Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በከተሞች ውስጥ መቋቋም ያለባቸው ቤተ ክርስቲያናት እንጂ ተቋሞች አይደሉም

    ለከተሞች መሥራት ያለብን ከከተማ ራቅ ብለው ካሉት ማዕከላት እንደሆነ ጌታ በተደጋጋሚ መመሪያ ሰጥቶኛል፡፡ በእነዚህ ከተሞች ውስጥ የእግዚአብሔር መታሰቢያ እንዲሆኑ የአምልኮ ቤቶች ሊኖሩን ይገባል፤ ነገር ግን ሥነ-ጽሁፎቻችንን የምናትምባቸው፣ ሕሙማንን የምንፈውስባቸው እና ሰራተኞቻችንን የምናሰለጥንባቸው ተቋሞች ከከተሞች ውጭ መቋቋም አለባቸው፡፡ በተለየ ሁኔታ ወጣቶቻችን ከከተማ ሕይወት ፈተናዎች መከለል አለባቸው፡፡Amh2SM 358.3

    ከዚህ መመሪያ ጋር በተጣጣመ ሁኔታ የመሰብሰቢያ ቤቶች በዋሽንግተን እና ናሽቪሌ ተገዝተው ለአገልግሎት የተለዩ ሲሆን በእነዚያ ማዕከሎች ያሉ ማተሚያ ቤቶችና የጤና ማዕከሎች ከተጨናነቀ የከተሞች ልብ ወጥተው ራቅ ባሉ ጣቢያዎች ተቋቁመዋል፡፡ ይህ ዕቅድ ሌሎች የማተሚያ ቤቶችንና የጤና ማዕከሎችን ወደ ገጠር ለመውሰድ የተከተልነው ዕቅድ ነው፣ ይህ ዕቅድ በታላቋ ቢርታኒያ ያለውን የለንደን ማተሚያ ቤትንና ሌሎች ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶችን ከከተማ ለማውጣት ሥራ ላይ እየዋለ ነው፡፡ እግዚአብሔር በፈቃዱ እየከፈተ ባለው መንገድ በእነዚህና በሌሎች ጠቃሚ በሆኑ ብዙ ማዕከሎች ሥራው በጥንካሬ ወደ ፊት እንዲቀጥል በጽኑ መሰረት ላይ ለመመስረት ወንድሞቻችንን በመርዳት ሥራውን ወደ ፊት ለማስቀጠል አሁን ዕድል ተሰጥቶናል፡፡ Special Testimonies, Series B, No. 8, pp. 7, 8 (1907).Amh2SM 358.4

    በገጠር ውስጥ ንብረትን በአነስተኛ ወጪ ለማግኘት በምናደርገው ጥረት እንደ እባብ ጠቢናንና እንደ ርግብ የዋሆች መሆን አለብን፡፡ ከእነዚህ ማዕከሎች በመነሳት በከተሞች መሥራት አለብን፡፡ Ibid., No. 14, p. 7 (1902).Amh2SM 359.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents