Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መክሊቶች የእግዚአብሔር ናቸው

    በጽድቅ የሚፈርድ እንዲህ ብሏል፣ «ያለ እኔ ምንም ነገር ማድረግ አትችሉም” (ዮሐ. 15፡ 5)፡፡ መክሊቶች ሁሉ፣ ትንሽም ቢሆኑ ትልቅ፣ እርሱን ለማገልገል ጥቅም ላይ እንዲውሉ በእግዚአብሔር የተሰጡ ስለሆኑ ሰዎች ዝም ብለው ችሎታቸውን ለራሳቸው ሲጠቀሙበትና ከእነርሱ ጋር ተመሳሳይ እምነት ካላቸው በሕክምና ልምምድ ውስጥ ካሉት ጋር በተጣጣመ ሁኔታ ለመስራት የተለየ ጥንቃቄ ካላደረጉ፣ ራሳቸው በእነዚህ ሰዎች ላይ ወደ መፍረድ ያዘነበሉ መሆናቸውን ያሳያሉ፤ እርሱ ከአባቱ ጋር አንድ እንደሆነ እነርሱም አንድ ይሆኑ ዘንድ የጸለየውን የክርስቶስን ጸሎት ለመመለስ አይሹም፡፡ ለአገልግሎቶቻቸው ከፍተኛ የሆነ ዋጋ በሚጠይቁበት ጊዜ፣ የምድር ሁሉ ፈራጅ የሆነው እግዚአብሔር ራሳቸው ስለራሳቸው በሰጡት ከመጠን ያለፈ ግምት ይይዛቸውና ለራሳቸው በሰጡት ዋጋ መጠን ይፈልግባቸዋል፡፡Amh2SM 195.1

    የራሳቸውን ጠቃሚነት ከገንዘብ አንጻር ሲፈርዱ፣ እግዚአብሔር ደግሞ አገልግሎታቸውን ለራሳቸው ከሰጡት ዋጋ ጋር በማነጻጸር ከሥራቸው የተነሳ ይፈርዳል፡፡ ለችሎታው ከመጠን በላይ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጥ ሰው በክርስቶስ አገልግሎት ውስጥ የግል ተጽእኖው ለራሱ ካለው ግምት ጋር ወይም ሌሎችን ላገለገለበት አገልግሎት ከሚጠይቀው ዋጋ ጋር በፍጹም ስለማይመጣጠን ካልተለወጠ በቀር በፍጹም ወደ ሰማይ አይገባም፡፡. . . .Amh2SM 195.2

    ራስ ወዳድና ስግብግብ የሆነ ሰው፣ ለሰጣቸው አገልግሎቶች ከተቋሞቻችን ማግኘት የሚችለውን እያንዳንዱን ዶላር ለመውሰድ የሚጓጓ ሰው የእግዚአብሔር ሥራ ወደ ፊት እንዳይቀጥል እየገደበ ነው፤ በእርግጥ ዋጋውን አግኝቷል፡፡ ራሳቸውን በመካድ መስቀልን ተሸክመው ለሚከተሉት ክርስቶስ ሊያዘጋጅላቸው በሄደው በሰማይ ቤት የተዘጋጀውን ሽልማት ለመቀበል ብቁ ሆኖ አይቆጠርም፡፡ ሰዎች በደም ወደ ተገዛው ውርስ የመግባት ብቃታቸው የሚፈተነው በዚህ የመጠበቂያ ጊዜ ውስጥ በሚኖሩት ሕይወት ነው፡፡ ለወደቀው ሰው ድነት ራሱን አሳልፎ በሰጠ ጊዜ በክርስቶስ የታየው ራስን መስዋዕት የማድረግ መንፈስ ያለባቸው ሰዎች ጽዋውን የሚጠጡና ጥምቀቱን የሚጠመቁ፣ የአዳኙን ክብር የሚጋሩ እነርሱ ናቸው፡፡--Letter 41, 1890.Amh2SM 195.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents