Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አብርሃም መልካም ምሳሌ

    ለአብርሃም የተሰጠው ፈተና ቀላል አልነበረም፤ እንዲያቀርብ የተጠየቀው መሥዋዕትም እንዲሁ የዋዛ አልነበረም፡፡ አብርሃም ከአገሩ፣ ከቤተሰቡና ከቤቱ ጋር የሚያያይዘው ጠንካራ ትስስር ቢኖረውም ነገር ግን ጥሪውን ለመቀበል አላመነታም፡፡ የተስፋይቱ ምድር ለም የሆነ አፈርና ተስማሚ የአየር ንብረት እንዳላት፣ አገሪቱ ተስማሚ አካባቢዎችን የያዘችና ሐብትን ለማከማቸት ዕድል የምትፈጥር ስለመሆኗ ጥያቄ አላቀረበም፡፡ እግዚአብሔር ከተናገረ አገልጋዩ መታዘዝ አለበት፡፡ ለእርሱ በምድር ላይ እጅግ የሚያስደስተው ቦታ እግዚአብሔር እንዲገኝ የሚጠይቀው ስፍራ ነው፡፡ ChSAmh 251.2

    አሁን ድረስ በርካቶች እንደ አብርሃም ዓይነት ፈተና ይሰጣቸዋል፡፡ እነዚህ ወገኖች የእግዚአብሔርን ድምፅ በቀጥታ ከሰማይ ባይሰሙም ነገር ግን በቃሉ አስተምህሮና በቸርነቱ መስመሮች ጣልቃ እየገባ ይጠራቸዋል፡፡ ሐብትና ክብር የሚያስገኝላቸውን ሥራቸውን እንዲተዉ፣ ተስማሚና አትራፊ ድርጅቶቻቸውን እንዲለቁና ከቤተሰባቸው እንዲነጠሉ፣ ወደ ራስን መካድ፣ መከራና መሥዋዕትነት የመክፈል መስመር እንዲገቡ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ ChSAmh 252.1

    እግዚአብሔር እነርሱ እንዲሠሩ ያዘጋጀው ሥራ አለ፤ ነገር ግን ምቾት ያለው ሕይወት፣ የጓደኞችና የቤተሰብ ተጽእኖ ሥራው እንዲሳካ የሚያስፈልጉ ወሳኝ ግብአቶች እንዳይጐለብቱ ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር ሲጠራቸው ከሰብዓዊው ፍጡር ተጽእኖና እገዛ ውጪ ሆነው የእርሱ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው እንዲሰማቸውና በእርሱ ላይ ብቻ እንዲተማመኑ በማድረግ ራሱን ሊገልጥላቸው ይችላል፡፡ የኑሮ እቅዶችን እንዲሁም የተለመዱ ቤተሰባዊና ማኅበራዊ ግንኙነቶችን በእግዚአብሔር ጥሪ ምክንያት ለመተው የተዘጋጀ ማን ነው? አዳዲስ ተግባራትን ተቀብሎ ከዚህ በፊት ወዳልተሞhሩ መስኮች የሚገባ፣ የእግዚአብሔርን ሥራ ጽኑና ፈቃደኛ በሆነ ልብ እየሠራ ትርፍና ኪሳራውን ከክርስቶስ አንጻር የሚመዝን ማን ነው? ይህንን የሚያደርግ የአብርሃም እምነት አለው፡፡ “ቀላልና ጊዜያዊ የሆነው መከራችን ወደር የማይገኝለት ዘላለማዊ ክብር ያስገኝልናል፡፡”የኃይማኖት አባቶችና ነቢያት ገጽ 135 ChSAmh 252.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents