Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የአıር ውስጥ አገልግሎትና የውጪ ተልዕኮ

    በውጪ አገ ሊተገበር የሚችለውን የወንጌል ሥራ የሚያበለጽገውነፃ አስተሳሰብ፣ ከንቱውን ፈቃድ መካድና ራስን ለሌሎች መሥዋዕት አድርጎ የመስጠት መንፈስ--ተገልጦ መታየት ሲችል የአገር ውስጥም የወንጌል ሥራ ይበልጥ ወደፊት መራመድ ይችላል፡፡ በሌሎች አገሮች በሚሠራው የወንጌል ሥራ በአገር ውስጥ የወንጌል ብልጽግና ላይ ብርቱ ተጽእኖ ማሳረፉን ተከትሎ የአገር ውስጥ አገልግሎት በውጪው ላይ መተማመን ያደርጋል፡፡ ነፍሳችንን የኃይል ምንጭ ወደ ሆነው አምላክ በማምጣት ከእርሱ ጋር ግንኙነት እንዲፈጥር ማድረግ የምንችለው ለአምላካዊው ሥራ የሚያስፈልገውን ሁሉ በመስጠት በአገልግሎት እንቅስቃሴ ስንጠመድ ነው፡፡--Testimonies, vol. 6, p. 27 ChSAmh 235.1

    ቅን ክርስቲያን የነበረው አሜሪካዊ ነጋዴ በቀን ውስጥ ለሃያ አራት ሰዓታት ለክርስቶስ ይሠራ እንደ ነበር ከሠራተኛው ጋር ባደረገው ንግግር ገልጾአል፡፡ “በሁሉም የንግድ ሥራዎቼ ጌታዬን ለመወከል ብርቱ ጥረት አደርጋለሁ፡፡ ሁናቴዎች በተመቻቹልኝ ቁጥር ሌሎችን ወደ እርሱ ለመማረክ እሞክራለሁ፡፡ ቀኑን ሙሉ ለክርስቶስ እየሠራሁ እውልና ምሽት ላይ እኔ ሳንቀላፋ—በቻይና ለእርሱ የሚሠራ ሠራተኛ አለኝ፡፡ በወጣትነቴ ወደ ባዕድ አገር ሄጄ የወንጌል አገልግሎተ የመስጠት ቁርጥ ሃሳብ አድሮብኝ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በወቅቱ አባታችን በሞት ስለተለየን ለቤተሰባችን የሚያስፈልገውን ለማሟላት በእርሱ እግር ተተክቼ የንግድ ሥራውን መሥራት ጀመርኩ፡፡ አሁን እኔ ራሴ ወደ ስፍራው ሄጄ አገልግሎት በመስጠት ፋንታ በዚያ የሚያıለግለውን ወንጌላዊ እደግፋለሁ፡፡ ከቻይና ክፍላተ ሀራት በአንዱ ምድብ የእኔ ሠራተኛ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ሰለዚህ መሽቶ ሳንቀላፋ በወኪሌ አማካይነት ለክርስቶስ አገልግሎት እየሰጠሁ እገኛለሁ፡፡” እንዲህ ያለውን አገልግሎት የሚሰጡ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች የሉምን? ቀደም ብለው እውነትን ላስተዋሉት የቤተ ክርስቲያን አባላት ያለማቋረጥ አገልጋዮች ሲመደቡላቸው ይስተዋላል፡፡ አባላት እነዚህን ሠራተኞች እንዲህ ይበሏቸው፡- “እናንተ በጨለማ ውስጥ እየጠፉ ላሉ ነፍሳት ለመሥራት ሂዱ፡፡ እኛ ራሳችን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ወደፊት መራመድ እንሠራለን፡፡ ከክርስቶስ ጋር ጸንተን በመቆም ስብሰባዎችን እየመራን መንፈሳዊውን ሕይወት ጠብቀን እንመላለሳለን፡፡ ከእኛ ጋር ያሉትን ነፍሳት በተመለከተ--ለእነርሱ እንሠራለን፡፡ የላቀ እጦት ላለባቸው ሰበካዎች ጸሎታችንንና ስጦታችንን እየላክን አገልግሎታቸውን እንደግፋለን፡፡”- Testimonies, vol. 6, pp. 29, 30.ChSAmh 235.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents