Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ቁልፍ የስኬት ተግባራት

    የወቅታዊውን እውነት ዕውቀት ለሌሎች የማሰራጨት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለንን ማኛውንም የሥራ ዕቅድ ከመከተላችንና ሥራውን ወደፊት ከሚያራምደው አስደናቂ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ጋር ግንኙነት ከመፍጠራችን አስቀድመን ስሙን ከፍ ለማድረግ ለምንመኘው፣ ለእርሱ ራሳችንን ቀድሰን እንስጥ፡፡ ልንጎበኝ ስለምናስባቸው ወገኖች ሳንታክት በትጋት እየጸለይን ሕያው በሆነ እምነት እያንዳዳቸውን አንድ በአንድ ወደ አምላካዊው መገኛ እናምጣቸው፡፡ የሰውን ሐሳብና ዓላማ የሚያውቀው ጌታ የደነደነውን ልብ በቀላሉ ማቅለጥ ይቻለዋል! በእቶን እሳት የሚመሰል መንፈሱ እንደ ባልጩት የጠጠረውን ልብ ማስገዛት ይሆንለታል! ነፍስን በፍቅርና በርኅራኄ መሙላት ይችላል! በግቢም በውጪም ለነፍሳት እንድንሠራ ብቁ የሚያደርገንን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ LamSA-MS., “Consecrated Efforts to Reach Unbelievers,” June 5, 1914 ChSAmh 233.2

    ሰዎችን በጥበብ እየቀረብን ከሥራው ጋር ብናስተዋውቃቸውና ለእኛ የተሰጠው ልዩ መብትና ጥቅም እነርሱም ተጋሪ የሚሆኑበትን ዕድል እያመቻቸን አገልግሎቱ እመርታ እንዲያገኝ ብንጥር፤ የጌታ ሥራ አሁን ካለው ይልቅ የላቀ ተቀባይነት ማግኘት በቻለ ነበር፡፡ እንደ እግዚአብሔር አገልጋይነታችን ጠንቃቃና አርቆ አሳቢ አካሄድ ብንከተል አምላካዊው እጅ በጥረታችን ሁሉ ባበለጸገን ነበር፡፡-Southern Watchman, March 15, 1904 ChSAmh 234.1

    በጌታ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሁሉ አገልግሎቱ ምን ያህል በእነርሱ ታማኝነትና ለመሥራት ባሰቡት ዕድቅ ላይ መተማመን እንደሚደርግ ቢገነዘቡ ኖሮ ጥረቶቻቸው እጅግ በላቀ ብልጽግና በተጎበኙ ነበር፡፡ ወላዋይነታችንና ኋላ ቀርነታችን በትhከል ልንደርስበት እንችል የነበረውን ነገር የራሳችን ከማድረግ ሲያግደን በተደጋጋሚ ተስተውሎአል፡፡ እኛ አቅማችን የፈቀደውን የድርሻችንን ለመሥራት ዝግጅት ሲኖረን እግዚአብሔር ለእኛ ይሠራል፡፡-Southern Watchman, March 15, 1904. ChSAmh 234.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents