Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    የተፈለገው ወታደራዊ ሥልጠና

    በቢሮአችን ውስጥ ኃላፊነት ከሚሰማቸው ሰዎች መካከል ሶስቱን ሶስት ሳምንታትን በሚፈጅ ወታደራዊ ሥልጠና እንዲያገለግሉ መንግሥት ስለጠራቸው ተሰናብተናቸዋል፡፡ በማተሚያ ቤታችን ውስጥ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ሥራ የሚሠራበት ወቅት ነበር፣ ነገር ግን የመንግሥት ጥሪዎች የእኛን ምቾት ከግምት ውስጥ አያስገቡም፡፡ ለውትድርና የተቀበሉአቸው ወጣቶች ለውትድርና አገልግሎት አስፈላጊ የሆነ ልምምድና ሥልጠና ችላ ማለት እንደማይችሉ አጠንክረው ይናገራሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከውትድርና የደንብ ልብሳቸው ጋር በሥራቸው ታማኝነትን የማክበር ምልክት እንዳለባቸው በመመልከታችን ደስተኞች ነበርን፡፡ እምነት የሚጣልባቸው ወጣቶች ነበሩ፡፡Amh2SM 335.1

    እነዚህ የሄዱት በምርጫቸው ሳይሆን የአገራቸው ሕግ ስለሚጠይቅባቸው ነው፡፡ የክርስቶስ መስቀል እውነተኛ ወታደሮች ሆነው እንዲገኙ የማደፋፈሪያ ቃል ሰጠናቸው፡፡ ከእነዚህ ወጣቶች ጋር የእግዚአብሔር መላእክት አብረው እንዲሄዱ እና ከእያንዳንዱ ፈተና እንዲጠብቁአቸው ጸሎቶቻችን ይከተሉአቸዋል፡፡ (Written from Basel, Switzerland, Sept. 2, 1886).Amh2SM 335.2