ለአንድ ወንድምና ለሚስቱ የተሰጠ ምክር
ውድ ወንድም እና እህት ኤል፡-
በቅርብ ጊዜ፣ ልነግራችሁ የሚገቡኝ አንዳንድ ነገሮች ማታ በራዕይ በፊቴ ተገልጠው ነበር፡፡ አንዳንድ አሳዛኝ ስህተቶችን እየፈጸማችሁ እንደሆነ እንዳይ ተደርጌያለሁ፡፡ ቅዱሳን መጻሕፍትንና ምስክሮችን ስታጠኑ ሳለ ከተሳሳቱ ድምዳሜዎች ላይ ደርሳችኋል፡፡ አሁን ለመሥራት በጀመራችሁት መንገድ ከቀጠላችሁ ሰዎች የእግዚአብሔርን ሥራ በከፍተኛ ደረጃ በስህተት ያስተውላሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ቃልና ለተጻፉ ምስክሮች የውሸት ትርጉም ትሰጣላችሁ፤ በእናንተ ሀሳብ ለእነርሱ ባላችሁ ትርጉም መሠረት እንግዳ የሆነ ሥራ መሥራታችሁን መቀጠል ትሻላችሁ፡፡ አጋንንትን እንድታወጡ ኃይል እንደተሰጣችሁም አምናችኋል፡፡ እናንተ በሰዎች አእምሮ ካሳደረችሁት ተጽዕኖ የተነሳ ወንዶችና ሴቶች በአጋንንት እንደተያዙ እና እነዚህን ክፉ መናፍት ለማውጣት እግዚአብሔር ወኪሎቹ አድርጎ እንደሾማችሁ ወደ ማመን ተመርተዋል፡፡ {2SM 44.5}Amh2SM 44.5
ባለቤትህ በንግግር፣ በመዝሙር እና ከትክክለኛው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ጋር በማይጣጣሙ እንግዳ በሆኑ ትርኢቶች አማካይነት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማንኛውም ቦታ ቢሰጠው ኖሮ የእግዚአብሔርን ሥራ በከፍተኛ ደረጃ ሊጎዳ የሚችል የወግ አጥባቂነት ገጽታን ለማምጣት እየረዳች ነው፡፡ {2SM 45.1}Amh2SM 45.1
ወንድሜና እህቴ ሆይ፣ ለእናንተ መልእክት አለኝ፡- የውሸት ሀሳብ እየጀመራችሁ ነው፡፡ በትርኢቶቻችሁ ውስጥ በራሳችሁ የተሸመነ ብዙ ነገር አለበት፡፡ በእነዚህ ትርኢቶች አማካይነት ሰይጣን የአስማት ኃይሉን ይዞ ይመጣል፡፡ ቆም የምትሉበት ወሳኝ ሰዓት ነው፡፡ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚሆን የተለየ መልእክት ሰጥቷችሁ ቢሆን ኖሮ በትያትር መድረክ ላይ እንዳላችሁ ሳይሆን ራሱን ዝቅ ያደረገው የናዝሬቱ ኢየሱስ ተከታይ በሚኖረው የዋህነት በትህትና ትሄዱና ትመላለሱ ነበር፡፡ የምታሳድሩት ተጽዕኖ አሁን እያሳደራችሁ ካላችሁት ሙሉ በሙሉ የተለየ ይሆን ነበር፡፡ . . . {2SM 45.2}Amh2SM 45.2
ለሌሎች መልካም የማድረግ ልባዊ ፍላጎት ክርስቲያን ሠራተኛን በወቅቱ እውነት ውስጥ ወንዶችንና ሴቶችን ወደ ወግ አጥባቂነት የሚመራ ምንም ዓይነት እንግዳ የሆነ አስተምህሮ የማምጣት ሀሳብን እንዲያስወግድ ያደርጋል፡፡ በዚህ የዓለም ታሪክ ወቅት በዚህ ረገድ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ {2SM 45.3}Amh2SM 45.3
እናንተ እያለፋችሁበት ያላችሁትን ልምምድ የሚገልጹ አንዳንድ ሀረጎች የእናንተን ነፍስ ብቻ ሳይሆን የሌሎች ብዙ ሰዎችን ነፍስ ለአደጋ ያጋልጣሉ፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የእናንተ መልእክት ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ በቅዱሳን መጻሕፍት ወዳሉት የክርስቶስ ቃላትና ወደ ምስክርነቶች ስለምትማጸኑ ነው፡፡ እውነትነት ያለውንና እውነት የሆነውን ክቡር ቃል እና እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጣቸውን ምስክርነቶች የእናንተ ኃይል አድርጋችሁ ከገመታችሁ ተታላችኋል፡፡ በተሳሳቱ ስሜቶች ተነድታችኋል፣ ወደ ስህተት በሚመሩ ገለጻዎች ራሳችሁን እያነቃቃችሁ ነው፡፡ የእግዚአብሔር እውነት ተለዋዋጭ እና ወግ አጥባቂ የሆኑ የውሸት ሀሳቦችን እንዲደግፍ ለማድረግ ትጥራለህ፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን ሰዎችን ከሦስተኛው መልአክ መልእክት እውነቶች ጋር ለማስተዋወቅ እየሰራች ያለችውን ሥራ አሥር እጥፍ፣ እንዲያውም ሃያ እጥፍ ከባድ ያደርገዋል፡፡--Letter 358a, 1908. {2SM 45.4}Amh2SM 45.4