Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እርሱ በኢየሱስ አንቀላፍቷል

    በባልና አባት ሞት ምክንያት የተሰጠ ማጽናኛ

    ውድ በስቃይ ላይ ያለሽ እህቴ ሆይ፣

    በስቃይሽ እኔም ተሰቃይቻለሁ፡፡ ምንም እንኳን ባለቤትሽን እንደገና በዚህ ሕይወት ለመገናኘት ባልጠብቅም መሞቱን በመስማቴና ከዚህ ችግር የተነሳ ለቤተሰብ የመጠንቀቅ ከባድ ኃላፊነት በላይሽ በመውደቁ አዝኛለሁ፡፡ ሀዘንሽን እንደ ሀዘናችን በመቁጠር ለአንቺም ለልጆችሽም እንጸልያለን፡፡ ባለቤትሽ በኢየሱስ አንቀላፍቷል፡፡ “ከሰማይም፡- ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብጹአን ናቸው፡፡ መንፈስ፡- አዎን ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፣ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል ብለህ ጻፍ የሚል ድምጽ ሰማሁ” (ራዕይ 14፡ 13)፡፡ Amh2SM 264.3

    ክርስቶስ ራስ የሆነለት አካል አባላት በመሆን በተግባርና በእውነት የሚያምኑትን ሁሉ አባት ይወዳል፡፡ በክርስቶስ ጥላ ሥር መቀመጥ አለብሽ፣ እንዲህ ስታደርጊ የእርሱን ሰላም ትገነዘቢያለሽ፡፡ ስለ ክርስቶስ አስቢ፡፡ ተስፋዎቹን በማመን ወደ እርሱ በእምነት ተመልከቺ፡፡ አእምሮሽ በኢየሱስ ይታመን፡፡ እርሱ መቆያሽ ይሆንሻል፡፡ በእርሱ ተደገፊ፣ በእርሱ እረፊ፡፡ ከሚገባ በላይ አትዘኚ፣ ቻዪ፤ ከባድ ሸክም በላይሽ አርፏል፡፡ በፍጹም በማይጥሉ በእርሱ ክንዶች ታመኚ፡፡ Amh2SM 265.1

    እኔም ባለቤቴን ስላጣሁ ሀዘንሽ ምን እንደሆነ ከልምድ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ወደ ኢየሱስ በመመልከት ማበረታቻ ታገኚያለሽ፡፡ የጌታ በረከት በየቀኑ ይሁንልሽ፡፡ ውድ እህቴ ሆይ፣ ጌታ ይባርክሽ፣ በሕይወትም ያቆይሽ፡፡ Amh2SM 265.2

    አሁን ለማየት በጣም ስለጨለመ ደህና እደሪ እልሻለሁ፡፡ ለልጆችሽ ብለሽ በተቻለሽ መጠን ደስተኛ ሁኚ፡፡--Letter 167, 1905.Amh2SM 265.3

    ውድ ልጆች ሆይ፣

    ለእናንተም ጥቂት መስመሮችን መጻፍ አለብኝ፡፡ ምኞታችን ወደ ቤታችሁ ገብተን አብረናችሁ ብናለቅስና ከእናንተ ጋር አብረን ተንበርክከን መጸለይ ብንችል ነበር፡፡ እያንዳንዳችሁ ጌታን ትሹታላችሁን? ታገለግሉታላችሁን? የእናታችሁን ልብ የሚያሳዝን አንድም ነገር ባታደርጉ ታላቅ በረከት ትሆኑላታላችሁ፡፡ ልባችሁን ከሰጣችሁ ጌታ ኢየሱስ ይቀበላችኋል፡፡ እናታችሁን ከእያንዳንዱ ጭንቀትና ሸክም ለማሳረፍ ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ፡፡ Amh2SM 265.4

    ጌታ አባት ለሌላቸው አባት ለመሆን ቃል ገብቷል፡፡ ልባችሁን ለእርሱ ከሰጣችሁ የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንድትሆኑ ኃይል ይሰጣችኋል፡፡ ታላላቅ ልጆች አቅማቸው የሚፈቅደውን ያህል ብዙ ሸክሞች በመሸከም፣ ታናናሽ ልጆችን በርህራሄ በመያዝ፣ ትክክለኛ የሆነውን ነገር እንዲያደርጉ በማስተማር እና እናታቸውን ባለማሳዘን ቢያሳርፏት ጌታ አብዝቶ ይባርካቸዋል፡፡ Amh2SM 265.5

    ልባችሁን አፍቃሪ ለሆነው አዳኝ በመስጠት በእርሱ እይታ አስደሳች የሆኑትን ነገሮች ብቻ አድርጉ፡፡ እናታችሁን ለማሳዘን ምንም ነገር አታድርጉ፡፡ ጌታ እንደሚወዳችሁና እያንዳንዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል መሆን እንደምትችሉ አስታውሱ፡፡ በምድር ላይ ታማኝ ከሆናችሁ፣ ጌታ በሰማይ ደመና ሲመጣ አባታችሁን ትገናኙትና አንድ ቤተሰብ ትሆናላችሁ፡፡ Amh2SM 265.6

    እወዳችኋለሁ፡፡--Letter 165, 1905.Amh2SM 266.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents