደሰ እውነት በአደራ ተሰጥቶዎታል፡በእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አባል ውስጥ የሚኖረው ክርስቶስ—ዘላለማዊ ህይወት የሚሰጥ ምንጭ ነው፡፡ ይህን የሕይወት ውሃ ለሌሎች ለማደል የተቻሎትን ሁሉ ጥረት የማያደርጉ ከሆነ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ጥፋተኛ ይቆጠራሉ፡፡-Historical Sketches, ገጽ 291. ChSAmh 15.1

    ነፍሳትን ለክርስቶስ በማሸነፉ ረገድ እንደ ክርስቲያንነታችን ከሚጠበቅብን ሥራ አንድ ሃያኛውን እንኳ አልሠራንም፡፡ ማስጠንቀቂያ ሊሰጠው የሚገባ ዓለም ያለ እንደመሆኑ እያንዳንዱ እውነተኛና ታማኝ ክርስቲያን ለሌሎች መሪ፣ መልካም _ ምሳሌ፣ _ መስቀሉን የሚሸከም፣ ለአገልግሎት ተነሳሽና ብርቱ፣ ለእውነት መርኅ ጽኑና ታማኝ እምነት ያለው፣ የእግዚአብሔርን ሥራ ወደፊት ለማራመድ ተገቢውን መሥዋዕትነት የሚከፍል አገልጋይ ይሆናል፡፡--Review and Herald, Aug. 23, 1881, ChSAmh 15.2

    የእውነትን ብርሃን የተቀበለ ማንኛውም ሰው መልካም አጋጣሚዎች እየሰፉና እየተበራከቱለት ሲሄዱ “የሰው ልጅ ሆይ፤ አንተን ለእስራኤል ቤት ጎበኛ አድርጌሃለሁ፤ ስለዚህ የምናገረውን ቃል ስማ ማስጠንቀቂያዬንም ስጣቸው” (ሕዝ. 33፡7) የሚል ቃል ከመጣለት የእስራኤል ነቢይ ጋር ተመሳሳይ ኃላፊነት ይጋራል፡፡--Testimonies, vol. 9, pp. 19, 20.ChSAmh 15.3

    የአምላካዊው ጸጋ ተካፋይ የሚሆን ማንኛውም ሰው ጌታ ወደ ሌሎች የሚደርስበትን ሥራ መድቦለታል፡፡ እያንዳንዳችን በግል በተመደብንበት ስፍራ ቆመን “እነሆኝ፤ እኔን ላከኝ” እንበል፡፡ የቃሉ መጋቢ፣ ወንጌላዊ ነርስ፣ ክርስቲያን ሐኪም፣ ነጋዴ፣ ገበሬ፣ ከፍተኛ ባለሙያ ወይም መካኒክ--እያንዳንዱ ሰው ኃላፊነት ወድቆበታል፡፡ ሰዎች የሚድኑበትን ወንጌል መግለጥ የእኛ ሥራና ኃላፊነት ነው፡፡ ማንኛውም የተሰማራንበት ሙያ ውሎ አድሮ ይህን እውነት ማስተላለፊያ መሣሪያ ሊሆን ይገባል፡፡--The Ministry of Healing p. 148. ChSAmh 15.4

    የቤቱ ጌታ አገልዮቹን ጠርቶ እያንዱ ሰው የሚሠራውን የእርሱን ሥራ ሰጥቶአል፡፡ መላው የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባላት የጌታቸውን መሣሪያዎች የመጠቀም ኃላፊነት ተሰጥቶአቸዋል፡፡ እጅግ ዝቅ ካለው አንስቶ የከበረ ኃላፊነት የተሰጠው እያንዳንዱ በግብረገብና ሥነ ምግባር የታነጸ የአምላካዊው ወኪል በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂ የሚያደርገው ማንኛውም ችሎታ ተሰጥቶታል፡፡--Bible Echo, June 10, 1901.ChSAmh 16.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents