Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መልካም ማኅበራዊ ግንኙነት ይኑሮት

    ከሰዎች ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ ማድረግ የምትችሉበት ሁናቴ በተመቻቸ ቁጥር ያገኛችሁትን መልካም ዕድል ተጠቀሙበት ስል ለክርስቶስ በመሥራት ላይ ለሚገኙ ሁሉ ለመንገር እወዳለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳችሁን ብትከፍቱላቸው ልታካፍሏቸው የምትሏቸው ታላላቅ እውነቶች አሉ፡፡ ስኬትዎ አብልጦ የሚወሰነው በዕውቀትዎና በክንውንዎ ላይ ሳይሆን የዚያን ነፍስ ልብ ለማግኘት በሚያደርጉት አካሄድ ነው፡፡ በቤተሰብ መሃል፣ በእሳት ዳር እንዲሁም በቤት ውስጥ በሚካሄዱ አነስተኛ ስብሰባዎች ክርስቶስን በማቅረብ ነፍሳትን ለየሱስ በማሸነፉ ረገድ ከስብከት የላቀ ውጤት አለው፡፡Gospel Workers, p. 193.ChSAmh 169.1

    ክርስቶስ ራሱን hሰብዓዊ ፍላጎት ጋር ማያያዙ ቃሉን የሚሰብኩና የወንጌልን ጸጋ የተቀበሉ ሁሉ ሊከተሉት የሚገባ አርአያነት ነው፡፡ ማኅበራዊ ግንኙነትን መተው የለብንም፡፡ ራሳችንንም ከሌሎች ማግለል የለብንም፡፡ ወደ ተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ለመድረስ ወዳሉበት ቦታ ሄደን ልናገኛቸው ይገባል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ፈልገውን አይመጡም፡፡ የሰዎች ልብ ከቤተ ክርስቲያን መድረክ ብቻ በሚሰበክ መለኮታዊ እውነት አይነካም፡፡ ዝቅተኛ ደረጃ ያለው ቢመስልም የዚያኑ ያህል ተስፋ ሊጣልበት የሚችል ሌላ የአሠራር ዘዴ ያለ ሲሆን ይኸውም በደሳሳ ጎጆዎች፣ በትላልቅ ቪላዎች፣ በሆስፒታሎችና በማኅበራዊ ስብሰባዎች መሃል ነው፡፡The Desire of Ages, p. 152.ChSAmh 169.2

    ውሱን ያልነበረው የክርስቶስ ጥረት ጥብቅ ሕጋቸውን ችላ በማለት ለፈሪሳውያኖች ልዩ መሰናክል ሆነባቸው፡፡ የኃይማኖት ክልል በየዕለት ኑሮ እንዳይረክስ በሚል በረጅም ግንብ ታጥሮ ስላገኘው ይህን የተከለለ የግንብ አጥር አፈራረሰው፡፡ ከሰዎች ጋር ሲገናኝ የኃይማኖታቸው መመሪያ ምን እንደሆነ ወይም የየትኛው እምነት ተከታዮች እንደሆኑ አልጠየቀም፡፡ ዕርዳታ ላስፈለጋቸው ሁሉ ዕርዳታ ሰጭ ኃይሉን ተጠቀመበት፡፡ ሰማያዊ ባህሪውን ለማሳወቅ በአንዲት ባህታዊ ጎጆ ውስጥ ከመሸሸግ ይልቅ ስለ ሰብዓዊ ፍጡሮች በቅንነት አገለገለ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይማኖት መሰረተ ሐሳብ አካልን በማጎሳቆል ላይ ያልተመሰረተ መሆኑን አስተማረ፡፡ የጠራና ያልተበከለ ኃይማኖት ለተወሰነና ለተለየ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል እንዳልሆነ ትምህርት ሰጠ፡፡ ሁል ጊዜና በማንኛውም ቦታ ለሰዎች ያለውን ፍቅር ገለጸ፡፡ በዙሪያውም የደስተኝነት >ይማተኖት ብርሃን አበራ፡ -The Desire of Ages p. 86.ChSAmh 170.1

    በጠባብ አስተሳሰብና በተሳሳተ ፍረጃ ቢሞሉም የሱስ ግን የእነዚህን የተናቁ ሰዎች መስተንግዶ ተቀበለ፡፡ በቤታቸው ውስጥ ተኛ፣ በእነርሱ እጅ የተዘጋጀውን ምግብ አብሮ በላ፣ በመንገዶቻቸው ላይ አስተማረ፣ በከፍተኛ ርኅረኄና አክብሮት ተቀበላቸው፡፡--The Desire of Ages, p. 193.ChSAmh 170.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents