Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የክርስቲያን አገልግሎት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 23—የተለያዩ የወንጌል አገልግሎት ዘርፎች

    ለዓይነ ሥውራን የሚደረግ ልዩ ጥንቃቄ፡

    መላእክት የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማገልገል ወደ ምድር ይላካሉ፡፡ በእያንዳንዱ እርምጃቸው ተገን በመሆን በሺv ከሚቆጠሩ ሥውር አደጋዎች ይታደጓቸዋል፡፡--Testimonies, vol. 3, p. 516. ChSAmh 296.1

    ዐይነ ሥውራንና የታመሙ በወገኖቻቸው መሃል ችላ ተብለው እየተመለከተ. የሕዝቡን ጸሎት በንቃት ማዳጥ አይሆንለትም፡፡ Testimonies, vol. 3, p. 518. ChSAmh 296.2

    አግዚአብሔር ለዐይነ ሥውራን፣ በሥቃይ ውስጥ ለሚገኙ፣ ባላቸው ለሞተባቸው ሴቶችና ወላጅ አልባ ለሆኑ ህጻናት ጠባቂ አድርጎ የሾመን እንደመሆኑ በቤተ ክርስቲያን--ለዐይነ ሥውሩ እንቅፋት የሚሆኑ ካሉ ወደ ፍርድ ሊመጡ ይገባል፡፡ የዐይነ ሥውራንን እግር የሚያደናቅፈው በእግዚአብሔር ቃል እንቅፋት በሚል የተጠቀሰው ቃል የእንጨት ሳይሆን የድንጋይ እንደመሆኑ ትርጉሙ ከዚህ የላቀ ነው፡፡ የዐይነ ሥውሩን ወንድም ብርታት፣ ማንሰራራትና ብልጽግና የሚጎዳ ወይም የሚገድብ ማንኛውም ዓይነት አካሄድ እንቅፋት ነው፡፡— Testimonies, vol. 3, p. 519. ChSAmh 296.3

    ዐይነ ሥውሩ የዐይን ብርሃኑን ማጣቱ በማንኛውም የህይወት ፈርጅ ለእጦት ይዳር?ዋል፡፡ በጨለማ የተዳፈነበትን ዓለም _ እየዳበሰ የሚውተረተረውን ዐይነ ሥውር እያየን ልባችን የማያዝንና የማይራራ ከሆነ በእርግጥ ይህ ከባድና አስቸጋሪ ነው፡: ልባችን በእግዚአብሔር ጸጋ ሊለሳለስ የግድ ነው፡፡Testimonies, vol. 3, p. 521. ChSAmh 296.4

    ወላጅ አልባዎቹን መንከባከብ፡-የቤተ ክርስቲያን አባላት ርኅራኄ፣ ፍቅርና ደግነት በማሳየት የበኩላቸውን ካልተወጡ በቀር በአንድ ሳይሆን ነገር ግን በብዙ መንገድ እየተሠቃዩ ያሉ፣ እንክብካቤ የሚሹ ወላጅ ዐልባ ህጻናት አሉ፡፡ ጌታ “ተንከራታቹን ደኻ ወደ ቤትህ አስገባው” ሲል ጥሪውን ያቀርብልናል፡፡ ክርስትና ለእነዚህ መኖሪያ ዐልባ ወገኖች እናትና አባት ሊሰጣቸው የግድ ይሆናል፡፡ ለመበለቲቱና ለወላጅ ዐልባዎቹ ህጻናት በጸሎትና በተግባር የሚገለጸው ርኅራኄያችን በእግዚአብሔር ፊት ይታወሳል—ውሎ አድሮም ከፍ ያለ ሽልማት ያሰጣል፡፡Review and Herald, June 27, 1893.ChSAmh 297.1

    ለደኻው እርዳታ ስናደርግ፣ በሥቃይ የሚገኙትንና የተጨቆኑትን ችግር ስንጋራና ወላጅ ዐልባውን ወዳጃችን ስናደርግ ራሳችንን ወደ የሱስ እናቀርባለን፤ ከእርሱ ጋር የቀረበ ትስስር እንፈጥራለን፡፡Testimonies, vol. 2, p. 25. ChSAmh 297.2

    ልዩ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው የምንችል ወላጅ ዐልባ ህጻናት ቢኖሩም ነገር ግን አገልግሎቱ የዚህ ሥራ ተሳታፊዎች የመንፈስ እርካታ ለማግኘት ከሚያደርጉት ጥንቃቄ የላቅ ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ ብዙዎች ራሳቸውን የሥራው አካል አያደርጉም፡፡ ሆኖም በዚህ ተግባር ላይ አንዳችም እንቅስቃሴ የማያደርጉ፣ ንፉጎችና ራስ ወዳድ ነፍሶች ሰማይ ራሳቸውን ስለ ክርስቶስ የካዱ ትጉ ሠራተኞች ስፍራ መሆኑን ንጉሡ የፍርድ ምርመራ በሚያደርግበት በዚያን ወቅት ያስተውላሉ፡፡ በፍቅር የተሞላውን ልዩ ጥንቃቄ ስለ ራሳቸው ሲሉ ፈጽሞ አድርገውት የማያውቁ ከምኅረት ውጪ ይሆናሉ፡፡ ንጉሡ በግራው በኩል በቆሙት ላይ አስከፊ ቅጣት የሚጥለው የከፋ ወንጀል ስለ ሠሩ አይደለም፡፡ የሚኮነኑት ስላደረጉት በጎ ሳይሆን ስላላደረጉት ነገር ነው፡፡ እንዲሠሩ በሰማይ የተመደባላቸውን ሥራ አልሠሩም፡፡ የራሳቸውን ድርሻ በደስታ መውሰድ ሲገባቸው ራሳቸውን በማስደሰት ብቻ ተወስነው ቀሩ፡፡--Review and Herald, Aug. 16, 1881.ChSAmh 297.3

    የhርስቶስ ተከታዮች ወላጅ ዐልባ ህጻናትን ለመንከባከብ ከእግዚአብሔር የተቀበሉት አደራ አለ፡፡ ሆኖም ብዙዎች እጅግ በተደጋጋሚ አደራውን በቸልተኝነት ሲመለከቱ ይታያሉ፡፡ ወላጅ የሌላቸው ልጆች የተቀዳደደ ልብስ ቢለብሱ፣ ቢታረዙ ወይም ምናቸውም የማይስብ ቢስል ነገር ግን የእግዚአብሔር ንብረቶች ናቸው፡፡ በዋጋ የተገዙ በመሆናቸው እንደ ማናችንም በፊቱ የከበሩ ናቸው፡፡ የእርሱ መጋቢ የሆኑ ክርስቲያኖች ለላቁ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባላት ኃላፊነት አለባቸው “አንተንም ስለ ደሙ በኃላፊነት እጠይቅሃለሁ”- Christ’s Object Lessons, pp. 386, 387. ChSAmh 298.1

    እያንዳንዱ የቤተ hርስቲያን አባል ለወላጅ ዐልባ ልጆች የበኩሉን እንዲያበረክት ጌታ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ ሆኖም ለእነርሱ የምትሰጡት አገልግሎት ስለምትወዷቸውና ከርስቶስ እነርሱን ለማዳን ስለሞተ እንጂ እንደ ግዴታ መቆጠር የለበትም፡፡ የእርስዎን ጥንቃቄ የሚሹትን እነዚህን ነፍሳት ክርስቶስ በደሙ ገዝቶአቸዋል፡፡ ስለዚv _ በኃጢአተኝነትዎና በአስቸጋሪነትዎ እንደወደዶት እርስዎም ሲወዷቸው ለማየት ይጠባበቃል፡፡ --Review and Herald, June 27, 1893.ChSAmh 298.2

    በሕዝብ መካከል የሚኖሩ ወላጅ የሌላቸው vጻናት፣ አባት የሌላቸው ልጆች፣ አካለ ስንኩላን፣ ዐይነ ሥውሮችና በደዌ የተመቱ ወገኖች ችላ ተብለው እግዚአብሔር የሕዝቡን ጸሎት በንቃት ሊያዳምጥ አይችልም፡፡ Testimonies, vol. 3, p. 518.ChSAmh 298.3

    ለወዳጅ ዐልባዎቹ ህጻናትና ወጣቶች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የእግዚአብሔር ልጆች የሚያደርጋቸው ትhክለኛው ጸባይ በውስጣቸው እንዲቀረጽና በጥሩ አቋም ላይ እንዲገኙ የሚረዳ፣ ሁሉም ሰው ሊሳተፍበት የሚችል ከፊታችን የተንጣለለ ሰፊ የሥራ መስክ አለ፡፡ እምብዛም ተስፋ የማይጣልባቸው የሚመስሉከፍተኛ ርኅራኄ ልናሳያቸው የሚገባ ልጆች አሉ፡፡ ለእነዚህ ህጻናት መሥራት ካልቻልን አብዛኞቹ ያለ አንዳች ዕውቀት ስለሚያድጉ ምግባረ ብልሹዎችና በወንጀል ነክ ተግባራት ሰጥመው የሚቀሩ ይሆናሉ፡፡ ሆኖም እነዚህን ህጻናት በመልካምና ምቹ ሁናቴ ውስጥ እንዲከበቡ በማድረግ ክርስቶስን በሚመስል ህይወትና ርኅራኄ በተሞላው ጥንቃቄ የእርሱ ተከታዮች አድርገን ልናድናቸው እንችላለን... ይህ ለሌሎች የምንሠራው ሥራ ብርቱ ጥረት ማድረግ፣ ራስን መካድና መሥዋዕትነት መክፈልን የሚጠይቀን ቢሆንምእግዚአብሔር አንድ ልጁን በመስጠት ካበረከተው ታላቅ ስጦታ አኳያ ይህ ልንከፍል የምንችለው አነስተኛ መሥዋዕትነት ምንድን ነው? እግዚአብሔር _ ከእርሱ ጋር ሠራተኞች የምንሆንበትን ልዩ መብትና ጥቅም ሰጥቶናል፡ ፡Review and Herald, June 27, 1893ChSAmh 298.4

    ጥቁሮቹ ዝርያዎች፡-በአሜሪካ ገና ያልተነኩ የወንጌል መስኮች አሉ፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጥቁር ሕዝቦች የእያንዳንዱን እውነተኛና በክርስቶስ ላይ ያለውን እምነት በተግባር የሚገልጽ አማኝ ልዩ ትኩረትና የድጋፍ ስሜት ይሻሉ፡፡ እነዚህ ሕዝቦች በአሜሪካ የሚኖሩ እንደመሆናቸው በባሕላዊ እምነቶች የተጠመዱ አይደሉም፡፡ እግዚአብሔር በመንፈሱ ምስክርነት አማካይነት ትኩረታችንን ለእነዚህ ችላ የተባሉት ሰብዓዊ ፍጡሮች እንድናደርግ በተደጋጋሚ ጥሪ እያቀረበልን ይገኛል፡፡ ከፊት ለፊታችን ወደ ተንጣለለው ያልተሠራበት እጅግ ሰፊ መስክ በማምራት እግዚአብሔር በእምነት የሰጠንን ብርሐን እንፈንጥቅ፡፡Testimonies, vol. 8, p. 205.ChSAmh 299.1

    በጥቁርና በነጭ ሕዝቦች መካከል የመለያያ ግድግዳዎች ተገንብተዋል፡፡ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን ቃል በመታዘዝ ለፈጣሪያቸው የላቀውን ፍቅር ሲቸሩና ባልንጀሮቻቸውን አድሎ በሌለው ፍቅር ሲወዱ እነዚህ ጠባብነትን መሰረት ያደረጉ ግድግዳዎች እንደ ኢያሪኮ ቅጥር ይፈራርሳሉ... ለዚህ ዘመን የተሰጠውን እውነት እናምናለን የሚል እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አባል ባርነት ባስከተለው መራራ ገፈት የማሰብ መብታቸውንና ለራሳቸው ጥቅም መድከማቸውን ለተገፈፉ፣ ችላ የተባሉ፣የተጨቆኑ ዝርያዎችን ይመልከት፡፡Review and Herald, Dec. 17, 1895.ChSAmh 299.2

    በደቡባዊው ክልል ለሚኖር የዚvች አገር ሕዝብ የተቀናጀ ሥራ እንሥራ፡፡ አንዳችም ተግባር ሳይከናወን ዐይናችን በሚመለከተው ነገር ብቻ አንርካ፡፡ የጥቁር ወንድሞቻችንን ጉዳትና ሥቃይ በማስታገስ ለጌታ አንድ ነገር እንኳ ከልባችን እናበርክት፡፡Review and Herald, Feb. 4, 1896.ChSAmh 300.1

    የጥቁሩ ዝርያ ስም ከነጩ አጠገብ በሕይወት መጽሐፍ ላይ ሰፍሮአል፡፡ ሁሉም በክርስቶስ አንድ ናቸው፡፡ ዜግነት፣ ሥልጣን ብሔር ወይም የቆዳ ቀለም አንዱን ሰብዓዊ ዝርያ ከሌላው ከፍ ወይም ዝቅ አያደርግም፡፡ የአንድ ሰው ማንነተ እንደ ግለሰቡ ጸባይ ይወሰናል፡፡ ቀይ የቆዳ ቀለም ያለው፣ ቻይናዊው ወይም አፍሪካዊው እግዚአብሔርን በመታዘዝና በእምነት ልቡን ለጌታ ቢሰጥ የቆዳውን ቀለም ሳይሆን ልቡን የሚመለከተው የሱስ ይወደዋል፡፡ የእርሱ የተወደደ ወንድም አድርጎ ይጠራዋል፡፡The Southern Work, p. 8, written March 20, 1891. ChSAmh 300.2

    የምድር ነገሥታትና ጌቶች ተስፋውን በወንጌል ላይ ካደረገው ትሑት አፍሪካዊ ጋር በእኩል ለመሥራት ደስተኞች የሚሆኑበት ቀን እየመጣ ነው፡፡The Southern Work, p. 8, written March 20, 1891.ChSAmh 300.3

    እግዚአብሔር እርሱን ለማገልገል ለተለወጠው አፍሪካዊ የሚያደርገው ጥንቃቄ ለአንድ እስራኤላዊ ያደርግ ከነበረው የሚያንስ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ለሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎችበተለይ የነጭ ዝርያ ለሌላቸው ወገኖች እየሰጡ ካለው አገልግሎት የላቀውን እንዲሰጡ ጌታ ይጠይቃቸዋል፡፡ መልእክቱን ለመስማት ከፍተኛ ዕድል ካገኙት ነጮች ይልቅ በአስከፊ ሁናቴ ለሚገኙ የሌሎች ቀለማት ሕዝቦች የማሰራጨት ብርቱ ግዴታ ስር አልወደቅንምን? ለመሆኑ እነዚህን ሕዝቦች በባርነት ጠፍንጎ የያዛቸው ማን ነው? መሀይማን አድርጎ ያስቀመጣቸው ማን ነው?... ይህ ሰብዓዊ ዝርያ ዝቅ ተደርጎ የሚታይ ከሆነ፣ አጸያፊና አጓጉል ልማድ አላቸው ካልን--እንዲህ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ማን ነው? ነጭ ቆዳ ያላቸው ሕዝቦች ስለዚህ ጉዳይ ከፍ ያለ ባለ ዕዳ አይደሉምን? ከዚህ ሁሉ መጠነ ሰፊ በደል በኋላ የእነዚህን ሕዝቦች አንገት ቀና ለማድረግ ጽኑና ቅን ጥረት መደረግ የለበትምን? እውነት ወደነዚህ ሕዝቦች ሊደርስ የግድ ነው፡፡ እነርሱም ሆኑ እኛ ነፍሳትን በማዳን ሥራ መሰማራት ይኖርብናል፡፡The Southern Work, pp. 11, 12, written March 20, 1891.ChSAmh 300.4

    የባህሪ ተሐድሶ፡-- ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች መሻትን በመግዛት ተጠቃሾች ነን ከሚሉ ሕዝቦች መሃል ከፊተኛው ረድፍ ሊቆሙ ይገባል፡፡-Gospel Workers, P 384. ChSAmh 301.1

    በሕዝብ ፊት ከምንናገረው በተጓዳኝ ራስን ገዝቶ የባሕሪ ለውጥ በማምጣት ዙሪያ የምንሠራው ሥራ አለ፡፡ በራሪ ጽሑፎችንና የኅትመት ውጤቶቻችንን ተጠቅመን መርኅዎቻችንን ማቅረብ ይኖርብናል፡፡ እያንዳንዱን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመን ሕዝባችን እውነትን ከማያውቁ ጋር የግንኙነት መስመር የሚፈጥርበትን ኃላፊነት እንዲወስድ ማነሳሳት ይኖርብናል፡፡ በወንጌል ሥራ አግኝተነው የነበረ ስኬት ራስን ከመካድና ራስን መሥዋዕት አድርጎ ከመስጠት ጥረት ጋር ሙሉ ለሙሉ የተመጣጠነ ነበር፡፡ እኛ እንደ ሕዝብ ራሳችንን በፊቱ ትሑት አድርገን በመመላለስ መሻትን የመግዛትን እውነት በግልጽ አውጀን ቢሆን—ልናገኝ የምንችለውን ክንውን ሊያውቅ የሚችለው ጌታ ብቻ ነው፡፡Gospel Workers, p. 385.ChSAmh 301.2

    ከእግዚአብሔር ሕዝቦች ወሳኝ ድጋፍ ማግኘትመሻትን የመግዛት ጥያቄ ምላሽ ነው፡፡ ራስን መግዛት አለመቻል ሰውን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር የሚደረግ ትግል አካል እንደመሆኑ ልልና ያልተገራው ማንነት እየጎለበተ እንዳይሄድ ለማድረግ ወይም ለመግታት ስለ ጤና ተሐድሶ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ የኅትመት ውጠቶች በእጅጉ ያስፈልጋሉ፡፡ በዚህ ነጥብ ዙሪያ ለሰዎች ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የኅትመት ውጤት የወንጌል ረዳት እጅ በመሆን ነፍሳት አምላካዊውን ቃል እንዲመረምሩና እውነትን በተሻለ እንዲያስተውሉ ይመራቸዋል፡፡ የክፉው ታላቅ መሣሪያ የሆነው-መሻትን ያለመግዛት የማስጠንቀቂያ ድምጽ ለሕዝብ ሊቀርብ ይገባል፡፡ ይህ ተግባራዊ መሆን ይችል ዘንድ እያንዳንዱ ሰንበት ጠባቂ ጤንነቱን እንዴት መጠበቅ እንዳለበት በኅትመት ውጤቶቻችን የቀረቡትን መመሪያዎች ማጥናትና _ መተግበር ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪ እነዚህን የኅትመት ውጤቶች ለጎረቤቶች በማሰራጨት ከዚህ በላይ ጥረት ማድረግ ይጠበቃል፡፡ Southern Watchman, Nov. 20, 1902. ChSAmh 301.3

    በአልኮል መጠጥ፣ በትንባሆ ወይም በሌሎች ሱስ አስያዥ ንጥረ ነገሮች የተጠመዱ ሙሉ ለሙሉ ከሱስ የሚወጡበትን መንገድ በመቀየስ ለዚህ ይወጣ የነበረ ገንዘብ ለመምተኛው ሕክምና፣ ለደኻው መደጎሚያ ወይም ህጻናትና ታዳጊ ወጣቶች ለዓለም ጠቃሚ የሚያደርጋቸውን ሥልጠና ለሚያገኙበት ተግባር ይዋል፡፡The Ministry of Healing p 211. ChSAmh 302.1

    የሥራ ክትትል አስፈላጊነት፡---እውነት በታላላቅ ጉባዔዎች መቅረብ ሲችል በታዳሚው አእምሮ ውስጥ የመጠየቅ መንፈስ መነቃቃት ያገኛል፡፡ ይህን ፍላጎት ተከትሎ ወደ እያንዳንዱ ነፍስ በግል መድረስ አስፈላጊ ነው፡፡ እውነትን የመመርመር ምኞት ያላቸው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል በትጋት እንዲያጠኑ መማር ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህ ነፍሳት በትክክለኛው መሰረት ላይ ይታነጹ ዘንድ የሆነ ሰው ሊረዳቸው የግድ ነው፡፡ በዚv ወሳኝ ወቅት እንዲህ ዓይነቱን አገልግሎት ለመስጠት ጥሩ ስተዋል ያላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ሠራተኞች በስፍራው ተገኝተው ተዝቆ የማያልቀውን የእግዚአብሔር ቃል መክፈታቸው እንዴት አስፈላz ይሆን!—Testimonies, vol. 9, p. 11.ChSAmh 302.2

    ወርቃማውን ጊዜ እያሳለፍን ነው፡፡ ነፍሳት እውነትን ለመቀበል ልባቸውን ከፍተውና አሰፍስፈው እያለ በግል መሠራት የነበረበት የክትትል ሥራ አልተሠራም፡፡ አእምሮ ለአምላካዊው እውነት በተነካበት ወቅት ወደዚያ ነፍስ መድረስ ካለመቻል ይልቅ መጀመሪያውኑ የማነቃቃት ሥራ ሳይሠራ ቢቀር ይሻል ነበር፡፡ ሰብዓዊው ልብ ለቀረበለት ጥሪ አለሳልሶት የነበረን ማንነት ከተቋቋመና ካገደ በኋላ ዳግመኛ አእምሮን በእውነት መንካት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡--Testimonies, vol, 2, p. 118. ChSAmh 303.1

    መጋቢነት፡ የመላው hርስቲያኖች ጥረት የሆነው አልፋ ኦሜጋ አምላካዊ ዓላማ ከግብ ይደርስ ዘንድ ባለን የገንዘብ መጠን ሥራውን ለመደገፍ መታıል ይኖርብናል፡፡Testimonies, vol. 9 p. 49.ChSAmh 303.2

    ገንዘብ ታላላቅ መልካም ነገሮችን ለማድረግ የሚያስችል ኃይል ስላለው ዋጋው ከፍተኛ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ልጆች እጅ ያለ ገንዘብ ለተራቡ ምግብ፣ ለተጠሙ ፈሳሽ—ለታረዙ ልብስ ነው፡፡ ገንዘብ ለተጨቆኑ መከታ፣ የታመመው ደግሞ እርዳታ የሚያገኝበት ምንጭ ነው፡፡ ሆኖም ገንዘብ ለሌሎች በረከት በመሆንና የክርስቶስን ዳግም ምጽአት በማፋጠን በሕይወታችን ለሚያስፈልጉን ነገሮች መዋል ካልቻለ ከባሕር አሸዋ የዘለለ ዋጋ አይኖረውም፡፡Christ’s Object Lessons, p. 351.ChSAmh 303.3

    ሥራው ግስጋሴ የሚያኝበትን ዕቅድ ራሱ የጠነሰሰው አምላክ ሕዝቡ የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋ ጥሪ ሲያደርግ “ጌታ ሆይ የሰጠኸኝ ምናን አሥር ምናን ትርፍ አስገኝቶአል” የሚል ምላሽ ያገኝ ዘንድ አትረፍርፈው የሚበለጽጉበትን መንገድ ቀይሶአል፡፡- Testimonies, vol. 9 p. 58.ChSAmh 303.4

    ነፍሳትን ለክርስቶስ ያሸነፍንበት መልካሙ ተጋድሎአችን ሰማያዊውን ቅጥር አልፎ ይገባል—7ንዘብ ከምድራዊው ሕይወት ባሻı አልፎ መሄድ አይችልም፡፡ ገንዘብ በሰማይ አንዳች አይፈይድልንም፡፡ ነገር ግን የጌታን ስጦታ በስስት ለራሳቸው ብቻ በከንቱ እያባከኑ በችግር ላሉ ወገኖቻቸው አንዳች በጎ ተግባር የማያከናውኑ፣ በምድር የእግዚአብሔርን ሥራ ወደ ፊት ለማራመድ የችሮታ እጆቻቸውን የማይዘረጉየፈጠራቸውን አምላክ ክብር የሚያዋርድ ተግባር ይፈጽማሉ፡፡ በሰማይ መጻሕፍት በስሞቻቸው ትይዩ እግዚአብሔርን የሚሰርቁ የሚል ጽሑፍ ይኖራል፡፡—Christ’s Object Lessons, p. 266.ChSAmh 303.5

    ገንዘብ ከነፍሳት ዘላለማዊ ሕይወት ጋር ሲነጻጸር አሁን በዚህ ምድር ያለው ዋጋው ምን ያህል ነው? እያንዳንዱ በኪሳችን የሚገኝ የገንዘብ መጠን የከበረ ዋጋ ያለው ሆኖ ከእግዚአብሔር የተሰጠን እንደመሆኑ የራሳችን ሳይሆን የጌታ ተደርጎ ሊታሰብ ይገባል፡፡ ገንዘብ ከንቱና አልባሌ ለሆነ ነገር ሊመነዘርና ሊጠፋ አይገባም፡፡ በዚህ ፋንታ ወንዶችንና ሴቶችን ከጥፋት ለሚታደገው አምላካዊ ሥራ ማስፋፊያነት በጥንቃቄ ሊውል ይገባል፡፡Life Sketches of Ellen G. White, p. 24. ChSAmh 304.1

    ከፍተኛ ጠቀሜታ ላለው ተጽእኖአችንና ድጋፋችን ብርቱ አጽንኦት ሰጥተን ለዓለማችን የወንጌልን መልእክት የማሰራጨት ሥራ መሥራት የለብንምን? እውነት ወደ ሌሎች አገሮች እንዲሰራጭና በአገር ውስጥ ያለውም የወንጌል እንቅስቃሴ እንዲደገፍ ራሳችንን ከእያንዳንዱ ገንዘብ አባካኝነት ክደን ስጦታችንን ወደ እግዚአብሔር ግምጃ ቤት ማስገባት የለብንምን? ሥራው የሰማይን ድጋፍና ተቀባይነት ማግኘት የለበትምን? በምድር ታሪክ መደምደሚያ ወቅት የሚሠራው ይህ ሥራ በታላላቅ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ወይም በምድራዊ ተጽእኖ ወደፊት አይራመድም፡፡ ይልቁንም ሥራው የሚደገፈው ራስን የመካድ ውጤት በሆኑ ስጦታዎችና መሥዋዕትነት ነው፡፡ እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ወራሾች የምንሆንበትን ልዩ መብትና ጥቅም በመስጠት በምንወርሳት አዲሲቱ ምድር ባለ ማዕረጎች ኢድርጎ ጠርቶናል፡፡Review and Herald, Dec, 2, 1890.ChSAmh 304.2

    መዝገብ የያዘው መልXክ እያንዳንዱን ለእግዚአብሔር ሥራ የሚሰጥ፣ ወደ አምላካዊው ግምጃ ቤት የሚገባ እንዲሁም በስተመጨረሻ ስጦታውየሚውልበትን አገልግሎት በታማኝነት እንደሚዘግብ ጌታ አሳይቶኛል፡፡ የእግዚአብሔር ዐይን ለመስጠት ፈቃደኛ ልብ ያለውን ወይም የሚያመነታውን--በየትኛውም ርቀት ላይ የሚገኘውን ለሥራው ቅንአት ያለውን ነፍስ ለይቶ ይመለከታል፡፡ ለመስጠት የሚኖር መነሳሳትም እንዲሁ በመዝገቡ ላይ ይሰፍራል፡፡ እርሱ በሚጠይቃቸው መሰረት የእግዚአብሔር የሆነውን ለእርሱ በመመለስ ራሳቸውን መሥዋዕት አድርገውና ማንነታቸውን ቀድሰው የሰጡ እንደ ሥራቸው መጠን የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ይቀበላሉ፡፡ምንምእንኳ ሰጪው ቀድሶ የሰጠው ገንዘብ ለእግዚአብሔር ክብርና ለነፍሳት መዳኛ ትክክለኛ ሥራ ላይ ሳይውልና የታማኙን ተጨባጭ ዓላማ ከግብ ሳያደርስ ቢቀር ለነፍሳት _ ካለው ታማኝነትና ለእግዚአብሔር ከሚሰጠው ክብር አኳያ ለከፈለው መሥዋዕትነት የተዘጋጀለተን ሽልማት አያጣም፡፡Testimonies, vol. 2, Pp. 518, 519. ChSAmh 305.1

    በችግር ውስጥ ያለውን ወንድም ለመርዳት ወይም የእግዚአብሔርን እውነት ለማሰራጨት የሚያስችል ማንኛውንም ዕድል መጠቀም ደኅንነቱ አስተማማኝ በሆነው cማያዊ ግምጃ ቤት ዕንቁ እንደ ማስቀመጥ ይቆጠራል፡፡ እግዚአብሔር ይፈትኖታል--እውነተኛውን ማንነትዎንም ያውቃል፡፡ እግዚአብሔር በለጋስ እጁ ያፈሰሰሎትን በረከት ተጠቅመው እርዳታ ለሚያሻቸው የድጋፍ እጅዎን እየዘረጉ ነው? ስለ ነፍሳት ዋጋ ግድ እያሎት ነው? እርሱ ያበረከተሎትን ስጦታ በምን ላይ እያዋሉት እንደሆነ እየተመለከተ ይገኛል፡፡ እያንዳንዱ እንዲህ ያለው መልካም ዕድል በሰማያዊው መዝገብ ተጨማሪ በረከት እንዲያከማቹ ይረዳዎታል፡፡ Testimonies, vol. 3, pp. 249, 250.ChSAmh 305.2

    የሰማያዊው ዘገባ አጻጻፍ፡- መላእክት የእያንዳንዱን ሰው ሥራ በታማኝነት ይመዘግባሉ፡:-- Testimonies, vol. 1, p. 198.ChSAmh 305.3

    እያንዳንዱ በፍቅር የተሞላ ድርጊት፣ ደግ ቃላት እንዲሁም በሥቃይና በጭቆና ለሚገኙ የሚጸለይ ጸሎት በዘላማዊው ዙፋን ፊት ይቀርባል፤ በማይጠፋው ሰማያዊው መዝገብ ላይም ይሰፍራል፡፡Testimonies, vol 5, p. 133. ChSAmh 306.1

    ጨለማውን የሚያስወግድና የክርስቶስን ዕውቀት በየስፍራው የሚያሰራጭ እያንዳንዱ ስኬታማ ዘገባ ወደ ሰማይ ይተማል፡፡ መልካሙ ተግባር በአብ ፊት ሲቀርብ መላው የሰማይ ሰራዊት በሐሴት ይሞላል፡፡-The Acts of the Apostles, p. 154.ChSAmh 306.2

    ረዳቶቻችን ይሆኑ ዘንድ አምላካዊ ተልዕኮ የተሰጣቸው መላእክት በሰማይና በምድር መሃል እየተመላለሱ፤ የመዘገቧቸውን የcዎች ልጆች ድርጊት ይዘው ወደ ላይ ይተምማሉ፡፡Southern Watchman, April 2, 1903.ChSAmh 306.3

    በእግዚአብሔር የምንዳኝበት ማንኛውም ድርጊት አንዳችም ስህተት ወይም ስርዝ ድልዝ በሌለው ሰማያዊ መዝገብ ተመዝግቦ እንደሚገኝ ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ለመስጠት ያስችለን ለነበረ ዕድል ያሳየነው እያንዳንዱ ቸልተኝነት ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ እንዲሁም እያንዳንዱ በእምነትና በፍቅር ያከናወንነው ተግባር ለዘላለም እንዲታወስ ሆኖ ሰፍሮአል፡፡Prophets and Kings, p. 639.ChSAmh 306.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents