Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    በእስፖርት ውስጥ ያለ አደጋ

    ኳስን የመጫወትን ቀለል ያለ እንቅስቀሴ አልኮንንም፤ ነገር ግን ይህ ቀለል ያለ እንቅስቃሴ እንኳን ከልክ ያለፈ ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህ መዝናኛዎች የሚጀምሩበትን ወቅት ተከትለው የሚመጡ እርግጠኛ የሆኑ ውጤቶችን በመፍራት ሁል ጊዜ ወደ ኋላ አፈገፍጋለሁ፡፡ ያለ ክርስቶስ እየጠፉ ላሉት ነፍሳት የእውነትን ብርሃን ለማድረስ መዋል ያለበትን ገንዘብ ለሌላ ተግባር ወጪ ወደ ማድረግ ይመራል፡፡ ደረጃ በደረጃ የራስን ክብር ወደ መፈለግ ከመምራቱም በላይ በእነዚህ ጨዋታዎች ውስጥ ደስታን ለማግኘት ወደ ማስተማር የሚመሩት መዝናኛዎችና ራስን ለማስደሰት የሚወጡ ወጪዎች ክርስትያናዊ ባሕርይን ለመፈጸም ምቹ ያልሆነ ፍቅርና ፍላጎት ይፈጥራሉ፡፡Amh2SM 322.1

    የእስፖርት እንቅስቃሴዎች በኮሌጅ ውስጥ እየተካሄዱ ያሉበት ሁኔታ የሰማይን ጠባይ አያሳይም፡፡ የአእምሮ ችሎታን አያጠነክርም፡፡ ባሕርይን ሞርዶ አያስተካክልም፡፡ ዓለም ወደሚከተላቸው ልማዶች፣ ወጎች እና ልምምዶች የሚመሩ መስመሮች ስላሉት ተዋንያኖቹ በዚህ ነገር በመጠመድና ፍቅር ውስጥ በመግባት በሰማይ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ተብለው ተጠርተዋል፡፡ እንደ ተማሪዎች አእምሮአቸው የተሻለ ነገርን ለማከናወን በተሻለ ሁኔታ ብቁ ከመሆን ይልቅ በእነዚህ ጨዋታዎች ውስጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ አእምሮአቸውን ከጥናታቸው የሚያደናቅፉ ሀሳቦችን እየሞላ ነው፡፡ Amh2SM 322.2