ብዙ መልካምና ትንሽ የስህተት ዘር
ስለ እነዚህ ጉዳዮች የሆነ ነገር እንደማላውቅ ታስባለህን? ወደ ሰማያዊው ከነዓን በምንጓዝበት መንገድ ሁሉ ላይ የእምነት መርከባቸው የተሰበረባቸውንና በውሸት እንቅስቃሴዎቻቸው አማካይነት ልዩ በሆኑ ራዕዮች በእግዚአብሔር እንደተመሩ አድርገው በመገመት ሌሎችን ወደ ስህተት የመሩ ብዙ ነፍሳትን እናያለን፡፡ እነዚህን ስህተቶች ለማረም እጅግ ብዙ ገጾች መጻፍ ነበረብኝ፡፡ ወደ ስህተት በመመራት አደጋ ውስጥ ስለነበረው የእግዚአብሔር ርስት፣ ስለ ሕዝቡ ከነበረኝ የነፍስ ሰቆቃ የተነሳ እንቅልፍ በማጣት በየሌሊቱ ሸክም ይሰማኝና እጨነቅ ነበር፡፡ በእነዚህ ራዕዮችና ሕልሞች ውስጥ ያሉ ብዙ ነገሮች ቀጥተኛና በብዙ አመታት የስራ መስክ ውስጥ ያለ ነገር ድግግሞሽ ይመስላሉ፤ ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ትንሽ ነቁጣ እዚህ፣ ስር ሰዶ የሚያቆጠቁጥ ትንሽ የስህተት ዘር እዚያ ያስገቡና ብዙዎች ይረክሱበታል፡፡ {2SM 86.4}Amh2SM 86.4
ኦ፣ በሁሉም ነገር አሁን ካለን እጅግ የበለጠ ጥበብ ኖሮን ቢሆን ብዬ እመኝ ነበር! በጌታ የወይን ቦታ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሰው መማር ያለበት አንድ ነገር ቢኖር የክርስቶስን ጸሎት መለማመድና በክርስቶስ ኢየሱስ እንደ አንድ ሆኖ መሄድ ነው፡፡ ክርስቶስ እሱ ከአባት ጋር አንድ እንደሆነ ደቀ መዛሙርቱም አንድ እንዲሆኑ ጸለየ፡፡ ጠላት ለመከፋፈልና ለመበተን በሥራ ላይ ነው፡፡ አሁን ከመቼውም የበለጠ ኃይሎቻችንን ለመበተን ቁርጠኛ የሆኑ ጥረቶችን ያደርጋል፡፡ ከዚህ በፊት ከነበሩ ዘመኖች ሁሉ የበለጠ አሁን በራሳችን መስመሮች መሄድ አደጋ ያለበት ዘመን ነው፡፡ የወቅቱ እውነት ዝርዝሩ ሰፊና ብዙ አስተምህሮችን የሚያቅፍ ነው፤ ነገር ግን እነዚህ አስተምህሮዎች ትንሽ ሊባሉ እስከሚችሉ ድረስ የተነጠሉ ነገሮች አይደሉም፤ ክርስቶስ እንደ ሕያው ማዕከል ሆኖ የተሟለ ነገር ለመመስረት በወርቃማ ክሮች አንድ ሆነዋል፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ የምናቀርባቸው እውነቶች እንደ እግዚአብሔር ዙፋን የጸኑና የማይነቃነቁ ናቸው፡፡ {2SM 87.1}Amh2SM 87.1
ወንድሜ ሆይ፣ ኤልደር አር እና አንተ ራስህ አና ፊሊፕስን በተመለከተ ከእርሱ ሰምታ ለሕዝቡ እንድትናገር ብርሃንን የሚያስተላልፍባት መስመር አድርጎ ጌታ እንደመረጣት እርግጠኛ ሳትሆኑ የወሰዳችሁትን መንገድ የተከተላችሁት ለምንድን ነው? ወደ ፊት ከእግዚአብሔር የመጣ ራዕይ ነው እየተባለ የሚመጣውን የዚህ ዓይነት ሥርዓት ያለውን እያንዳንዱን ነገር ከተቀበልክ፣ ከዚህ በፊት እንዳደረግከው የእነዚህ ነቢያት ተብዬዎች ሥራቸው ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ የአንተን ምስክርነት ተጽእኖ በመስጠት መደገፍህን ከቀጠልክ፣ የጌታን ቅርስ ከአደጋ የምትጠብቅ ሰው አይደለህም፡፡ ክርስቶስ የሰጣቸው ማስጠንቀቂያዎች ለእኛ ጠቃሚ ነገሮች ናቸው፡፡ ማቴዎስ 24፡ 21-23ን ያንብቡ፡፡ {2SM 87.2}Amh2SM 87.2
ሰይጣን ክርስቶስን ለመምሰል በኃጢአተኝነት ማታለል ሁሉ ይሰራል፤ ከተቻለው የተመረጡትን ያታልላል፡፡ አሁን አስመሳዩ ከትክክለኛው ጋር እጅግ የቀረበ መመሳሰል ከኖረው ማንም ሰው እንዳያታልላችሁ በመጠበቂያችሁ ላይ መሆን አስፈላጊ አይደለምን? ክርስቶስ «እነሆ አስቀድሜ ነገርኋችሁ» (ማቴ. 24፡ 25) በማለት ማስጠንቀቂያዎቹን ያጸናል፡፡ ወንድሞች ሆይ፣ ቃሉን ስበኩ፣ ሰዎች እምነታቸውን እርግጠኛ ባልሆነ ነገር ላይ እንዲያሳርፉ ወይም በሰብዓዊ ወኪሎች ላይ እንዲታመኑ አትጥሩአቸው፡፡ ከጌታ ቃል አለኝ፡፡ ኤልደር አር በበርካታ ሰዎች ፊት አና ፊሊፕስ ራዕዮች ናቸው ከምትላቸው ነገሮች ውስጥ ሲያነብ እንዳይ ተደርጌያለሁ፡፡ በዚያ ቦታ የከበረ፣ ግርማ ሞገስ ያለው ሰው ነበር፤ በፊቱ ገጽታ ላይ የሀዘን ምልክት እየታየበት የተጻፈውን ነገር በማስወገድ በኤልደር አር እጅ መጽሐፍ ቅዱስን አስቀምጦ እንዲህ አለው፣ «የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መማሪያ መጽሐፍህ አድርገህ ውሰደው፣ ‹የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል” (2ጢሞ 3፡ 16-18)፡፡ {2SM 87.3}Amh2SM 87.3
ቅዱሳን መጻሕፍትን የሚመረምሩ ሰዎች በተግባራዊ የኃይማኖት ሕይወት ላይ እግዚአብሔር ምን እንደሚፈልግ ግልጽ የሆነ መመሪያ ያገኛሉ፡፡ የእግዚአብሔርን መንጋ ትኩረት ከቃሉ፣ ስህተት ከሌለበት የትንቢት ቃል ወደ ሌላ ነገር በመመለስ ስህተት እየሰራህ ነህ፡፡ የምትሰማውን በደንብ አዳምጥ፣ በምትቀበለው ነገር ላይ ጥንቃቄ ይኑርህ፡፡ የትንሹ መንጋ አእምሮዎች የመንፈስ ቅዱስ ትክክለኛ ሥራ ላልሆነው ነገር እውቅና እየሰጡ እንዳይገኙ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ቦታ ላይ እጅግ ታላቅ አደጋ አለ፡፡ ሰይጣን ምስክርን ማወክ እንዲችልና እውነትን ዝቅ አድርጎ ለማስገመት የሀሰት ነገሮችን ለማስገባት ሁል ጊዜ ይፈልጋል፡፡ ከእርሱ ጋር በእግዚአብሔር ሕዝብ መንገድ ላይ የመሰናከያ እንቅፋት የሚሆንን ነገር ይቀላቅላል፡፡ {2SM 88.1}Amh2SM 88.1
የእግዚአብሔር ትዕዛዛትና የኢየሱስ ምስክር ለዓለም ማድረስ ያለብን መልእክት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል አንድ አቅጣጫ ብቻ ያለው አይደለም፣ በሥራ መተርጎም ያለበት እውነት ነው፡፡ እንደ ፀሐይ ጨረሮች በሁሉም አቅጣጫ የሚሰፋ ነው፡፡ ትምህርቶቹን የሚያነብን፣ የሚያስተውልንና ሥራ ላይ የሚያውልን እያንዳንዱን ሰው የሚያበራ ብርሃን ነው፡፡ «ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፣ ለእርሱም ይሰጠዋል” (ያዕ. 1፡ 5)፡፡ --Letter 103, 1894. {2SM 88.2}Amh2SM 88.2