Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የመንፈሳዊ ማሽቆልቆል አደጋ

    ራሳቸውን ከዓለማዊ ሕብረት ጋር የሚያገናኙ ክርስቲያኖች ራሳቸውን እየጎዱ ሲሆን ሌሎችንም ወደ ስህተት እየመሩ ናቸው፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች በእግዚአብሔር የማያምኑ ሰዎችን ለጓደኝነት አይመርጡም፣ ከጉዳትም ይድናሉ፡፡ በእነዚህ ሕብረቶች በዓለማዊ መርሆዎችና ልምዶች ተጽእኖ ሥር እንዲሆኑ ይደረጋሉ፣ ከሚፈጠረው ግንኙነትና ልምድ የተነሳ አእምሮ ከዓለማውያን መስፈርት ጋር የበለጠውን እየተስማማ ይሄዳል፡፡ ለእግዚአብሔር ያላቸው ፍቅር እየቀዘቀዘ ይሄዳል፣ ከእርሱ ጋር ለመገናኘትም ፍላጎት አይኖራቸውም፡፡ በመንፈሳዊነት እውሮች ይሆናሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ በሚተላለፉ እና እግዚአብሔርን በሚፈሩና ትዕዛዛቱን በሚጠብቁ ሰዎች መካከል ልዩነት መኖሩን ማየት አይችሉም፡፡ ክፉን መልካም፣ መልካሙን ደግሞ ክፉ ብለው ይጠራሉ፡፡ የዘላለማዊ እውነታዎች ብሩህነት እየደበዘዘ ይሄዳል፡፡ እውነት ኃይለኛ በሆነ ሁኔታ ሊቀርብላቸው ይችላል፣ ነገር ግን የሕይወትን እንጀራ ለመመገብ አይራቡም ወይም የድነት ውኃን ለመጠጣት አይጠሙም፡፡ ውኃ መያዝ ከማይችሉ ጉድጓዶች እየጠጡ ናቸው፡፡ ከዓለም ጋር ሕብረት ስንፈጥር የኢየሱስንና የእውነትን ክቡርነት ማየት እስከማንችል ድረስ የእነርሱን መንፈስ መውሰድ፣ እነርሱ ለነገሮች ባላቸው አመለካከት መቀረጽ ቀላል ነው፡፡ የዓለም መንፈስ በልባችን ባደረ መጠን ሕይወታችንን ይቆጣጠራል፡፡ {2SM 128.4}Amh2SM 128.4

    ሰዎች በእግዚአብሔር ቃልና መንፈስ ቁጥጥር ሥር በማይሆኑበት ጊዜ የሰይጣን ምርኮኞች ስለሆኑ እስከ ምን ያህል ደረጃ ወደ ኃጢአት እንደሚመራቸው አናውቅም፡፡ አበው ያዕቆብ ክፉ በማድረግ የሚደሰቱ ሰዎችን ተመለከተ፡፡ ከእነርሱ ጋር አንድነት መፍጠር የሚያስከትለውን ውጤት ስለተመለከተ በመንፈስ እንዲህ በማለት ተናገረ፣ «በምክራቸው፥ ነፍሴ፥ አትግባ፤ ከጉባኤአቸውም ጋር፥ ክብሬ፥ አትተባበር፤ በቍጣቸው ሰውን ገድለዋልና፥ በገዛ ፈቃዳቸውም በሬን አስነክሰዋልና» (ዘፍ. 49፡6)፡፡ እያንዳንዱን ነፍስ እነዚህን ከሚመስሉ ግንኙነቶች እንዲጠበቁ ለማስጠንቀቅ የአደጋ ምልክትን ያነሳል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ማስጠንቀቂያውን እንደሚከተለው ያስተጋባል፡- «ፍሬ ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ» (ኤፌ. 5፡11)፡፡ «አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል» (1ቆሮ. 15፡33)፡፡ {2SM 129.1}Amh2SM 129.1

    ነፍስ በእሥራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ከመታመን ይልቅ በዓለማዊ ፖሊሲዎችና በሰው ፈጠራዎች ሲታመን ተታሏል፡፡ ሰው ከኢየሱስ ክርስቶስ የተሻለ መሪ ማግኘት ይችላለን? በጥርጣሬና በፈተና ጊዜ ከኢየሱስ ክርስቶስ የተሻለ መካሪ፣ በአደጋ ጊዜ የተሻለ መከላከያ ማግኘት ይችላልን? ለሰብዓዊ ጥበብ በማለት የእግዚአብሔርን ጥበብ ወደ ጎን መተው ነፍስን የሚያጠፋ መታለል ነው፡፡ {2SM 129.2}Amh2SM 129.2

    ሰው የእግዚአብሔርን ጸጋ ተጽዕኖ አልቀበል ሲል ምን እንደሚያደርግ ማየት ከፈለግክ በቁጣ የተሞላ ሕዝብ በአይሁድ ካህናትና ሽማግሌዎች እየተመራ የእግዚአብሔርን ልጅ ሕይወት ለመውሰድ ሲጨቃጨቅ የነበረበትን ሁኔታ ተመልከት፡፡ ስቃይ እየደረሰበት የነበረውን መለኮት ከበርባን ጎን ቆሞ ጲላጦስ ከሁለቱ የትኛውን ልልቀቅላችሁ ብሎ ሲጠይቅ ተመልከቱ፡፡ ስሜታዊነት በተጠናወታቸውና ሰይጣን ባነሳሳቸው በመቶዎች በሚቆጠሩ ድምጾች የታጀበ ሸካራ ጩኸት «ይህን አስወግድ፥ በርባንንም ፍታልን» (ሉቃስ 23፡18)! የሚል ነበር፡፡ ጲላጦስ ኢየሱስን ምን ላድርግ ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ «ስቀለው፣ ስቀለው» ብለው ጮኹ (ሉቃስ 23፡21)! {2SM 129.3}Amh2SM 129.3

    በዚያን ጊዜ የነበረው ሰብዓዊ ተፈጥሮ አሁንም ያለ ሰብዓዊ ተፈጥሮ ነው፡፡ ሰብአዊ ተፈጥሮን ማዳንና ከፍ ማድረግ ይችል የነበረው መለኮታዊ ፈውስ በሚናቅበት ጊዜ አሁንም በሰዎች ልብ ውስጥ ያው መንፈስ ስለሚኖር በእነርሱ ምሪት ልንታመን እና ለኢየሱስ ያለንን ታማኝነት አጽንተን ልንጠብቅ አንችልም፡፡ {2SM 130.1}Amh2SM 130.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents