Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እንድንነቃ የቀረበ ጥሪ

    ሥራው በፍጥነት ወደ ፍጻሜ እየተቃረበ፣ ክፋት በሁሉም አቅጣጫው እየተንሰራፋ ይገኛል፡፡ ሥራ ለመሥራት ያለን ጊዜ እጅግ አጭር ነው፡፡ ከመንፈሳዊው እንቅልፍ ነቅተን ያለንን ሁሉ ለጌታ ቀድሰን እናስረክብ፡፡ መንፈሱ ለእውነተኛ ወንጌላውያን የአገልግሎት ኃይል እየሆነ አብሮአቸው ይኖራል፡፡Southern Watchman, April 9, 1903.ChSAmh 110.2

    ወንድሞችና እህቶች--ንቁ! ማንቀላፋታችሁ ያብቃ፡፡ የሱስ እንዲህ ይለናል “ቀኑን ሙሉ ያለ ሥራ በከንቱ ለምን ቆምክ? በል ዛሬውኑ ወደ ወይኑ ስፍራ ሄደህ ሥራ፡፡” መንፈስ ቅዱስን የተቀበለ ሁሉ በሕይወቱ እንዲታይ ይፈቅዳል፡፡ ሙሉ ኃይሉን ሥራ ላይ በማዋል ንቁ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በእርግጥ በእምነት ክርስቶስን የተቀበሉ ሁሉ የሥራው ተካፋይ ይሆናሉ፡፡ የነፍሳት ሸክም ይሰማቸዋል፡፡ የእውነት ዕውቀት ያለው እያንዳንዱ ሰው ካንቀላፋበት ነቅቶ ሰማያዊውን ብርሃን ለሌሎች እንዲያበራ እግዚአብሔር ጥሪ ያቀርብለታል፡፡-Review and Herald, Dec. 6, 1893.ChSAmh 111.1

    ወንደሞች ንቁ! ለገዛ ነፍሳችሁ ብላችሁ ከእንቅልፋችሁ ተነሱ፡፡ ያለ ክርስቶስ ጸጋ አንዳች ማድረግ አትችሉም፡፡ መሥራት በምትችሉበት ወቅት ሥሩ፡፡--Southern Watchman, July 17, 1906.ChSAmh 111.2

    የወደቁት መላእክት ምድራዊ ምቾትና ደህንነት ከሚሰማቸው ጋር የሚሠሩትን ዓይኖቻችን ተከፍተው፣ ለይተው መመልከት ቢችሉ የደህንነት ስሜት ባልተሰማን ነበር፡፡ ክፉ መላእክት ሁሌም መንገዳችን ላይ ይጋረጣሉ፡፡--Testimonies, vol. 1, p. 302. ChSAmh 111.3

    ሰባኪዎችም ሆኑ ሕዝቡ ከእንቅልፉ እንዲነቃ እግዚአብሔር ጥሪውን ያቀርባል፡፡ መላው ሰማይ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ የምድር ታሪክ ትዕይንቶች በፍጥነት ወደ ፍጻሜ እያመሩ ነው፡፡ በመጨረሻዎቹ በአደጋ የተሞሉ ጊዜያቶች ላይ እንገኛለን፡፡ ከፊት ለፊታችን አስከፊ መቅሰፍቶች ቢኖሩም እኛ ግን አልነቃንም፡፡ የዚህ ከእንቅስቃሴ የራቀና ቅንነት የጎደለው ተግባር ውጤት አሰቃቂ ነው፡፡ እንደ ሞት ጨምድዶ የሚይዘው አፍዝ አደንግዝ ከሰይጣን ነው፡፡--Testimonies, vol. 1, pp. 260, 261.ChSAmh 111.4

    የእግዚአብሔርን ትሩፋን ሕዝቦች ለማነሳሳት ከቶ ምን ብል ይሻል ይሆን? አስፈሪ ትዕይንት ከፊታችን እንዳለ ተመልክቼ ነበር፡፡ ሰይጣንና መላእክቱ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ለመቋቋም ኃይላቸውን ሁሉ በአንድ እያሰባሰቡ ነው፡፡ ለጥቂት ጊዜያት እንዳንቀላፉ የሚቀጥሉ ከሆነ የመጥፋታቸው ነገር የተረጋገጠ እንደሚሆን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡-Testimonies, vol. 1, p. 263.ChSAmh 111.5

    የእያንዳንዱ ነፍስ ጉዳይ በቅርቡ ዘላለማዊ ውሳኔ በሚያገኝበት በእነዚህ ለሰው ልጆች በተሰጡ የምህረት ማብቂያ፣ የጨረሻ ጊዜያቶች የሰማይና የምድር ጌታ የሆነው አምላክ ቤተ ክርስቲያን ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንድትገባ ይጠባበቃታል፡፡ የከበረውን እውነት በማወቃቸው በክርስቶስ ነፃ የሆኑት-ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃን ከጠራቸው በምድር ገጽ ካሉ ሕዝቦች ሁሉ የላቁና ከምርጦቹ እንደ አንዱ ሆነው በጌታ ይታያሉ፡፡ ከሌሎች ጋር ግንኙነት መፍጠር በነጻ የተሰጡን በረከቶች ናቸው፡፡ መልካም የምስራች የሆነው የደኅንነት ቃል ወደ ሁሉም አገር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ሕዝብ መሰራጨት ይኖርበታል፡፡Prophets and Kings, pp. 716, 717.ChSAmh 112.1

    ከመሃላችን ከመቶ ሰዎች አንዱ እንኳ ከተለመደው ተግባር ውጪ ዓለማቀፋዊ ባህሪ ያለውን አገልግሎት እየሰጠ አይደለም፡፡ ክርስቶስ ለሞተላቸው ነፍሳት ጥቅም ለመሥራት በግማሽ እንኳ አልነቃንም፡፡Testimonies, vol.8, P 148. ChSAmh 112.2

    የክርስቶስ ተከታዮች ተግባራቸውን ተገንዝበው ከእቅልፋቸው ቢነቁ በባዕድ አገር ወንጌልን እየሰበከ የሚገኘው አንድ ሰው አንድ ሺ ይሆናሉ፡፡ በሥራው ላይ በግንባር መሳተፍ ያልቻሉ ሁሉ አገልግሎቱን በገንዘባቸው፣ የሌላውን ስሜት በመካፈልና በጸሎታቸው ሊደግፉ ይገባል፡፡ እንዲሁም ክርስቲያን በሆኑ አገሮች ለሚኖሩ ነፍሳት ከዚህ የላቀ ጽኑ አገልግሎት ይኖራል፡፡ Steps to Christ, P 81.ChSAmh 112.3

    ምንም እንኳ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃንና የከበሩ ዕድሎች ቢያገኙም ነገር ግን ተጽእኖአቸውን ወይም ገንዘባቸውን ለሌሎች ለመንገር ጥቅም ላይ አያውሉትም፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ሸክምእንዳይሆኑ የገዛ ነፍሶቻቸውን በአምላካዊው ፍቅር ውስጥ የማኖር ኃላፊነት እንኳ አይሰማቸውም፡፡ ስለ ክርስቶስ፣ ስለ እውነትም ሆነ ስለ ራሳቸው ደኅንነት ሲሉ ካንቀላፉበት ነቅተው ዘላለማዊ ውጤት ያለውን ሥራ በትጋት ይሥሩ— Review and Herald, March 1, 1887.ChSAmh 113.1

    የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን እንደ አንድ ብቁ የመከላከያ ሠራዊት ልትታይ ትችላለች፡፡ የእያንዳንዱ ወታደር ሕይወት በአድካሚ እንቅስቃሴ፣ በውጣ ውረድና በአደጋ የተሞላ ነው፡፡ በእያንዳንዱ አቅጣጫ ፈጽሞ የማያንቀላፋና ምድቡን የማይከዳ በጨለማው ልዑል ኃይል የሚመራ፣ በንቃት የሚጠባበቅ ጠላት ሁል ጊዜም አለ፡፡ ማንኛውም ክርስቲያን ከጥበቃ ውጪ በሚሆንበት ጊዜ ይህ ብርቱ ጠላት ያልታሰበ ከባድ ጥቃት ይሰነዝርበታል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባላት ሁል ጊዜ ንቁ ሆነው ካልተገኙ በአሳች መሣሪያዎቹ ሽንፈት ይደርስባቸዋል፡፡ ChSAmh 113.2

    የአንድ ሠራዊት አካል ከሆኑ በግዳጅ ላይ እንዲሰማሩ ትእዛዝ ከተሰጣቸው ወታደሮች መሃል ግማሽ ያህሉ ያለ ሥራ ቢቀመጡ ወይም ቢያንቀላፉ ውጤቱ ሽንፈት፣ ምርኮ ወይም ሞት ይሆናል፡፡ ከእነዚህ መካከል የተወሰኑት ከጠላት እጅ ቢያመልጡ ለሽልማት ብቁ ተደረገው ይታሰባሉ? በፍጹም! እንደውም የተለየ የሞት ፍርድ ይወሰንባቸዋል፡፡ በተመሳሳይ በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ግዴለሽነት ወይም ታማኝነትን ማጉደል ከዚያ የላቀ ውጤት እንዲከተል መንስኤ ይሆናል፡፡ የሚያንቀላፉ የክርስቲያን ወታደሮች ከመሆን ምን የከፋ ነገር ሊኖር ይችላል? በጨለማው ልዑል ቁጥጥር ስር የሚገኘውን ዓለም ለመታደግ ምን ዓይነት ግስጋሴ ሊደረግ ይገባል? በውጊያው ሰዓት አንዳችም ፍላጎት ሳያሳዩም ሆነ ኃላፊነት ሳይሰማቸው በግዴለሽነት ወደ ኋላ የሚቀሩ -ጊዜ ሳይወስዱ አካሄዳቸውን ያስተካክሉ ወይም ማዕረጋቸውን ይተዉ፡፡-Testimonies, vol. 5, p. 394.ChSAmh 113.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents