Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በፐርሰንት ለመከፈል የቀረበ ሀሳብን የሚቃረን ምክር ተሰጠ

    ወንድም ቪ ያቀረበውን ሀሳብ በተመለከተ እኔ ጉዳዩን የምመለከተው ልክ አንተ እንደምትመለከተው ነው፡፡ (ሀሳቦቹ በሳምንት ሃያ አምስት ዶላር ደሞዝ መከፈል፣ ቀዶ ጥገና ሲደረግ ሰላሳ ፐርሰንት መቀበል፣ የአምስት አመት ኮንትራት፣ በአመት ለትምህርትና ራስን ለማሻሻል በራስ ወጪ የአንድ ወር ሥራ ላይ አለመገኘት የሚል ነበር)፡፡ በከፍተኛ ደሞዝ እቅድ መጀመር አንችልም፡፡ ይህ በባትል ክሪክ የነበረው ሕዝብ መጥፎ አጋጣሚ ሲሆን በዚህ ነጥብ ላይ ማለት የምፈልገው ነገር አለኝ፡፡ ከፊት ለፊታችን ትልቅ የሆነ ሚስዮናዊ የሥራ መስክ አለ፡፡ ለዓለማችን ራሱን ስጦታ አድርጎ ያቀረበውን የክርስቶስን መስፈርቶች መስማታችንን እርግጠኞች መሆን አለብን፡፡ ማድረግ የምንችለው ምንም ነገር ቢሆን ሳይደረግ መቅረት የለበትም፡፡ ውበትና ሥርዓት መኖር አለበት፣ በእያንዳንዱ መስመር ምሉእነትን ለማሳየት ማድረግ የሚቻል ነገር ሁሉ መደረግ አለበት፡፡ ነገር ግን በሳምንት ሃያ አምስት ዶላርን መክፈልን እና የቀዶ ጥገና ሥራ ሲሰራ ከፍተኛ የሆነ ፐርሰንት መስጠትን በተመለከተ መዝገባችን አደጋ ላይ ስለሆነ ይህ በፍጹም መሆን እንደማይችል በአውስትራሊያ ሳለሁ ብርሃን ተሰጥቶኝ ነበር፡፡ ብዙ የጤና ማሰልጠኛ ተቋማት በደቡባዊ ካሊፎርኒያ እንደሚቋቋሙ ጉዳዩ ቀርቦልኝ ነበር፤ ይህ የሆነበት ምክንያት ወደዚያ ቦታ ትልቅ የሆነ የሕዝብ መጉረፍ ስለሚኖር ነበር፡፡ ብዙዎች የአየር ንብረቱን ይሻሉ፡፡ Amh2SM 200.2

    እያንዳንዳችን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ ለመከተል ተዘጋጅተን በእግዚአብሔር ምክር መቆም አለብን፡፡ ከመጠን ያለፈ ደሞዝን ለመክፈል መስማማት አንችልም፡፡ እግዚአብሔር ከሥሩ ሆነው የሚሰሩ ሀኪሞች እንዲህ ከሚለው ግብዣ ጋር እንዲስማሙ ይሻል፣ «ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፣ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና፡- ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ፡፡ ቀንበሬ ልዝብ፣ ሸክሜም ቀሊል ነውና” (ማቴ. 11፡ 29፣ 30)፡፡ --Letter 309, 1905.Amh2SM 200.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents