የቀድሞ ወግ አጥባቂነት ድግግሞሽ
[ሚያዝያ 17 ቀን 1901 ዓ. ም ሚስስ ኢ. ጂ. ኋይት በጄኔራል ኮንፈረንስ በአገልጋዮች ፊት ያነበበችው መግለጫ] {2SM 31.2}Amh2SM 31.2
ወደ ኋላ ዘግይቶ የመጣውን በኢንዲያና የነበሩ ወንድሞች ልምምድና በቤተ ክርስቲያናት ውስጥ የሰጡትን ትምህርት በተመለከተ መመሪያ ተሰጥቶኝ ነበር፡፡ በዚህ ልምምድና ትምህርት አማካይነት ነፍሳትን ከመንገድ ሊያስታቸው ጠላት ሲሰራ ነበር፡፡ {2SM 31.3}Amh2SM 31.3
«ቅዱስ ሥጋ» ስለሚባለው የተሰጠው ትምህርት ስህተት ነው፡፡ አሁን ሁሉም ቅዱስ ልብ ማግኘት ይችላሉ፣ ነገር ግን በዚህ ሕይወት ቅዱስ ሥጋ ይኖረናል ማለት ስህተት ነው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ «በእኔ ማለት በሥጋዬ በጎ ነገር እንዳይኖር አውቃለሁ” (ሮሜ 7፡ 18) በማለት ይናገራል፡፡ ቅዱስ ሥጋ የሚባለውን በእምነት ለማግኘት እጅግ ጠንክረው ለሞከሩት ልታገኙ አትችሉም እላቸዋለሁ፡፡ አሁን ነፍሳችሁ ቅዱስ ሥጋ የለውም፡፡ በምድር ላይ ያለ ማንም ሰብዓዊ ፍጡር ቅዱስ ሥጋ የለውም፡፡ ይህ የማይቻል ነገር ነው፡፡ {2SM 32.1}Amh2SM 32.1
በሥጋ ፍጹም ስለመሆን በነጻነት የሚናገሩ ሰዎች ነገሮችን በእውነተኛ ብርሃን ማየት ቢችሉ ኖሮ በታላቅ ድንጋጤ ከድፍረት ሀሳቦቻቸው ያፈገፍጉ ነበር፡፡ ጌታ ቅዱስ ሥጋን በተመለከተ ያላቸውን የተሳሳተ ግምት በማሳየት ወንዶችና ሴቶች ወደ አካል፣ ወደ ነፍስ እና ወደ መንፈስ ብክለት የሚመራ ፈጠራን በቃሉ ውስጥ እንዳይጨምሩ ለመከልከል እየፈለገ ነው፡፡ ይህ የአስተምህሮ ዘርፍ ትንሽ ወደ ፊት ቢወሰድ ኖሮ ይህን ሀሳብ የሚቀበሉ ኃጢአት መሥራት አይችሉም፤ ቅዱስ ሥጋ ስላላቸው ተግባሮቻቸው ሁሉ ቅዱስ ናቸው ወደሚል አመለካከት ይመራል፡፡ ከዚህ የተነሳ እንዴት ያለ የፈተና በር ነው የሚከፈተው! {2SM 32.2}Amh2SM 32.2
ቅዱሳን መጻሕፍት የአካል፣ የነፍስና የመንፈስ ቅድስናን ከእግዚአብሔር መሻት እንዳለብን ያስተምሩናል፡፡ በዚህ ሥራ ከእግዚአብሔር ጋር አብረን ሠራተኞች መሆን አለብን፡፡ በሰው ውስጥ የእግዚአብሔርን የግብረገብ ምስል ለመመለስ፣ የአካል፣ የአእምሮና የግብረገብ ችሎታዎችን ለማሻሻል ብዙ ሊደረግ ይችላል፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግጋት በመታዘዝና በአካል ውስጥ ማንኛውንም የሚበክል ነገር ባለማምጣት በአካል ሥርዓት ውስጥ ታላቅ ለውጥ ሊደረግ ይችላል፡፡ የሥጋ ፍጽምና እንዳለን መናገር ባንችልም ክርስቲያናዊ የነፍስ ፍጽምና ሊኖረን ይችላል፡፡ በእኛ በኩል በሚደረገው መስዋዕትነት አማካይነት ኃጢአት በፍጹም ይቅር ሊባል ይችላል፡፡ የምንደገፈው ሰው ሊያደርግ በሚችለው ነገር ላይ ሳይሆን እግዚአብሔር በክርስቶስ አማካይነት ለሰው ሊያደርግ በሚችለው ነገር ላይ ነው፡፡ ራሳችንን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር አሳልፈን ስንሰጥ እና በሙሉ ልባችን ስናምን የክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻል፡፡ ሕሊና ከኩነኔ ነጻ መሆን ይችላል፡፡ በደሙ በማመን፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ሁሉም ፍጹማን መሆን ይችላሉ፡፡ እየተናገርን ያለነው ስለማይቻል ነገር ስላልሆነ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ቅድስናን ልናገኝ እንችላለን፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ልናገኝ እንችላለን፡፡ ክርስቶስና እግዚአብሔር ስለ እኛ ምን እንደሚያስቡ ሊያሳስበን አይገባም፣ ነገር ግን ሊያሳስበን የሚገባ ነገር ቢኖር የእኛ ምትክ ስለሆነው ክርስቶስ እግዚአብሔርን ምን ያስባል የሚለው ነው፡፡ በውድ ልጁ ሆናችሁ ተቀባይነት አግኝታችኋል፡፡ ለሚናዘዝና ለሚያምን ሰው፣ ነፍስ በእሱ አምሳያ ለመቀረጽና ለመሰራት ራሷን አሳልፋ ስትሰጥ፣ ክርስቶስ ያንን እንደሚቀበል ጌታ ያሳያል፡፡ {2SM 32.3}Amh2SM 32.3
ክርስቶስ በምድር ላይ በኖረበት ሕይወት ሰብዓዊ ግኝቶችን በሙሉ የሚጋርድና እንዲረሱ የሚያደርግ መገለጥ ማድረግ ይችል ነበር፡፡ ምስጢራዊ የሆኑ ነገሮችን በሮች መክፈት ይችል ነበር፣ የዘላለማዊ እውነታዎች ብዙ መገለጦች እርግጠኛ ውጤት ይሆኑ ነበር፡፡ እስከ ዘመን መጨረሻ ድረስ ያሉ ትውልዶችን አእምሮ መያዝ የሚችሉ ምስጢሮችን ለመክፈት እንደ ቁልፍ መሆን ይችሉ የነበሩ ቃላትን መናገር ይችል ነበር፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ ሰብዓዊ የማወቅ ፍላጎት መግቢያ ሊያገኝ ጥረት የሚያደርግባቸውን በርካታ በሮች አይከፍትም፡፡ ክርስቶስ ለሰዎች እጅግ ከፍተኛ ለሆኑ ፍላጎቶቻቸው ጎጂ ሊሆን የሚችል ግብዣን አያቀርብም፡፡ እርሱ የመጣው ለሰዎች ክፉንና ደጉን የሚያሳውቀውን ዛፍ ለመትከል ሳይሆን የህይወትን ዛፍ ለመትከል ነው፡፡ . . . {2SM 33.1}Amh2SM 33.1
በኢንዲያና ላሉትና እንግዳ የሆነ አስተምህሮን እየተቀበሉ ላሉት ሰዎች እጅግ ውድና አስፈላጊ ለሆነው የእግዚአብሔር ሥራ መጥፎ ቅርጽ እየሰጣችሁ ነው እንድል ታዝዣለሁ፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወሰን አትውጡ፡፡ የክርስቶስን ትምህርቶች ውሰዱና መልሳችሁ መላልሳችሁ ድገሙት፡፡ «ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽህት ናት፣ በኋላም ታራቂ፣ ገር፣ እሺ ባይ፣ ምህረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፣ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት፡፡ የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል» (ያዕ. 3፡ 17፣ 18) የሚለውን አስታውሱ፡፡” … {2SM 33.2}Amh2SM 33.2
ሰብዓዊ ፍጡራን ቅዱስ ሥጋን ሲቀበሉ በምድር ላይ አይቆዩም፣ ነገር ግን ወደ ሰማይ ይወሰዳሉ፡፡ በዚህ ሕይወት ኃጢአት ይቅር ቢባልም አሁን ውጤቶቹ ግን ሙሉ በሙሉ አይወገዱም፡፡ ክርስቶስ «ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጠዋል» (ፊል. 3፡21) የተባለው ተፈጻሚ የሚሆነው በዳግም ምጻቱ ነው፡፡ (ፊልጵ. 3:21). . . . {2SM 33.3}Amh2SM 33.3
ሥራችን ወደ ፊት እየቀጠለ ሳለ በተደጋጋሚ የወግ አጥባቂነት እንቅስቃሴዎች ተነስተዋል፣ ጉዳዩ በፊቴ ሲቀርብልኝ በኢንዲያና ላሉት ወንድሞች እየወሰድኩ ካለሁት መልእክት ጋር ተመሳሳይ የሆነ መልእክት መውሰድ ነበረብኝ፡፡ ይህ በኢንዲያና ያለው እንቅስቃሴ ባለፉት ዓመታት ከነበሩት እንቅስቃሴዎች ጋር ተመሳሳይ ባሕርይ ያለው መሆኑ ተነግሮኛል፡፡ በኃይማኖታዊ ስብሰባዎቻቸው ባለፉት ጊዜያቶች ከነበሩት እንቅስቃሴዎች ጋር በተገናኘ ሁኔታ ከተመለከትኳቸው እንቅስቃሴዎች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ነበሩ፡፡ {2SM 33.4}Amh2SM 33.4
1844 ዓ.ም ካለፈ በኋላ በነበረው ተስፋ የመቁረጥ ወቅት ጽንፈኝነት በተለያየ መልኩ ተነሳ፡፡ አንዳንዶች የሞቱ ቅዱሳን ትንሣኤ ከዚህ በፊት ሆኗል የሚል አቋም ያዙ፡፡ አሁን ለእናንተ መልእክት እንዳመጣሁላችሁ ለእነርሱም መልእክት እንዳደርስ ተልኬ ነበር፡፡ ፍጹማን እንደሆኑና አካል፣ ነፍስና መንፈስ ቅዱስ እንደሆኑ ተናገሩ፡፡ እናንተ የምታሳዩአቸውን ዓይነት ነገሮች በማሳየት አስገራሚ በሆነ ግምታቸው የራሳቸውን እና የሌሎችን አእምሮ ግራ አጋቡ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች የምንወዳቸው ወንድሞቻችን ስለነበሩ ልንረዳቸው እንናፍቅ ነበር፡፡ ወደ ስብሰባዎቻቸው ሄድኩ፡፡ ጩኸትና ምስቅልቅል ያለበት ብዙ ግርግር ነበር፡፡ የሚነፋውም ሆነ የሚመታው ምን እንደሆነ መንገር አይቻልም ነበር፡፡ አንዳንዶች ራዕይ የሚያዩ መሰሉና ወለሉ ላይ ወደቁ፡፡ ሌሎቹ ይዘሉ፣ ይዘፍኑና ይጮሁ ነበር፡፡ ሥጋቸው ስለነጻ ለመነጠቅ እንደተዘጋጁ ተናገሩ፡፡ ይህን ደግመው ደጋግመው ተናገሩ፡፡ በእነዚህ መገለጦች ላይ የእሱን ተግሳጽ በማስቀመጥ በጌታ ስም ምስክርነቴን ተሸከምኩ፡፡ {2SM 34.1}Amh2SM 34.1
በእነዚህ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሰማርተው የነበሩ አንዳንዶች ወደ ትክክለኛ አእምሮአቸው በመመለስ መታለላቸውን አዩ፡፡ አንዳንዶቹ እጅግ በጣም ጥሩና ታማኝ ሰዎች ነበሩ፣ ነገር ግን የተቀደሰ ሥጋ ኃጢአት መስራት አይችልም ብለው ስላሰቡ በሰይጣን ወጥመድ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ጠንካራ የሆኑ ሀሳቦቻቸውን እስከዚህ ድረስ ከመውሰዳቸው የተነሳ ውድ ለሆነው የእግዚአብሔር ሥራ ማፈሪያ ሆኑ፡፡ እነዚህ ከልባቸው ተናዘዙ፣ ከዚያ በኋላ አንዳንዶቹ እጅግ እምነት ከሚጣልባቸው ወንዶችና ሴቶች መካከል ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከዚያ በኋላ ሌሎች ሁል ጊዜ በሀዘን ውስጥ ሆነው የተመላለሱ ነበሩ፡፡ በማንኛውም ጊዜ ቢሆን ውድ ሥራውን በከፍተኛ ደረጃ ላዋረዱት ለጌታ ለመስራት የተገቡ እንደሆኑ እንዲሰማቸው ማድረግ አልቻልንም ነበር፡፡ {2SM 34.2}Amh2SM 34.2
አስቀድሜ እንደገለጽኩት ካሉት የወግ አጥባቂነት እንቅስቃሴዎች የተነሳ ለእነዚህ ነገሮች በምንም መንገድ ቢሆን ተጠያቂ መሆን የማይችሉ ሰዎች በአንዳንድ ሁኔታዎች የማገናዘብ ችሎታቸውን አጥተዋል፡፡ የግርግርና የሁከት ሁኔታዎችን ከራሳቸው ያለፈው ውድ ልምምድ ጋር ማጣጣም አልቻሉም ነበር፤ የስህተት መልእክትን እንዲቀበሉ ከልክ በላይ ጫና ተደርጎባቸው ነበር፤ ይህን ካላደረጉ በስተቀር እንደሚጠፉ ተደርጎ ቀርቦላቸው ነበር፤ ከዚህ የተነሳ አእምሮአቸው ሚዛናዊነትን ስላጣ አንዳንዶች የአእምሮ ሕመምተኞች ሆኑ፡፡ እነዚህ ነገሮች በእውነት ሥራ ላይ ነቀፌታ ያመጣሉ፣ የመጨረሻው የምህረት መልእክት ለዓለም እንዳይታወጅም እንቅፋት ይሆናሉ፡፡ {2SM 34.3}Amh2SM 34.3