Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 15—ተግሳጽ ይሰማል

    [Appeared In Notebook Leaflets, Methods, NO. 1.]

    እየኖርን ያለነው በዚህ ምድር ታሪክ የመጨረሻ ቀናት ስለሆነ የክህደትና እውነትን የመካድ መስመሮችን በተመለከተ በምንም ነገር ላንደነቅ እንችላለን፡፡ አሁን አለማመን ሰዎች ለጥፋታቸው የሚሰሩት ዕደ-ጥበብ ሆኗል፡፡ ሕይወታቸው የሚናገሯቸውን ቃላት በሚቃወሙ በመድረክ ላይ ሰባኪዎች ውስጥ ማስመሰል የመታየት የማያቋርጥ አደጋ አለ፤ ነገር ግን ዘመን እስካለ ድረስ የማስጠንቀቂያና የተግሳጽ ድምፅ ይሰማል፤ በፍጹም መግባት በሌለባቸው ንግዶች ውስጥ በመግባታቸው ጥፋተኞች የሆኑ ሰዎች ጌታ በሾማቸው ወኪሎች አማካይነት ተግሳጽ ወይም ምክር ሲሰጣቸው መልእክቱን አልቀበል በማለት ለመታረም እምቢ ይላሉ፡፡ እግዚአብሔር የማገናዘብ ችሎታቸውን እስኪወስድባቸውና ልባቸው ሊነካ የማይችል እስኪሆን ድረስ ፈርዖንና ናቡካደናፆር እንዳደረጉት ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ይመጣላቸዋል፤ ነገር ግን ለመስማት ካልመረጡ ለራሳቸው ጥፋት እግዚአብሔር ተጠያቂ ያደርጋቸዋል፡፡ {2SM 147.1}Amh2SM 147.1

    የጌታን መንገድ እንዲያዘጋጅ እግዚአብሔር ለራሱ መጥምቁ ዮሐንስን አስነሳ፡፡ ኃጢአትን በመገሰጽና በማውገዝ ፍንክች የማይልን መልእክት ለዓለም ማስተላለፍ ነበረበት፡፡ ሉቃስ የእሱን ተልእኮና ሥራ ሲያስተዋውቅ እንዲህ ይላል፣ «እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል» (ሉቃስ 1፡17)፡፡ {2SM 147.2}Amh2SM 147.2

    ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ለዮሐንስ ጥምቀት መጡና እነርሱን ሲናገራቸው እንዲህ አላቸው፣ «ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ? እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤ በልባችሁም፡- አብርሃም አባት አለን እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና። ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል፡፡ አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል። እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤ መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል» (ማቴ. 3፡7-12)፡፡ {2SM 148.1}Amh2SM 148.1

    የዮሐንስ ድምፅ እንደ መለከት ከፍ ብሎ ነበር፡፡ የእርሱ ተልዕኮ የነበረው «ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር” (ኢሳ. 58፡1) ነበር፡፡ ምንም ሰብዓዊ የትምህርት እድል አላገኘም ነበር፡፡ እግዚአብሔርና ተፈጥሮ መምህራኑ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ለክርስቶስ መንገድ ለማዘጋጀት እንደ ጥንቶቹ ነቢያት የተበላሸን ሕዝብ ወደ ንስሃ በመጥራት ድምጹን ለማሰማት ደፋር የሆነ ሰው አስፈልጎ ነበር፡፡ {2SM 148.2}Amh2SM 148.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents