Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምክር በተጠየቀ ጊዜ ቀላል ፈውሶች ተመከሩ

    ነርሶች የቀላል ፈውሶችን ጥቅም ቢማሩና በመድሃኒቶች ፈንታ ቢጠቀሙ ኖሮ በጣም ውጤታማ ሆነው የሚያገኟቸው ብዙ ቀላል እጽዋት አሉ፡፡ በሕመም ወይም በአደጋ ጊዜ ምን መደረግ አለበት በማለት ሰዎች ብዙ ጊዜ ምክር የጠየቁኝ ሲሆን እኔም እነዚህን ቀላል ፈውሶች ነግሬያቸው ጠቃሚነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡Amh2SM 295.1

    በአንድ አጋጣሚ አንድ ሐኪም ትልቅ ሀዘን ተሰምቶት ወደ እኔ መጣ፡፡ በአደገኛ ሁኔታ የታመመችን ሴት እንዲከታተል ተጠርቶ ነበር፡፡ በስብሰባ ቦታ ትኩሳት ይዟት በአውስትራሊያ አገር በሚልቦርን አጠገብ ወዳለው የትምህርት ቤታችን ሕንፃ ተወሰደች፡፡ ሕመሟ እጅግ አስከፊ ስለነበር በሕይወት አትኖርም ተብሎ ተፈርቶ ነበር፡፡ ዶክተር ሚሪት ኬሎግ የሚባል ሐኪም ወደ እኔ መጣና «እህት ኋይት፣ በዚህ ጉዳይ ላይ የምትነግሪኝ ብርሃን አለን? እህታችን ከሕመሟ የሚያስታግሳት ነገር መስጠት ካልተቻለ መኖር የምትችለው ጥቂት ሰዓታትን ብቻ ነው» አለኝ፡፡ እኔም «ወደ ቀጥቃጭ ሱቅ ላክና የደቀቀ ከሰል አግኝ፤ ከዚያም በጨርቅ ጠቅልለህ በውኃ ንከርና በሆዷና በጎኗ አስቀምጥላት” አልኩት፡፡ የሰጠሁትን መመርያ ለመፈጸም ሐኪሙ ተቻኩሎ ሄደ፡፡ ወዲያውኑ እንዲህ እያለ ወደ እኔ ተመለሰ፣ «የከሰል ሕክምና ካደረግኩላት ከግማሽ ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ተሻላት፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተፈጥሮአዊ እንቅልፍ እየተኛች ነው፡፡» Amh2SM 295.2

    በታላቅ ሕመም እየተሰቃዩ ላሉት ሰዎች ያንኑ ሕክምና አዝዤ ሕመማቸውን ከማስታገሱም በላይ ሕይወት የማዳን መንገድ ሆኗል፡፡ እባብ፣ ሌሎች በደረታቸው የሚሳቡ ፍጡራንና መርዘኛ ነፍሳት ሲነድፉ ከሰል በጨርቅ ተደርጎ በቁስሉ ወይም በተነደፈው ቦታ ላይ ሲደረግ መርዙ ጉዳት የለሽ እንደሚሆን እናቴ ነግራኝ ነበር፡፡ በአውስትራሊያ ውስጥ አቮንዳሌ በሚባል ቦታ በነበረው መሬት ላይ ይሰሩ የነበሩ ሰዎች ብዙ ጊዜ እጆቻቸውና እግሮቻቸው ይጎዳና ሰራተኞቹ ለተወሰነ ጊዜ ሥራቸውን እስከሚተዉ ድረስ ሰውነታቸው በጣም ይቆጣ ነበር፡፡ አንድ ቀን ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ ተመሳሳይ ችግር ደርሶበት እጆቹ በወንጭፍ ታስሮ ወደ እኔ መጣ፡፡ መሬቱን ለመመንጠር የእሱ እርዳታ ይፈለግ ስለነበር ሰውዬው በሁኔታው በጣም ተጨንቆ ነበር፡፡ እኔም እንዲህ አልኩት፣ «እንጨት ታቃጥል ወደነበረበት ቦታ ሄዳህ የባሕር ዛፍን ከሰል ወስደህ አድቅቀውና ወደ እኔ ይዘህ ና፣ ከዚያ በኋላ እጅህን አክምልሃለሁ፡፡” ይህ ሕክምና ተደረገለትና በሚቀጥለው ማለዳ ሕመሙ እንደጠፋለት ነገረኝ፡፡ ወዲያውኑ ወደ ሥራው ለመመለስ ዝግጁ ሆነ፡፡ Amh2SM 295.3

    እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ የምንጠቀማቸው መድሃኒቶች የአካል ክፍሎቻችንን እንደሚያዳክሙት እና የማያደክሙ ቀላል ፈውሶችን እግዚአብሔር ሳይሰጠን ዝም እንዳላለ እንድታውቁ ነው፡፡ ጤንነትን ወደ ትክክለኛ ሁኔታ እንዲመልሱ ተፈጥሮ የምትሰጣቸውን ቀላል ፈውሶች እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው መረዳት የሚችሉ በደንብ የሰለጠኑና እነዚህ ቀላል ግን ውጤታማ የሆኑ ፈውሶችን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ስለ ጤና ሕጎች እውቀት የሌላቸውን የሚያስተምሩ ነርሶች ያስፈልጉናል፡፡Amh2SM 296.1

    ወንዶችንና ሴቶችን የፈጠረው አምላክ ስቃይ የሚደርስባቸው ሰዎች ጉዳይ ይገደዋል፡፡ የጤና ተቋሞቻችን በሚቋቋሙበት ጊዜ ትምህርት ቤቶቻችን በጤና ተቋሞቻችን አጠገብ እንዲገነቡና እየተሰቃየ ያለውን ሰብአዊ ዘር ለማገልገል ብቃት ያላቸው ወንዶችና ሴቶች የሚሰለጥኑባቸው ማዕከሎች እንዲሆኑ መመሪያ ሰጥቷል፡፡ ሕመምተኞችን ለማከም መርዘኛ የሆኑ መድሃኒቶችን መጠቀም አስፈላጊ አይደለም፡፡ የእነዚህ ክፉ ነገሮች ጣዕም በአእምሮው ስውጥ እንዳይቀረጽ አስካሪ መጠጥ ወይም ትንባሆ በማንኛውም መልክ ቢሆን መታዘዝ የለበትም፡፡ Letter 19, 1908 (To J. A. Burden and others bearing responsibility at Loma Linda).Amh2SM 296.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents