Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ተአምራት ሰሪው የእግዚአብሔርን ሕግ አልቀበልም ሲል

    ሰዎች በሚሉት ነገር መታመን የለብንም፡፡ ክርስቶስ እንደገለጸው በሽተኞችን በመፈወስ ተአምራት እንደሚሰሩ ሊናገሩ ይችላሉ፡፡ ከኋላቸው ገና በሰዎች ፊት ከሰማይ እሳት እስከሚያወርድ ድረስ ተአምራት የሚሰራው ታላቁ አታላይ ቆሞ ሳለ ይህ አስደናቂ ነገር ሊሆን ይችላል ወይ? {2SM 49.3}Amh2SM 49.3

    በግምቶችም መታመን የለብንም፡፡ ሰው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በእግሩ እየረገጠ ሳለ የእግዚአብሔርን ቃል የመታዘዝ ግዴታ የለብህም፣ ቅዱስና ኃጢአት የለሽ ነህ የሚል ድምፅ ወይም መንፈስ የኢየሱስ ድምፅ አይደለም፡፡ እሱ እንዲህ ብሏል፡- «የአባቴን ትዕዛዛት ጠብቄያለሁ» (ዮሐ. 15፡10)፡፡ ዮሐንስም እንዲህ በማለት ይመሰክራል፡- «አውቄዋለሁ የሚል ትዕዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም” (1ዮሐ. 2፡ 4)፡፡ {2SM 49.4}Amh2SM 49.4

    እነዚህ ታላቅ ኃይል ያላቸው መገለጦች እና አስደናቂ ግምቶች ዓለምን በሙሉ ለማሳት እና በውሸት እንዲያምኑ ለማድረግ ጠንካራ በሆነ ማታለያ ሰዎችን በማረከው ተአምራት ሰሪ መንፈስ ተጽእኖ በተሰጡት ላይ ተመስርቶ ካልሆነ በስተቀር እንዴት መልስ ሊሰጥባቸው ይችላል? ወንዶችና ሴቶች ታላቅ መንፈሳዊ ኃይል እንዳላቸው እየተናገሩ የእግዚአብሔርን ሕግ ችላ ሲሉ፣ በእነርሱ ባለመታዘዝ ሌሎችን ወደ ስህተት ስለሚመሩና ሰይጣን እነርሱን በሥራው ውስጥ የተዋጣላቸው ወኪሎቹ አድርጎ ሊጠቀምባቸው ስለሚችል ደስ ይለዋል፡፡ --The Signs of the Times, July 21, 1887. {2SM 49.5}Amh2SM 49.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents