Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ብርቱ ሥዕላዊ ማሳያዎች

    እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ደኅንነት ሲል ጥልቅ የሆነውን መለኮታዊ ፍቅር ለገሰ፡፡ ሆኖም ሰዎች ስለዚv ታላቅ ፍቅር የሚያሳዩት አመስጋኝነት ከአንገት በላይ በመሆኑ መላእክት ይገርማቸዋል፡፡ ሰዎች ለእግዚአብሔር ፍቅር ያላቸው አድናቆት ጥልቀት የሌለው መሆኑ መላእክትን ያስገርማቸዋል፡፡ ሰዎች ስለሌሎች ነፍስ ግዴለሽ መሆናቸው እግዚአብሔርን ያስቆጣል፡፡ ክርስቶስ ነፍሳትን ምን ያህል እንደሚወድ ይገባን ይሆን? አንድ ልጅ በረዶና ቁር በበዛበት ቦታ ቢጠፋና ሊያድኑት ሲችሉ ሰዎች እያዩ ይሙት ብለው ትተውው እንደሄዱ ወላጆቹ ቢያውቁ ምን ይሰማቸው ይሆን? በጣም አያዝኑምን? አይናደዱም? ለልጃቸው ባላቸው ፍቅርና ስለ እርሱ በተሰማቸው ዘን መጠን ነፍሰ ገዳዮቹን አያወግዙአቸውም? የእያንዳንዱ ሰው ሥቃይ የእግዚአብሔር ልጅ ሥቃይ ስለሆነ ለሚጠፉት ባለንጀሮቻቸው የዕርዳታ እጅ የማይዘረጉ ሁሉ የእግዚአብሔርን ጻድቅ ቁጣ ይቀሰቅሳሉ፡፡--The Desire of Ages, p. 825.ChSAmh 127.1

    በአንድ ክረምት ቀን በክምር በረዶ በተሸፈነ መንገድ ጉዞ በማድረጉ ብዙም ሳይታወቀው ሰውነቱ በቅዝቃዜ ደንዝዞ መላ አቅሙን ሊያሳጣው ስለነበረ ሰው ታሪክ አንብቤ ነበር፡፡ ይህ ሰው እጅግ ብርቱ በሆነው ቅዝቃዜ ሰውነቱ መታዘዝ ሊያቆም ተቃርቦ በሞት አፋፍ እያለ እንደርሱ በጉዞ ላይ የነበረ፣ _ በቅዝቃዜው ሕይወቱ አደጋ ላይ የወደቀ አንድ የሚያቃስት ወንድም ድምፅ ይሰማል፡፡ ትvትናው ይህን ሰው እንዲያድን ገፋፋው፡፡ በረዶውን ከዚህ ምስኪን ሰው አካል ላይ ካራገፈና እንዲያንሰራራ የሚያስችለውን ማንኛውንም አስፈላጊ ጥረት ካደረገ በኋላ በእግሮቹ እንዲቆም ብድግ አደረገው፡፡ ሆኖም መራመድ የማይችል በመሆኑ የድጋፍ ስሜት በተላበሱት ክንዶቹ ተሸክሞ ፈጽሞ ለብቻው አልፎት ሊሄድ እንደማይችል አስቦት በነበረው አቅጣጫ መሄድ ቻለ፡፡ መንገደኛውን ደኅንነቱ የተረጋገጠ ስፍራ ላይ እንዳሳረፈው ባልጀራውን በማዳኑ የእርሱም ሕይወት የመትረፉ እውነታ ብልጭ አለለት፡፡ ሌላውን ለማዳን ያደረበት ቅን ፍላጎት ወደ በረዶነት እየተቀየረ የነበረው የገዛ ደሙ በፍጥነት እንዲንሸራሸርና ጤናማ የሰውነት ሙቀት በመላ አካሉ ከጫፍ እስከ ጫፍ እንዲሰራጭ አደረገ፡፡ ታሪኩ ወጣት አማኞች በኃይማኖታዊ አስተምህሮና መርኅ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በክርስትና ተሞክሮአቸውም ተመሳሳይ ክስተቶችን ማጤን እንዲችሉ ያላሰለሰ ኃይል ሊሆናቸው ይገባል፡፡Testimonies, vol. 4, pp. 319, 320.ChSAmh 127.2

    የእውነትን ዕውቀት በማግኘት በመባረካችሁ ደስተኞች ብትሆኑም ነገር ግን ይህን ያገኛችሁትን ብርሃን ለራሳችሁ ብቻ ይዛችሁ አታስቀሩ፡፡ ለመሆኑ እውነትን ማን አካፈላችሁ? አምላካዊውን የዓለም ብርሃን ማን አሳያችሁ? እግዚአብሔር ብርሃኑን በማሰሮ _ ውስጥ እንድታኖሩት አልሰጣችሁም፡፡ የእንግሊዝ ባሕር ኃይል ባልደረባና አሳሽ የነበሩት ሰር ጆን ፍራንክሊንን ለመፈለግ በዘመቻ ስለወጣው ጓድ አንብቤ ነበር፡፡ ጀግኖች ሰዎች ቤታቸውን ትተው ወደ ሰሜን ባሕር አቅጣጫ በመጓዝ ሥቃይ፣ ረሐብ፣ ቁር እና ጉዳት ሳይበግራቸው ተንከራተቱ፡፡ ያን ሁሉ ማድረጉ ለምን አስፈለገ? ሞተው ከሆነእዚህን በማሰስ ላይ የነበሩትን ወገኖች አስከሬን በክብር ለማሳረፍ—በሕይወት ካሉም—በእርግጠኝነት ካንዣበበባቸው አስከፊ የሞት ጥላ ለመታደግ ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ ከተሰወሩት መካከል የአንድ ሰው ሕይወት እንኳ ማትረፍ ቢችሉ ድካማቸውን እንደ ከንቱ አይቆጥሩትም፡፡ ይህ ሁሉ መሥዋዕትነት የተከፈለው ለተሰወሩት ወገኖች ምቾትና ደስታ ሲባል ነበር፡፡ChSAmh 128.1

    ከላይ ስለቀረበው ታሪክ በማሰብ በዙሪያችን ለሚገኙ የከበሩ ነፍሳትደኅንነት ምን ያህል አነስተኛ ጥረት እያደረግን እንደሆነ ልብ እንበል፡፡ እየጠፋ የሚገኘውን ሟች ለማዳን የምንኖርበትን አካባቢ ለቅቀን ረጅምና አድካሚ ጉዞ እንድንጓዝአልተገደድንም፡፡ ይልቁንም በገዛ በራፋችን-በግራም ሆነ በቀኝ በኩል ሊድኑ የሚገባቸው እየጠፉ ያሉ ነፍሳት አሉ፡፡ ወንዶችና ሴቶች ያለ ተስፋ፣ ያለ ክርስቶስ እየሞቱ ቢሆንም ጉዳዩ እምብዛም የሚሳስበን አይመስልም፡፡ ከአንደበታችን ባይወጣም ድርጊታችን “የወንድሜ ጠባቂ ነኝን? ለማለት ምንም የቀረው አይመስልም፡፡ እነዚያ ሌሎችን በማዳን ተግባር ተጠምደው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች እንደ ጀግኖችና ሰማዕት ተቆጥረው ዓለማዊ ውዳሴ የሚያገኙ ከሆነ፤ ታዲያ የዘላለማዊ ሕይወት ተስፋ ከፊታችን የተደቀነው እኛ ስለ ሰው ልጆች ደኅንነት እግዚአብሔር የሚጠይቀንን አነስተኛውን መሥዋዕትነት የማንከፍል ከሆነ ምን ሊሰማን ይገባል?-Review and Herald, Aug. 14, 1888.ChSAmh 129.1

    በኒው ኢንግላንድ በሚገኝ አንድ ከተማ ውስጥ የውሃ ጉድጓድ እየተቆፈረ ነበር፡፡ ሥራው ለመጠናቀቅ ጥቂት ሲቀር አፈሩ ተደርምሶ በጉድዱ ውስጥ የነበረን አንድ ሰው ቀበረ፡፡ የአደጋ ጊዜ ጥሪ በፍጥነት ተሰማ፡፡ መካኒኩ፣ ነጋዴው፣ ገበሬው፣ የሕግ ባለሙያው ይህን ሰው ለማትረፍ ብርቱ ርብርብ አደረጉ፡፡ ረጅም ገመድ፣ መሰላል፣ አካፋ፣ ፈቃደኛ እጆች--vይወት ለማትረፍ በከፍተኛ ጉጉት ቀረቡ፡፡ ብዙም ሳይቆይ “ተርፎአል! በሕይወት አለ! የሚሉ የደስታ ሲቃዎች መደመጥ ጀመሩ፡፡ChSAmh 129.2

    ስዎች ላባቸው በግንባራቸው ጠብ እስከሚል፣ _ እጆቻቸው እስከሚንቀጠቀጡ ያለ ኃይላቸውን አሟጠው ሠሩ፡፡ ረጅም ቁመት ያለውን ቧንቧ ቁልቁል በስተው በማውረድ በጉድጓድ ውስጥ ያለው ሰው በሕይወት ካለ መልስ እንዲሰጣቸው ጠየቁ፡፡ “በሕይወት አለሁ፤ ግን ፍጠኑ፡፡ ያለሁበት ስፍራ በጣም ያስፈራል” የሚል ምላሽ ሰጣቸው፡፡ በከፍተኛ ደስታ ተሞልተውና የታደሰውን ኃይላቸውን አስተባብረው በስተመጨረሻ ከወደቀበት አዘቅት ደርሰው ሊያድኑት ቻሉ፡፡ በወቅቱ በጎዳናው ላይያስተጋባው የደስታ ስሜት ሰማይን ጥሶ የሚገባ ይመስል ነበር፡፡ChSAmh 129.3

    አንድን ሰው ለማዳን ሲባል የተደረገ ይህ ሁሉ ቅንአት፣ ፍላጎትና ትጋት--አልበዛም? በፍጹም አልበዛም! ነገር ግን በዜአዊውና በዘላለማዊው ሞት መካከል ያለውን እጦት እንዴት እናስተያየዋለን? የምድራዊው ሕይወት አደጋ ላይ መውደቅ የሰብዓዊውን ልብ ይህን ያህል በጥልቀት ካነሳሳ ከክርስቶስ መነጠል የሚያስከትለውን አደጋ እንገነዘባለን ለሚሉ ነፍስን ማጣት ከዚህ በላቀ ሊያሳስብና ሊያስጨንቅ አይገባ ይሆን? የእግዚአብሔር አገልጋዮች ለነፍሳት ደኅንነት በሚሠሩት ሥራ በውሃ ጉጓዱ ውስጥ የተቀበረውን አንድ ሰው ለማትረፍ የተደረገው ዓይነት ታላቅ ቅንአተ ማሳየት የለባቸውምን? --Gospel Workers, pp. 31, 32.ChSAmh 130.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents