Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እግዚአብሔር አልተዋችሁም

    ውድ ስቃይ የደረሰባችሁና ክፉኛ ያዘናችሁ ሆይ፣ የሰይጣን ፈተናዎች መጫወቻ እንድትሆኑ እግዚአብሔር አልተዋችሁም፡፡ ያዘኑ ልቦቻችሁ ከሚያዝንላችሁ አዳኝ የማጽናኛ ቃላትን ለመቀበል ይከፈቱ፡፡ ኢየሱስ ይወዳችኋል፡፡ የጽድቅ ፀሐይን ብሩህ ጮራዎች ተቀበሉና ተጽናኑ፡፡ ከሙታን የተነሳውንና ለእናንተ ለማማለድ ሁልጊዜ የሚኖረውን አመስግኑ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው አዳኝ ነው፡፡ እርሱ በዮሴፍ አዲስ መቃብር ውስጥ አይደለም፡፡ ተነስቷል! ተነስቷል! በሀዘናችሁ ሁሉ የሚራራላችሁ አዳኝ ስላላችሁ በዚህ የሀዘንና የልቅሶ ቀን ደስ ይበላችሁ፡፡ በአልኣዛር መቃብር አልቅሷል፣ ዛሬም ከሚያዝኑ ልጆች ጋር አብሮ ያዝናል፡፡ Amh2SM 272.2

    በጦርነቶቻችሁ ሁሉ፣ በሕይወት ፈተናዎችና ግራ መጋባቶች ሁሉ፣ ከእግዚአብሔር ምክርን ፈልጉ፡፡ ለእግዚአብሔር የመታዘዝ መንገድ ብሩህነቱ እየጨመረ ሄዶ እስከ ሙሉ ቀን እንደሚደርስ እንደሚበራ ብርሃን ነው፡፡ በተግባር መንገድ ላይ ከአንዱ እርምጃ ወደ ሌላኛው ተከተሉ፡፡ አቀበት መውጣት ሊኖር ይችላል፣ ነገር ግን የጥርጣሬ ደመናዎችን ከኋላችሁ በመተው በትህትና፣ በእምነትና ራስን በመካድ መንገድ ወደ ፊት ሂዱ፡፡ በሕይወት ያሉት የእናንተን ፍቅርና እንክብካቤ ስለሚፈልጉ ተስፋቢስ በሆነ መንገድ አትዘኑ፡፡ በእግዚአብሔር ሰራዊት ውስጥ ተመልምላችኋል፤ የኢየሱስ ክርስቶስ ጀግና ወታደሮች ሁኑ፡፡ የንስሃና የምስጋና ቃላት በሰማያዊ ቤተ መቅደስ ባለው በእግዚአብሔር ፊት እንደ ጣፋጭ እጣን ይውጡ፡፡ Amh2SM 272.3

    ተስፋ ልትቆርጡ ትችላላችሁ፣ ፈቃዳችሁና መንገዳችሁም ተቀባይነት ሊያጣ ይችል ይሆናል፤ ነገር ግን ጌታ እንደሚወዳችሁ እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ሊያጠፋችሁ ሳይሆን ሰባት ጊዜ በእሳት ተፈትኖ እንደ ነጠረ ወርቅ እንድትሆኑ ቆሻሻውን ሊያቃጥል የእቶኑ እሳት በላያችሁ ሊነድ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር በሌሊት ዝማሬ ሊሰጣችሁ እንደሚችል አስታውሱ፡፡ ጨለማ የሚሸፍናችሁ ሊመስል ይችላል፣ ነገር ግን ደመናዎችን መመልከት የለባችሁም፡፡ ከድቅድቅ ጨለማው ባሻገር ሁልጊዜ የሚያበራ ብርሃን አለ፡፡ ኢየሱስ ለእያንዳንዱ ነፍስ ብርሃን ነው፡፡ የልብን በር ለተስፋ፣ ለሰላም እና ለደስታ ክፍት አድርጉ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ይላል፣ “ደስታዬም በእናንተ እንዲሆን ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን ነግሬአችኋለሁ” (ዮሐ. 15፡ 11)፡፡ Amh2SM 272.4

    እግዚአብሔር እያንዳንዱ ሰው የሚሰራለት ሥራ ስላለው እያንዳንዳችን እርሱ የሰጠንን ሥራ በደንብ መሥራት እንችላለን፡፡ በእኛ በኩል መፍራት ያለብን ብቸኛው ነገር ቢኖር የጦር መሣሪያዎቻችንን አስቀምጠን በሞት እንድናርፍ የምንጠራ ቢሆን የተሰጠንን ኃላፊነት በታማኝነት ለመፈጸማችን ምላሽ መስጠት እስከማንችል ድረስ ሁልጊዜ ዓይናችንን በኢየሱስ ላይ አለማድረግን፣ እና በእግዚአብሔር ክብር ላይ ዓይናችንን አለማተኮርን ነው፡፡ ክርስቶስን በመንፈሳችሁ እና በአካላችሁ እንድታከብሩት በዘላለማዊ ዋጋ የተገዛችሁ የእርሱ ንብረት መሆናችሁን ለአፍታ እንኳን አትርሱ፡፡ Amh2SM 273.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents