Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከሌሎች መንገዶች ይልቅ እጅግ በጣም ጥሩ መንገድ

    አእምሮንና ጡንቻን የሚያሰራው ያው ኃይል ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ሠራተኞች እንዲሆኑ የሚያደርጋቸውን ሚስዮናዊ ሥራ እንዲሰሩ ከፍተኛ ብቃት ያለውን መንገድና ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል፤ የትምህርት እጅግ ጠቃሚ ዘርፍ የሆነውን ጠቃሚ ሥራ በመሥራት በአሁኑ ሕይወት ለበለጠ ጠቃሚነት ሊያስተምራቸው ይችላል፡፡Amh2SM 322.3

    ወጣቶች ራሳቸውን እንዲያስደስቱ ሳይሆን እርሱን እንዲያስከብሩ እና የእርሱን ሥራ እንዲገነቡ እግዚአብሔር የሰጣቸውን መክሊቶች ትርፋማ ሊያደርጉ የሚችሉባቸው በርካታ መንገዶች አሉ፡፡ የሰማይ ንጉሥ፣ የክብር ንጉሥ፣ ሰብዓዊ ዘርን ከፍ ለማድረግና እንዲከብሩ ለማድረግ ወደ እኛ ዓለም በመምጣት ዘላለማዊ መስዋዕት አደረገ፡፡ እርሱ የማይሰለች ትጉህ ሰራተኛ ነበር፡፡ እርሱ «መልካም እያደረገ ዞረ» (የሐዋ. 10፡38) የሚለውን እናነባለን፡፡Amh2SM 322.4

    እያንዳንዱ ወጣት ለማድረግ መሻት ያለበት ሥራ ክርስቶስ በሰራበት መንገድ መሥራት መሆን የለበትምን? የክርስቶስ እገዛ አለላችሁ፡፡ የተማሪዎች ሀሳብ ይሰፋል፡፡ ያለማቋረጥ የሚያድጉ ከሆነ በተማሪነት ሕይወት እንኳን ብዙ ማድረግ የሚችሉ እና ለሚጠቅም ነገር ኃይል የሚሆኑ ይሆናሉ፡፡ በመጨረሻም «መልካም፣ አንተ በጎ ታማኝም ባርያ(ማቴ. 25፡ 21) ስትባል እንድትሰማ እግዚአብሔር የሰጣቸው ክንዶችና እጆች የሰማይን ምልክት የሚይዝ መልካም ሥራ ለመስራት ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው፡፡Amh2SM 323.1

    ጉዳዩ በፊቴ ከቀረበልኝ ሁኔታ በመነሳት የኳስ ጨዋታዎቻችሁ ተግባርን በሚመዝነው በእርሱ ግምት የተማሪዎቹ ባሕርይ ለተዋንያኑ ሽልማት በሚያስገኝ መልኩ እየተካሄደ ነው ብዬ አላስብም፡፡Amh2SM 323.2

    ለጌታ ለመስራት ነቅቶ በመጠበቅ እና ያሉትን መልካም አጋጣሚዎች በማሻሻል ረገድ ክርስቲያን ጥረት ለማድረግ ያለውን ዕቅድ በመከተል፣ በእያንዳንዱ ሀላፊነት በሚሰማው ሰብዓዊ ወኪል አማካይነት ምን ሊደረግ እንደሚቻል የሚመለከት ቡድን ይመስረት፡፡ እያንዳንዱ ሰው መልካም ሥራ መሥራት የሚችልበት የወይን ቦታ አለው፡፡ እየተሰቃየ ያለው ሰብአዊነት እርዳታ ይፈልጋል፡፡ ተማሪዎች ቃልን በጊዜው በመናገር፣ የጉልበት ሥራን ለሚፈልጉ እንኳን መልካም በመስራት ወደ ሰዎች ልብ መድረስ ይችላሉ፡፡ ይህንን ማድረግ ማናችሁንም ቢሆን ዝቅ የማያደርግ ሲሆን ለተፈጸመው ተግባር እግዚአብሔር ማረጋገጫ የመስጠቱን ሀሳብ ያመጣል፡፡ በጥበብ እንድትጠቀሙ የተሰጡአችሁን መክሊቶች ነግደው ለሚያተርፉ ሰዎች መስጠት ይሆናል፡፡ እነርሱን ነግዶ ያተርፍባቸዋል፡፡Amh2SM 323.3

    ለነፍስም ሆነ ለአካል በሚጠቅም ሁኔታ ሊታቀዱ የሚችሉ ጤናማ የእንቅስቃሴ ዘዴዎች አሉ፡፡ መሰራት ያለበት ትልቅ ሥራ ስላለ እያንዳንዱ ኃላፊነት የሚሰማው ወኪል ይህንን ሥራ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ባለው መልኩ ለመሥራት ራሱን ማስተማር አለበት፡፡ ሁላችንም መማር ያለብን ብዙ ነገር ስላለ መልካምን በማድረግና በዚህ ስድና አባካኝ በሆነ ዘመን ውስጥ የሚታዩ ክፉ ነገሮችን ለማስተካከል አንዳንድ ሰብዓዊ መሳሪያዎችን ሥራ ላይ ለማዋል የእግዚአብሔርን ጥበብ ከመቀበል ይልቅ አእምሮን አጥንትን እና ጡንቻን በተሻለ ሁኔታ መጠቀም የሚያስችል ሌላ ዘዴ መፈልሰፍ አይቻልም፡፡ Amh2SM 323.4

    ወጣቶች የሌሎች ሰዎችን የሥራ ክብደት በማቅለል፣ የሚያዝኑትን በማጽናናት፣ ተስፋ የቆረጡትን መንፈሳቸውን በማንሳት፣ ተስፋ ለሌላቸው የማጽናኛ ቃላትን በመናገር፣ የተማሪዎችን አእምሮዎች ከወንድነትና ሴትነት ክብር ወደ ውርደትና እፍረት ከሚወስዳቸው ቀልድና ፌዝ በመመለስ እግዚአብሔር ለወጣቶች የሰጣቸውን ጡንቻና አእምሮ በመጠቀም መልካም እንዲያደርጉ መሻት ሁል ጊዜ ሀላፊነታችን ነው፡፡Amh2SM 323.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents