Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በእድሜ የገፉ ሠራተኞችና መምህራን መካሪዎች እንዲሆኑ

    በእድሜ የገፉ አገልጋዮቹ መካሪዎች እንዲሆኑና በአንገብጋቢ ሁኔታዎች ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ወጣቶችን እንዲያስተምሩ እግዚአብሔር ይጠራቸዋል፡፡ በዕድሜ የገፉ ሰዎች፣ ዮሐንስ እንዳደረገው ሁሉ፣ የትክክለኛ ልምምድ ሕያው ምስክሮች መሆን አለባቸው፡፡ እነዚህ ታማኝ ሠራተኞች «በጌታ የሚሞቱ ብጹአን ናቸው” (ራዕይ 14፡ 13) በሚሉ የምስክርነት ቃላት ሲያርፉ በትምህርት ቤቶቻችን አርማውን ተቀብለው በአዳዲስ ቦታዎች ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ወንዶችና ሴቶች መገኘት አለባቸው፡፡Amh2SM 227.3

    በዕድሜ የገፉ ባንዲራ ተሸካሚዎች በመስክ ላይ እያሉ በእነርሱ ልፋት ተጠቃሚ የሆኑት ሊጠነቀቁላቸውና ሊያከብሯቸው ይገባል፡፡ ሸክም አትጫኑባቸው፡፡ ምክራቸውንና የምክር ቃላቶቻቸውን አድንቁ፡፡ የሥራውን ሸክም እንደተሸከሙ አባቶችና እናቶች አድርጋችሁ ያዙአቸው፡፡ ከዚህ በፊት ሥራው የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ያሰቡ ሠራተኞች ሁሉንም ሸክም ራሳቸው ከመሸከም ይልቅ በወጣት ወንዶችና ሴቶች ትካሻ ላይ የሚያስቀምጡ እና ኤልያስ ኤልሳዕን እንዳስተማረ እነርሱን የሚያስተምሩ የከበራ ሥራ ይሰራሉ፡፡Amh2SM 227.4

    ዳዊት ከመለኮት ስለተቀበለው ትምህርትና ምሪት ለአምላኩ የምሥጋና ሥጦታ አቀረበ፡፡ «አምላኬ፣ ከታናሽነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ” አለ (መዝ. 71፡ 17)፡፡ በመልእክቱ ታሪክ ውስጥ ሸክምንና የቀኑን ሙቀት የተሸከሙ ሰዎች ከወጣትነታቸው ጀምሮ «ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፣ ከእኔም ተማሩ (ማቴ. 11፡ 29) ብሎ ያስተማራቸው፣ የጋበዘውና የእውነት ብርሐን የሰጣቸው ጌታ ያኔ እነርሱን እንዳስተማራቸው ሁሉ ዛሬም ወጣት ወንዶችንና ሴቶችን ለማስተማር ፈቃደኛ መሆኑን ያስታውሱ፡፡Amh2SM 227.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents