ለእኩልነት የቀረበ ተጽእኖ
በመካከላችን እኩልነት ይኑር፡፡ ከሳ ለማግኘት ከመጠን ያለፈ መስገብገብ አለ፡፡ ለተሰራ ሥራ ራስ ወዳድነት ያለበት ግምት እየተሰጠው ነው፡፡ ማንም ቢሆን አንድን ሥራ ለመስራት ብቃት እንዳለው ስለሚያስብ፣ ለእግዚአብሔርና የእርሱ ሥራ ወደፊት እንዲቀጥል የተሰራውን ሥራ በቅጥረኛነት ስሌት በማስላት ከፍተኛ ደሞዝ አይቀበል፡፡ ብዙ ከተሰጠው ብዙ ይፈለግበታል፡፡ ከችሎታዎቻቸውና ልዩ ከሆኑ ተስጦዖዎቻቸው የተነሳ ከፍተኛ ደሞዝ ማግኘት እንዳለባቸው የሚከራከሩ ሰዎች ራሳቸውን እንዲህ በማለት ይጠይቁ፡- «እየነገድኩባቸው ያሉት መክሊቶች የማን ናቸው? እነዚህን መክሊቶች ለእግዚአብሔር ከፍተኛ የሆነ ክብር ለማምጣት ተጠቅሜባቸዋለሁን? በአደራ የተሰጡኝን መክሊቶች ነግጄ አትርፌባቸዋለሁን?” እነዚህን መክሊቶች በተቀደሰ ሁኔታ መጠቀም ለእግዚአብሔር ሥራ ገቢ ያስገኛል፡፡ መክሊቶቻችን በሙሉ የእግዚአብሔር ስለሆኑ አንድ ቀን ዋናውም ሆነ ትርፉ ለእርሱ ተመልሶ ይሰጣል፡፡Amh2SM 183.3
ለብዙ ዓመታት በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ጥበብ በጎደላቸው እንቅስቃሴዎች፣ ከትክክለኛ መርሆዎች በመለየትና ሌሎችን ወደ ጠማማ መንገድ ለመምራት ያላቸውን ተጽእኖ በመጠቀም ገንዘብን ከእግዚአብሔር ሥራ ወደ ሌላ አቅጣጫ በማዞር ምን ያህል ጉዳት እንዳስከተሉ በጥንቃቄ ቢያጤኑ ኖሮ ከፍተኛ ደሞዝ ለማግኘት ከመስገብገብ ይልቅ ወደ ፊት እንዳይጸጽታቸው በእግዚአብሔር ፊት ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ንስሃ ይገቡ ነበር፡፡ ራሳቸውን የሚከተለውን ጥያቄ ይጠይቁ፡- «ለጌታዬ ምን ያህል ዕዳ አለብኝ?” (ሉቃስ 16፡ 5)፡፡ የራሴን ያልተቀደሰ ዝንባሌ በመከተል ያለ አግባብ ለተጠቀምኩት መክሊት ምን መልስ እሰጣለሁ? ለሥራው የሚያስፈልጉ ነገሮች ውስንነት እንዲኖር ያደረጉ ጥበብ የጎደላቸው እንቅስቃሴዎቼ ያስከተሉትን መጥፎ ውጤቶች ለመፋቅ ምን ማድረግ እችላለሁ?» እያንዳንዱ ሰው የተሰጠውን ቦታ በታማኝነት ቢሸፍን ኖሮ ዛሬ በጌታ ግምጃ ቤት ውስጥ የገንዘብ እጥረት አይኖርም ነበር፡፡ Amh2SM 184.1
ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር ያለን ግንኙነት ይህን ያህል ሥራ ከሰራህ ይህን ያህል ክፍያ ትከፈላለህ እንደሚለው የሰው ግምት በቅጥረኛነት መሰረት ላይ መቀመጥ የለበትም፡፡ ሰዎች አገልግሎታቸውን ተወዳዳሪ የሌለው አድርገው መገመት ትልቅ ስህተት ነው፡፡ እግዚአብሔር ለቃሉ ታማኝ እንዲሆን ከፈቀዳችሁለት ለጌታ ለተሰራው ሥራ ባለው ግምት ላይ ትልቅ ለውጥ ይኖራል፡፡ Amh2SM 184.2
ብዙ ለማግኘት ዝግጁ በሆኑ ሰዎች ውስጥ መስተካከል ያለባቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ሽልማት ለማግኘት እየተደረጉ ያሉ ራስ ወዳድነት ያለባቸው መስገብገቦች ምንኛ አግባብበት የሌላቸው ናቸው፡፡ ይህ ለከፍተኛ ክፍያ መስገብገብ ከብዙዎች ልብ የእግዚአብሔርን ፍቅር አስወጥቷል፡፡ የሥልጣን ኩራት ብዙዎችን ያጠፋ ሥር የሰደደ ክፋት ነው፡፡ አዎን፣ በአሥር ሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎች፣ ከፍ ብለው ለመታየት ካላቸው ፍላጎት የተነሳ፣ መርህን ማየት ስላቃታቸው ጠፍተዋል፡፡ ራሳቸውን ከእርስበርሳቸው ጋር አወዳድረዋል፣ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር አወዳድረዋል፡፡ ዋጋና ሽልማት ለማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት ያለበት መስገብገብ መንፈሳዊነታቸውን እንዲሟሽሽ አድርጓል፡፡ ይህ ከራስ ወዳድነትና ከንፉግነት፣ እንዲሁም ለእግዚአብሔር ያለውን ፍቅር በማጥፋት ነፍስን ከሚያዝገው ትዕቢት ለመጠበቅ ማስጠንቀቂያ እንዲሆናቸው ሁሉም መማር ያለባቸው ትምህርት ነው፡፡ Amh2SM 184.3
ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር ግንኙነት ያለው ማንኛውም ሰው ቢሆን፣ እየሰጠ ካለው አገልግሎት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ እየተሰጠው ሳለ ለሚቀበለው ደሞዝ መስራት እምቢ ሲል፣ የጠየቀውን ሊያገኝ ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን ከወርቅ፣ ከብርና ከከበሩ ድንጋዮች ይልቅ የበለጠ ዋጋ ያለውን የእግዚአብሔርን ጸጋ ከልብ ውስጥ ማጣት ይሆንበታል፡፡ --Manuscript 164, 1899.Amh2SM 185.1