Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ልዩ የሆነ ምልክታችን

    «የእግዚአብሔር ትዕዛዛትና የኢየሱስ ኃይማኖት” የሚል የሶስተኛው መልአክ አርማ በላዩ ተቀርፆበታል፡፡ ተቋሞቻችን የእምነታችንን ባሕርይ የሚገልጸውን ስም ስለወሰዱ በዚህ ስም በፍጹም ማፈር የለብንም፡፡ ይህ ስም ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑንና ይህን ስም በመውሰዳችን ከሰማይ የተሰጠንን ብርሃን መከተላችንን እንዳይ ተደርጌያለሁ፡፡ …ሰንበት የእግዚአብሔር ፈጣሪነት መታሰቢያ ስለሆነ በዓለም ፊት በግልጽ መቅረብ ያለበት ምልክት ነው፡፡Amh2SM 384.3

    የጣዖት ሰንበትን ከሚያመልኩ ጋር ምንም ዓይነት ድርድር መኖር የለበትም፡፡ እውነትን ከሚያውቁና የእውነት ብርሃን በላያቸው እየበራ ሳለ ጆሮአቸውን ከእውነት ወደ ተረት ከሚያዞሩት ጋር በመከራከር ጊዜያችንን ማጥፋት የለብንም፡፡ በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶችና የሳምንቱን የመጀመሪያ ቀን በሚጠብቁ ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ጉልህ እንዳይሆን ለማድረግ ሰዎች እያንዳንዱን ፖሊሲ ሥራ ላይ እንደሚያውሉ ተነግሮኛል፡፡ በዚህ ተጋድሎ ላይ መላው ዓለም የሚሳተፍበት ሲሆን ጊዜውም አጭር ነው፡፡ ይህ መልካችንን የምንደብቅበት ጊዜ አይደለም፡፡Amh2SM 385.1

    ልዩ ሕዝብ የሚያደርገን አርማችን ወይም ምልክታችን ይህን ያህል ጉልህ ተደርጎ መያዝ የለበትም የሚል የሰባተኛ ቀን አድቬንቲሰት ስም የያዘ ቡድን በፊቴ ቀርቦልኝ ነበር፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚያቀርቡት ይህ ድርጊት ለተቋሞቻችን ስኬት ለማስገኘት የተሻለ ፖሊሲ አይደለም የሚል ነው፡፡ ይህ ልዩ አርማ በዓለም ውስጥ የምህረት በር እስከሚዘጋበት ጊዜ ድረስ ከፍ ተደርጎ መያዝ አለበት፡፡ ዮሐንስ የቅሬታውን ሕዝብ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፣ «የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁና የኢየሱስ ምስክር ያላቸው ቅዱሳን ትዕግሥት ከዚህ ነው» (ራዕይ 14፡12)፡፡ ይህ ሕግና ወንጌል ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ ለመተላለፍ፣ የእግዚአብሔርን መታሰቢያ ለመቅደድ እና የኃጢአት ሰውን ፊርማ የያዘውን ሰንበት ከፍ ከፍ ለማድረግ በመስማማት ዓለምና አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት እየፈጠሩ ናቸው፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር የአምላክህ ሰንበት በታዛዦችና በአመጸኞች መካከል ያለውን ልዩነት የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ አንዳንዶች አርማውን ከቦታው ለማስወገድና ያዘለውን ቁም ነገር ለመደበቅ እጃቸውን ሲዘረጉ አየሁ፡፡Amh2SM 385.2

    ሰዎች የሀሰት ሰንበትን ሲቀበሉና ከፍ ከፍ ሲያደርጉ፣ ነፍሳትንም ለእግዚአብሔር ከመታዘዝና ከመገዛት ሲመልሱ በክርስቶስ ዘመን የነበሩ ሰዎች ከደረሱበት ነጥብ ላይ ይደርሳሉ፡፡ …ማንም ቢሆን አርማውን ለመደበቅና ያለውን ታማኝነት ለመቀነስ ይመርጣልን? እግዚአብሔር ያከበረው፣ የባረከውና ያበለጸገው ሕዝብ እንዲህ ያለ ምስክርነት መተላለፍ ባለበት በእንደዚህ ዓይነት ወሳኝ ወቅት ምስክርነቱን ለማስተላለፍ እምቢ ይላልን? ሰዎች በእግዚአብሔር ሕግ ላይ ያላቸውን ንቀት ሲያሳዩ የእግዚአብሔር ሕግጋት ከፍተኛ ክብር አይሰጣቸውምን? Manuscript 15, 1896.Amh2SM 385.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents