Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክርስቶስን ከፍ ከፍ ማድረግ

    ክርስቶስን በትክክል በእምነት የሚቀበል እያንዳንዱ ነፍስ በልብ ትህትና ይሄዳል፡፡ ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ አይኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ የዘላለማዊ ሕይወት ተስፋ የሚያርፍበት ስለሆነ እርሱ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ «ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና» (ኤፌ. 2፡8) ብሏል፡፡ ምስክሮቹ የሚያደርገን በውስጣችን ያለው የክርስቶስ ጸጋ ነው፡፡ አሸናፊዎች መሆን የምንችለው በበጉ ደምና በምስክርነታችን ቃል ብቻ ነው፡፡ በደንብ ሥርዓት ባለው ሕይወትና እግዚአብሔርን በሚመስል ንግግር በቤተ ክርስቲያንና በዓለም ውስጥ ብርሃን እንሆናለን፡፡ መንፈሳዊ ነገሮች በመንፈሳዊ መንገድ ተለይተው ይታወቃሉ፡፡ ከድነት ውኃ በጥልቀት የሚጠጡ ሰዎች የክርስቶስን የዋህነትና ትህትና ከሁሉ የበለጠ በሙላት ያሳያሉ፡፡ {2SM 170.2}Amh2SM 170.2

    የእግዚአብሔርን ቃል ለሌሎች ለማስተማር ለተጠሩት እንዲህ እንድላቸው ታዝዣለሁ፡- {2SM 170.3}Amh2SM 170.3

    ጥበብን ለማግኘት ሰዎች ወደ እናንተ እንዲመለከቱ በፍጹም አታደፋፍሯቸው፡፡ ሰዎች ለምክር ወደ እናንተ ሲመጡ የእያንዳንዱን ልብ ሀሳብ ወደሚመረምረው ወደ እርሱ አመልክቱአቸው፡፡ በወንጌል አገልግሎት ስራችን ውስጥ የተለየ መንፈስ መምጣት አለበት፡፡ ማንም ሰው የንስሃ አባትን ሚና መጫወት የለበትም፤ ማንም ሰው እልቅና እንዳለው ሆኖ ከፍ ከፍ ማለት የለበትም፡፡ ሥራችን ራሳችንን ዝቅ ማድረግና ክርስቶስን በሰዎች ፊት ከፍ ከፍ ማድረግ ነው፡፡ ከትንሳኤው በኋላ የእርሱ ኃይል በስሙ ከሚሄዱ ሁሉ ጋር እንደሚሆን አዳኝ ቃል ገብቷል፡፡ ይህ ኃይልና ይህ ስም ይከበር፡፡ እኔነት በእውነትና በጽድቅ እንዲቀደስ ክርስቶስ የጸለየውን ጸሎት በአእምሮአችን ፊት ሁልጊዜ መጠበቅ ያስፈልገናል፡፡ {2SM 170.4}Amh2SM 170.4

    የዘላለማዊ አባት ኃይልና የልጁ መስዋዕትነት እስከ አሁን ከተጠናው የበለጠ መጠናት አለበት፡፡ የክርስቶስ ፍጹም ሥራ የተሟላ የሆነው በመስቀል ላይ በመሞቱ ነበር፡፡ የድነታችን ብቸኛው ተስፋ በመስዋዕትነቱና በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ በማማለዱ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ባሕርይ በሰዎች ፊት ከፍ ከፍ ማድረግ እና ስሙን በምድር ላይ እንዲመሰገን ማድረግ ደስታችን መሆን አለበት፡፡ --Manuscript 137, 1907. {2SM 170.5}Amh2SM 170.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents