Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል 1—አክራሪነትና አሳሳች ትምህርቶች

    መግቢያ

    ሰይጣን፣ ዘንዶው፣ «የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በሚጠብቁትና የኢየሱስ ምስክር ባላቸው» ላይ ያለመታከት ጦርነት ስለሚያካሄድ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች በትንቢት ውስጥ የታዩት በጦርነቱ መነሻ ቦታ ላይ ነው፡፡ ታላቁ ጠላት ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶችን ወደ ስህተት በመምራትና ግራ በማጋባት ከተሳካለት የእግዚአብሔርን ዓላማዎች እንደሚያሰናክል ያውቃል፡፡ ጥቃቶቹ በአብዛኛው የተንኮል ባሕርይ ያለባቸው እና እውነተኛ ቅናት ያላቸው ወንዶችና ሴቶች ሀሰትን እንዲያምኑ ወደ ፅንፍ ወደመምራት የሚያዘነብሉ ናቸው፡፡ Amh2SM 12.1

    የዳግም ምጻት እንቅስቃሴ በሚያስገርም ሁኔታ ከአክራሪነትና ከፅንፈኝነት ነጻ ቢሆንም ከጅምሩ ጀምሮ አክራሪነት የሚያመጣቸውን ሁኔታዎች ተጋፍጧል፡፡ ከኤለን ኋይት የመጀመሪያዎቹ ተግባሮቿ አንዱ አክራሪነትን በእግዚአብሔር ቃል ለመጋፈጥ ወደ መስክ መሄድ ነበር፡፡ በሰባ አመት አገልግሎቷ ጊዜ ሁሉ አክራሪነትን ወይም አሳሳች ትምህርቶችን በአንድ ወይም በሌላ መልክ እንድትጋፈጥ በተደጋጋሚ ተጠርታለች፡፡ አክራሪነት እንደሚደገም የሚገልጹ በርካታ ማስጠንቀቂያዎች የተሰጡት ቤተ ክርስቲያን ሊያገኟት ያሉትን አደጋዎች እንድትረዳ ለማንቃት ነው፤ የተለያዩ ዓይነት አክራሪነቶችና ስሜታዊ ኃይማኖቶች እንደሚከሰቱ የጌታ መልእክተኛ የሰጠቻቸው ምክሮች አሁን መንጋውን ከአደጋ በመጠበቅ ረገድ ትልቅ ጥቅም አላቸው፡፡Amh2SM 12.2

    በዚህ ክፍል ውስጥ የተካተተው መመሪያ፣ በቀደምት የኤለን ኋይት መጻሕፍት ውስጥ የተሰጡ ማስጠንቀቂያዎችን በማጠናከር፣ በአብዛኛው የተሰባሰበው በ1933 ዓ.ም በአንድ አጥቢያ ኮንፍራንስ የተከሰተን አሳሳቢ ሁኔታ ለመከላከል ነበር፡፡ ይህ ጽሁፍ ተባዝቶ በመቅረቡ እጅግ ከመደነቁም ባሻገር ቤተ ክርስቲያንን በደንብ አገልግሏል፡፡ የኤለን ጂ ኋይት ጽሁፎች የበላይ ጠባቂዎች ይህንን ጠቃሚ የሆነ ምክር በቋሚ መልክ የማቅረብ ዕድልን በደስታ ይቀበሉታል፡፡Amh2SM 12.3

    ይህ ክፍል የሚደመደመው ሀሰተኛ የሆነ ተዓምራት ሰሪ ኃይልን በሚያሳዩ መገለጦችና እውነትን ለመፈተን ለሚቀርቡ ነገሮች የተአምራቶችን አንጻራዊ ጥቅም በሚያሳዩ የተለያዩ ዓረፍተ ነገሮች ነው፡፡ ምክሮቹ ለአሁን የተለየ ዋጋ ያላቸው ሲሆን ወደ ምድራችን የመጨረሻ ቀናት ስንቃረብ፣ ሰይጣን የተለያዩ ስልቶችንና ዘዴዎችን በመጠቀም የተመረጡትን እንኳን ለማሳሳት ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ፣ የበለጠውን ጠቃሚ ይሆናሉ፡፡Amh2SM 12.4

    የኋይት የቦርድ አባላት

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents