Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የራስ ወዳድነትና የክፉ ምኞት አጥፊ ውጤቶች

    ለአንዳንድ ዓለማዊ ማባበያዎች በማለት ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚያቋርጡ ሰዎች በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ ፍላጎት እንዳላቸው ሊያስቡ ይችላሉ፤ ነገር ግን በሰው ልብ ውስጥ እያደቡ ያሉት ራስ ወዳድነትና ክፉ ምኞት እጅግ ኃይለኛ የሆኑ ስሜቶች ስለሆኑ ከሚፈጠረው ግጭት የሚገኘው ውጤት ተራ የሆነ ግምት ነው፡፡ ነፍስ በየቀኑ የክርስቶስን ሥጋ በመብላትና ደሙን በመጠጣት ካልኖረች በስተቀር መለኮታዊ ባሕርይ በሰይጣናዊ ባሕርይ ይሸነፋል፡፡ ራስ ወዳድነትና ክፉ ምኞት ድልን ይቀዳጃሉ፡፡ በራሱ የሚተማመን፣ በራሱ የሚወስን መንፈስ በፍጹም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት አይገባም፡፡ ከክርስቶስ ጋር የክብሩ ተካፋዮች የሚሆኑት በእርሱ ራስን የመካድና መስዋዕት የማድረግ ሥራ ላይ ተካፋዮች የሆኑት ብቻ ናቸው፡፡Amh2SM 216.1

    በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ድነት ለራሳቸውም ሆነ እንደ እነርሱ ላሉት ሌሎች ሰዎች ምን ማለት እንደሆነ የሚገነዘቡ ሰዎች በእምነት ይሄዳሉ፣ በተወሰነ ደረጃ የሰብአዊነትን ፍላጎቶችም ይገነዘባሉ፡፡ በዓለማችን ውስጥ ተስፋፍቶ ያለውን ድህነት- ማለትም ብዙ ሕዝብ ምግብና ልብስ በማጣት የሚሰቃዩ ሲሆን ይህ የአካል ስቃይ ከእነርሱ ጋር ሲነጻጸር ምንም እንዳልሆነ የሚታይበት እልፍ አእላፋት ሰዎች አስከፊ በሆነው የሞራል ድህነት እርግማን ጥላ ስር ያሉበትን ሁኔታ- መመልከት ልባቸው በርኅራኄ ስሜት እንዲነካ ያደርጋል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ኃይማኖት በሰብአዊ ራስ ወዳድነት ላይ አስደናቂ የሆኑ ድሎችን ተቀዳጅቷል፡፡ የክርስቶስ ራስን መካድና መስዋዕት ማድረግ ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር አብረው ሰራተኞች በሆኑት ሰዎች ፊት ስላለ የሰው ፈቃድ በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ይዋጣል፡፡...Amh2SM 216.2

    ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ሰራተኞች የሆኑ ሁሉ ከእርሱ ፍቅርና የማዳን ኃይል ጋር የጎለበተ ልምምድ እንዲኖራቸው እርሱ መንገዶችን ያዘጋጃል፡፡ ለጳውሎስ ልምድ የሰጠው እግዚአብሔር ከእውነተኛ ልቡ እርሱን ተግቶ ለሚሻ ነፍስ ራሱን ስለሚገልጥ በፍጹም «ልምድ የለኝም» ማለት የለብንም፡፡ እግዚአብሔር ለአብርሃም ምን ነበር ያለው? ልብን የሚመረምር እግዚአብሔር እንዲህ አለ፣ «ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና» (ዘፍ. 18፡ 19)፡፡ አብርሃም የቤት ኃይማኖትን ስላሳደገ ፈርሀ-እግዚአብሔር ወደ ሕይወት ታማኝነት ይመራል፡፡ የጻድቁን መኖሪያ የሚባርክ እንዲህ ይላል፣ «እርሱ ልጆቹንና ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁ፡፡” ቅዱስ ሀላፊነቶችን መካድ፣ ትክክልና ስህተት በሆኑ ነገሮች መካከል ማመንታት የለም፡፡ ቅዱስ የሆነው ማንም ከእነርሱ ቢርቅ ከበደል ነጻ መሆን የማይችልባቸውን የባሕርይ መስፈርቶችን ወይም ሁሉን የሚመሩ ደንቦችን ሰጥቷል፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ በትጋትና በማስተዋል መጠናት ያለበት ሲሆን በሁሉም የሕይወት ጉዳዮች ውስጥ ከሁሉም በላይ የሆነ ቦታ ሊሰጠው ይገባል፡፡ እያንዳንዱ ሰብአዊ ፍጡር መታዘዝ ያለበት ሕጎች የሚፈልቁት መጨረሻ ከሌለው የፍቅር ልብ ነው፡፡ Amh2SM 216.3

    ያው «አብርሃምን አውቃለሁ” የሚለው ቅዱስ ጠባቂ ቆርኔሊዎስንም ስላወቀ እግዚአብሔር የሰጠውን ብርሐን ሁሉ ለተቀበለውና ላሻሻለው ሰው መልእክት አስይዞ መልአኩን ላከለት፡፡ መልአኩ እንዲህ አለ፣ «ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ፡፡ አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ፡፡» ከዚያ በኋላ ዝርዝር መመሪያዎችን ሰጠው፣ «እርሱ ቤቱ በባሕር አጠገብ ባለው በቁርበት ፋቂው በስምዖን ዘንድ እንግድነት ተቀምጧል” (የሐዋ. 10፡ 4-6)፡፡ በመሆኑም የእግዚአብሔር መልአክ ለቆርኔሌዎስ የበለጠ ብርሃንን ሊያጋራው ከሚችል ሰብአዊ ወኪል ጋር ግንኙነት በመፍጠር ሰራ፡፡ ምዕራፉን በሙሉ በጥንቃቄ ያንብቡና ጠቅላላው ሂደት እንዴት ግልጽ እንደነበር ይመልከቱ፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን በስማችን እንደሚያውቅ፣ የት እንደምንኖርና ያለንን መንፈስ፣ የሕይወታችንን እያንዳንዱን ተግባር እንደሚያውቅ ልብ ይበሉ፡፡ አገልጋይ መላእክት በግል የስራ መስመራችን ያለንን ታማኝነት በመመዝገብ በቤተ ክርስቲያናት ውስጥ እያለፉ ናቸው፡፡ Amh2SM 217.1

    ለሥራ የምናሳየውን ቸልተኝነት በተመለከተም ማስታወሻ ይወስዳሉ፡፡ የአናኒያንና የሰጲራን ሁኔታ ልብ በሉ፡፡ ንብረታቸውን በሙሉ ለእግዚአብሔር እንደቀደሱ በማስመሰል ቅዱስ መንፈስን ዋሹ፣ ከዚህ የተነሳ የአሁኑን ሕይወት ብቻ ሳይሆን የወደፊቱንም ሕይወት አጡ፡፡ ሰዎች ቅዱስ ነገሮችን ይዘው ከኃጢአታቸው ጋር እግዚአብሔርን ለማገልገል በማዘጋጀት በአገልግሎት ውስጥ የራሳቸውን ልዩ የሆኑ ባሕርያት ማምጣት አሳዛኝ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልግባቸው ሀላፊነት በተሰጣቸው ቦታ የክርስቶስን አእምሮ እንዲያሳዩ ነው፣ ነገር ግን የሚያስጠሉ ባሕርያት በሥራቸው ሁሉ ውስጥ እንደ መረብ ስለተጠላለፉ የተቀደሰው የእግዚአብሔር ሥራ በእነርሱ ራስ ወዳድነት ተበላሽቷል፡፡ የሀላፊነትን ሸክም የተሸከሙ ሰዎች በእያንዳንዱ ስራ ውስጥ ጥብቅ የሆነ ታማኝነትን በመጠበቅና በሚሰሩት በእያንዳንዱ የስራ ክፍል ውስጥ አሻራ በማሳረፍ ታማኝ መጋቢዎች መሆን አለመሆናቸውን ጌታ ያውቃል፡፡. . .Amh2SM 217.2

    ልብህ አዝኗል፣ ነገር ግን ወንዶችና ሴቶች ልቦቻቸውን ለኢየሱስ እስከሚከፍቱበት ጊዜ ድረስ እግዚአብሔር ከራሱ ቅድስና የሰጣቸውን ብርሃን ዋጋ ይሰጣሉ በማለት ራስህን አታታልል፣ ወይም አትጠብቅ፡፡ እርሱ እንዲህ ይላል፡- « በእኔ ተደገፉ፣ በእኔ ታመኑ፡- አልጥላችሁም፤ በሚያስፈልጋችሁ ጊዜ ሁሉ የሚገኝ እርደታ እሆንላችኋለሁ፡፡» Amh2SM 218.1

    አሁን በሪቪው ቢሮ ውስጥ ወሳኝ የሆኑ ቦታዎችን የያዙ ሰዎች እንደሚፈተኑ እንዳይ ተደርጌያለሁ፡፡ ክርስቶስን አጋራቸው የሚያደርጉ ከሆነ እርሱ ጥበብን፣ እውቀትንና ማስተዋልን ይሰጣቸዋል፤ በክርስቶስ መንገድ በጸጋና በእውቀት ያድጋሉ፤ ባሕርያቸው በእርሱ አምሳያ ይቀረጻል፡፡ የእግዚአብሔርን መንገድ መጠበቅ ካልቻሉ ሌላ መንፈስ አእምሮንና የማገናዘብ ችሎታቸውን ስለሚቆጣጠር ያለ እግዚአብሔር እቅዶችን ያወጣሉ፣ የራሳቸውን መንገድ ይከተላሉ፣ የያዙትንም ሀላፊነት ይለቃሉ፡፡ ብርሃን ተሰጥቷቸዋል፤ ከዚህ ብርሃን ከተለዩና የራሳቸውን መንገድ ከተከተሉ እነርሱ በቦታቸው እንዲቆዩ ለማድረግ ማንም ሰው ጉቦ አይስጥ፡፡ እነርሱ እንቅፋትና ወጥመድ ይሆናሉ፡፡ መበጠር ያለበት ነገር ሁሉ መበጠር ያለበት ጊዜ መጥቷል፣ ተበጥረው የማይወጡት ነገሮች ይቀራሉ፡፡--Letter 20a, 1893. Amh2SM 218.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents