Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የአንጋፋ ሠራተኞች ተጽዕኖ

    በእምነት ወጣት የሆኑት ከዚህ በፊት ጌታ የሰጠን መልእክቶች አሁን የምድር ታሪክ ባለበት ደረጃ እጅግ ጠቃሚ መሆናቸውን ማስተዋል እንዲችሉ በጌታ ሥራ የሸበቱት የመስቀሉ አንጋፋ ወታደሮች ምስክርነታቸውን ቀጥታ እስከ ነጥቡ ማድረስ እንዲችሉ እፈልጋለሁ፡፡ ያለፈው ልምምዳችን ከነበረው ኃይል አንዲት ነጥብ እንኳን አላጣም፡፡Amh2SM 406.1

    ፈር-ቀዳጆችን ተስፋ እንዳያስቆርጡ ወይም እነርሱ ሊሰሩ የሚችሉት እጅግ ጥቂት እንደሆነ እንዲሰማቸው እንዳያደርጉ ሁሉም ይጠንቀቁ፡፡ በጌታ ሥራ ውስጥ የእነርሱ ተጽእኖ አሁንም ቢሆን በኃይል ሊሰማ ይችላል፡፡ በእድሜ የገፉ አገልጋዮች ምስክርነት ሁልጊዜም ቢሆን ለቤተ ክርስቲያን አጋዥና በረከት ሊሆን ይችላል፡፡ እግዚአብሔር የተፈተኑና ታማኝ የሆኑ የእርሱን አርማ ተሸካሚዎች የጦር መሣሪያቸውን የሚያስቀምጡበት ጊዜ እስኪመጣ ድረስ ቀንና ማታ ይጠብቃቸዋል፡፡ በፍጹም በማይተኛውና በማያንቀላፈው ጥበቃ ስር እንደሆኑ እርግጠኞች ይሁኑ፤ በማይደክሙ ዘቦች እየተጠበቁ ናቸው፡፡ ይህን በማወቅ እና በክርስቶስ ውስጥ መሆናቸውን በመገንዘብ በእግዚአብሔር ፈቃድ ታምነው ማረፍ ይችላሉ፡፡Amh2SM 406.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents