Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በአገልግሎት ውስጥ ለሸበቱ ሰዎች የተሰጠ ምክር

    ለሽማግሌ ኤስ ኤን ሃስከል የተሰጠ ማስጠንቀቂያ

    ሽማግሌው ሃስከል ሆይ፣ ማድረግ የምትችለውን ሁሉ ለማድረግ ጉጉ ስትሆን ምስክርነትህን እንድታስተላለፍ እነዚህን ብዙ አመታት የተጠበቅከው በእግዚአብሔር ታላቅ ምህረትና ፀጋ መሆኑን አስታውስ፡፡ ከአንተ በእድሜ የሚያንሱት ሊሸከሙት የሚችሉትን ሸክም በራስህ ላይ አትጫን፡፡Amh2SM 224.1

    በሕይወት ልምዶችህ ጥንቁቅ መሆን የአንተ ሀላፊነት ነው፡፡ አካላዊ፣ አእምሮአዊና መንፈሳዊ ጥንካሬህን በመጠቀም ረገድ ጠቢብ መሆን አለብህ፡፡ በርካታ በሆኑና የተለያዩ ዓይነት ልምምዶች ውስጥ ያለፍን ሰዎች የጌታን ሥራ ወደ ፊት ለማስቀጠል እሱ በእጣችን እንድንቆም እስከፈቀደ ድረስ ለእርሱ መሥራት እንድንችል ኃይሎቻችንን ጠብቀን ለማቆየት የሚቻለንን ሁሉ ማድረግ አለብን፡፡Amh2SM 224.2

    ሥራው ብዙዎች የሀሰተኛ ጽንሰ-ሀሳቦችን ማታለያ በመቀበል ፍርድን ለማመሰቃቀልና በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ለእግዚአብሔር ቅሬታ ሕዝብ በንጽህናው መሰጠት ያለበትን የእውነት መልእክት ዋጋ ቢስ ለማድረግ እየመጡ የነበሩ ጥንቆላዎችን ለማሳየት የእውነት ብርሐን በጨለማ እንዲበራ ለማድረግ የተደረጉ ጥረቶችን ሁሉ ሲቃወሙ የነበሩትን ሰዎች ያዩና በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ የብዙ ዓመታት ልምድ ያላቸውን ያረጁ እጆች፣ ሽማግሌ ሰራተኞች ይፈልጋል፡፡Amh2SM 224.3

    ከተፈተኑ የእግዚአብሔር ሠራተኞች መካከል ብዙዎቹ በኢየሱስ አንቀላፍተዋል፡፡ እስከዚህች ቀን ድረስ በሕይወት ያሉት ሰዎች የሰጡትን እርዳታ እጅግ እናደንቃለን፡፡ ለምስክርነታቸው ዋጋ እንሰጣለን፡፡ ከአንደኛ ዮሐንስ መልእክት ውስጥ የመጀመሪያውን ምዕራፍ ካነበብክ በኋላ ብዙ ድክመቶች ቢኖሩብህም አሁንም ለእርሱ መመስከር ስለምትችል እግዚአብሔርን አመስግን፡፡Amh2SM 225.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents