Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ 11—በመጠበቂያ ላይ ለመሆን

    በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ ሁሉም ነገር ጸጥ ያለና የተረጋጋ ነው

    ጠላት ተአምራት በመስራት ኃይሉ ዓለምን በሙሉ ለማሳሳት እየተዘጋጀ ነው፡፡ የብርሃን መላእክትን ለመምሰል፣ ኢየሱስ ክርስቶስን መስሎ ለመቅረብ ይሞክራል፡፡ የወቅቱን እውነት የሚሰብክ ሁሉ ቃሉን መስበክ አለበት፡፡ በቃሉ ላይ የሚጣበቁ ሰዎች ትንቢት መናገርን ወይም ሕልሞችንና ራዕዮችን በተመለከተ ጥንቃቄ የጎደላቸውን ቃላት በመናገር ለሰይጣን በር አይከፍቱም፡፡ የክርስቶስን ዳግም ምጻት ከጠበቅንበት ከ1844 ዓ.ም ወዲህ ይብዛም ይነስም እንጂ ሀሰተኛ መገለጦች ሲመጡ ነበር፡፡ እነዚህን ነገሮች በጋርማየር ሁኔታ፣ በኬ አረፍተ ነገሮች እና በስታንቶን እንቅስቃሴ አይተናል (ቴስቲሞኒስ ቱ ሚኒስተርስ በሚለው መጽሐፍ ገጽ ከ32-62ን ይመልከቱ)፡፡ ወደፊትም በብዛት ስለምናገኛቸው እንደ ታማኝ ዘብ በመጠበቂያ ላይ መሆን አለብን፡፡ ስላዩአቸው ራዕዮችና እነዚህን ራዕዮች ለሌሎች መናገር ግዴታቸው እንደሆነ ከሚሰማቸው ከብዙዎች ሰዎች ደብዳቤዎች እየመጡ ናቸው፡፡ አገልጋዮቹ ጥንቁቆች እንዲሆኑ ጌታ ይርዳቸው፡፡ {2SM 96.1}Amh2SM 96.1

    ጌታ ትክክለኛ የሆነ የብርሃን ማስተላለፊያ ሲኖረው በተቃራኒው ሁል ጊዜ ትክክል የሚመስሉ የውሸት የብርሃን መተላለፊያዎች አሉ፡፡ ሰይጣን ክፍት ወደሆነለት ወደ ማንኛውም በር በእርግጥ ይገባል፡፡ ነፍሳትን ወደ ስህተት ለመምራት የእውነት መልእክቶችን ከተዘጋጁ ከራሱ የእውነት ሀሳቦች ጋር ቀላቅሎ ይሰጣል፡፡ ይህን የሚያደርገው አእምሮን ወደ ሰብአዊ ፍጡሮችና እነርሱ ወደተናገሯቸው ነገሮች ለመመለስ እና «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” የሚለውን አጥብቀው እንዳይይዙ ለመከልከል ነው፡፡ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ሁሉም ነገር ጸጥ ያለ ነው፤ እሱን ለሚታመኑት ሁሉም ነገር የተረጋጋና ማስመሰል የሌለበት ነው፡፡ ትሁት፣ እውነተኛና ከልባቸው መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምኑ፣ ቃሉን የሚሰሙና የሚያደርጉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ትክክለኛ የሆነ፣ ልባዊና ማስተዋል ያለበት እግዚአብሔርን መጠበቅ ይኖራል፡፡ መስራትና መጸለይ፣ መንቃትና መጠበቅ አቋማችን ነው፡፡ --Letter 102, 1894. {2SM 96.2}Amh2SM 96.2