Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    አሁን ያለችውን ሚስቱን በመፍታት ጉዳዩ የተሻለ አይሆንም

    (ከብዙ ዓመታት በፊት፣ መጽሐፍ ቅዱስ በማይደግፈው ሁኔታ፣ ሁለተኛ ሚስትን ለማግባት የሕግ ድጋፍ ለማግኘት ሲል የመጀመሪያ ሚስቱን ፈትቶ ከሁለተኛው ሚስቱ ጋር ለብዙ ጊዜ አብሮ ከቆየ በኋላ የልጁን ጋብቻ ለማፍረስ ጥረት ላደረገ አባት የተሰጠ ምክር፡፡ ከአዘጋጆች፡፡)

    ኤምን በተመለከተ የጻፍከውን ደብዳቤ አንብቤያለሁ፡፡ ለጉዳዩ ያለኝ አመለካከት ከአንተው ጋር ተመሳሳይ ሲሆን የኤም አባት እየተከተለ ያለውን መንገድ መከተል ጭካኔ እና ክፉ መንገድ እንደሆነ አስባለሁ፡፡ የኤም ጉዳይ አሁን ያለችውን ሚስት በመፍታት አይሻሻልም፡፡ በጥያቄ ውስጥ ወዳለችው ወደ ሌላኛዋ ሴት መሄድ ጉዳዩን የተሻለ አያደርገውም፡፡ Amh2SM 341.3

    የአባቱን ጉዳይ እንግዳ የሆነ ነገር አድርጌ እቆጥረዋለሁ፣ ድርጊቱ የተፈጸመበት መዝገብም በጌታ ቀን ለማግኘት የማያስደስተው ዓይነት ነው፡፡ እሱ ስላለው መንፈስና እየሰራ ስላለው ሥራ በእግዚአብሔር ፊት መናዘዝ ያስፈልገዋል፡፡ እሱ ማድረግ ያለበት የተሻለ ሥራ ጠብን ማነሳሳትን ማቆም ነው፡፡ …አባትና ወንድም ለራሳቸው ተግተው ይስሩ፡፡ ሁለቱም የሚለውጠው የእግዚአብሔር ኃይል ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ ምስኪን ነፍሳት ከባሕርያቸው ነቁጣና ቆሻሻ እንዲያስወግዱ እና ለስህተታቸው በመናዘዝ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁ ጌታ ይርዳቸው፡፡Amh2SM 341.4

    እየተከተለ ያለው መንገድ ድርብ ድርብርብ ችግሮች ያሉበት ከመሆኑ የተነሣ ጣልቃ ለመግባት የማይመች መልስ ይዟል፡፡ ጌታ ሁኔታውን ስለሚረዳ ኤም በሙሉ ልቡ እሱን የሚፈልገው ከሆነ እሱ ይገኝለታል፡፡ እሱ የሚችለውን የሚያደርግ ከሆነ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ይቀበለዋል፡፡Amh2SM 342.1

    እጅግ ረዳተ-ቢስ የሆኑትን የሚያውቅና የሚረዳ አንድ አምላክ መኖሩን ማወቅ ምንኛ የከበረ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር እይታ እነርሱ ካላቸው ኩነኔ የከፋ ኩነኔ የሌለበትን ሰው ወደ ጥፋትና ሲኦል እየነዱ ባሉት አባትና ወንድም ላይ የእግዚአብሔር ተግሳጽ አለ፡፡ ሆኖም የንግግር ሥጦታዎቻቸውን ኤምን ተስፋ ለማስቆረጥ እና ለማደናቀፍ ይጠቀማሉ፡፡Amh2SM 342.2

    ኤም ረዳተ-ቢስ ነፍሱን በታላቁ የኃጢአት ተሸካሚ ላይ በመጣል እግዚአብሔርን ተስፋ ማድረግና ሙሉ በሙሉ ራሱን ዝቅ ማድረግ ይችላል፡፡ ለአባትም ሆነ ለልጅ አንድ ቃል አልጻፍኩም፡፡ ምስኪን የሆነው ኤም ነገሮችን እንዲያስተካክል ለማድረግ የሆነ ነገር በደስታ አደርጋለሁ፣ ነገር ግን አሁን ነገሮች ባሉበት ሁኔታ፣ ተበዳዩ በሌለበት ቦታ ላይ ይህ ሊደረግ አይችልም፡፡ Letter 175, 1901.Amh2SM 342.3