ርካሽ፣ ተራ፣ ምድራዊ ጉዳዮች
የዚህ ዓይነት ልምምዶች በጣም ተራ መሆን ጀምረዋል፡፡ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ብዙዎች በዚህ የማታለያ ዓይነት ሥር ናቸው፡፡…ከተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አባላት ውስጥ ለአንዳንድ ለሚንቀጠቀጥ ምስኪን ነፍስ «አንተ ኩራተኛ ነህ»፤ ለሌላኛው ደግሞ «አንተ የማታምን ነህ፤ ትጠፋለህ” የሚሉ መልእክቶች ይሰጣሉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የማጽናኛና የማበረታቻ ቃላት እንድናገር ጌታ ብርሃን ሰጠኝ፡፡ ቢቀበሉም ባይቀበሉም ለእነዚያ ለተታለሉት ምስክርነቴን አስተላለፍኩ፡፡ ራዕዮቻቸው የሰይጣን ሥራ ነበሩ፡፡ የተገለጡላቸው ነገሮች ብዙ ጊዜ ተራ፣ ምድራዊ ነገሮች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ በሚቀጥለው ቀን ጧት ቁርስ ማን ያግኝ፣ ራት ማን ያዘጋጅ፣ ማን ሳህኖችን ይጠብ የሚሉ ዓይነቶች ነበሩ፡፡ ከነዚህ ከማይረቡ ነገሮች ጋር ተቀላቅለው በመጽሐፍ ቅዱስና በምስክሮች ውስጥ ያገኙአቸው ቅዱስ እውነቶች ነበሩ፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ሰዎች እንዲጠሉና የራዕይ ተፈጥሮ ያለውን ነገር ሁሉ እንዲዘልፉ ለማድረግ የሰይጣን እጅ አለበት፡፡ ከዚህ የተነሳ እውነትና ውሸት በአንድነት ተቀባይነት ያጣሉ፡፡ በማታለያው ውስጥ የተሰማሩት እንኳን ሲሰለቻቸው ሁሉንም ራዕዮች ወደ መጠራጠር ያዘነብላሉ፡፡ {2SM 77.2}Amh2SM 77.2
ከእነዚህ ከተታለሉት ጋር እጅግ ከበድ ያለ ስብሰባ ከተደረገ በኋላ በተቻላቸው መጠን የሲስተር ኋይትን በሚመስሉ አመለካከቶች ውስጥ ራሳቸውን መጣላቸውን ተናዘዙ፡፡ ነገር ግን እነርሱ የተነበዩአቸው ብዙ ነገሮች እንደነገሩት ተፈጸሙ፡፡ {2SM 77.3}Amh2SM 77.3
ራዕዮቹ ሁሉ ውሸት ከሆኑ ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ተጠይቄ ነበር፡፡ በእነዚህ አታላይ እንቅስቃሴዎች አማካይነት ትክክለኛ የሆነውን ሥራ ውጤት የለሽ ለማድረግ እውነትን ከውሸት ጋር መቀላቀል የሰይጣን አላማው እንደሆነ ነገርኳቸው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ራዕዮቻቸው ሁሉ ተቋረጡ፡፡ ራዕዮች ለነበሩአቸውና እነርሱን ያበረታቱ ለነበሩት ምን ሆነ? ዛሬ ተጠራጣሪዎች ሆነው የሚኖሩ አብዛኞቹ በቤተ ክርስቲያን ስጦታዎች እምነት የላቸውም፣ በእውነት ላይ እምነት የላቸውም፣ ሙሉ በሙሉ ኃይማኖት የላቸውም፡፡ እንደዚህ ያለ ነገር የውሸት ራዕዮች ትክክለኛ ውጤት እንደሆነ እንዳይ ተደርጌ ነበር፡፡ {2SM 77.4}Amh2SM 77.4
የሴት ልጅህ መገለጦች ተመሳሳይ የሆኑ ማታለያዎች ናቸው፡፡ በእሷ ውስጥ ያሉትን እነዚህን ነገሮች ማደፋፈርህ፣ የሆነ ነገር መታለያውን ካላቋረጠው በስተቀር፣ የእሷንና የሌሎችን መጥፋት እርግጠኛ ያደርጋል፡፡ እነዚህን የውሸት ራዕዮችና ትርጉም የለሽ ሕልሞች አስደናቂ የእግዚአብሔር ብርሃን ብለህ ጠርተሃል፣ ነገር ግን ገለባን ስንዴ ብሎ እንደመጥራት ነው፡፡ ይህ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ በቤተሰብህ ላይ ወሳኝ ተጽእኖ ይኖረዋል፡፡ ሴት ልጅህ የተናገረቻቸውን ቃላት በእግዚአብሔር መንፈስ ተጽእኖ ሥር ሆና የተናገረቻቸው እንደሆኑ አድርገህ ስትቆጥር ለአንተም ተመሳሳይ ይሆናል፡፡ ጠንካራ በሆነ የሰይጣን ማታለያ ሥር ነህ፡፡ ለእነርሱ ዋጋ እንደምትሰጥ ትናገራለህ፣ ከዚህ የተነሳ ታዋቂ በሆነ ከእግዚአብሔር በሚመጣ መልእክት ላይ ያለህ መታመን ይነቀላል፡፡ አንተ እንደምታምን በሚያምኑ ሁሉ ላይ ተመሳሳይ የሆነ ነገር ይፈጸማል፡፡ ሰይጣን ከእውነት ለማሳት ሀሰት በሆነ ነገር ላይ ያለማቋረጥ ግፊት እያደረገ ያለበት ምክንያቱ ይህ ነው፡፡ {2SM 78.1}Amh2SM 78.1
የሰይጣን የመጨረሻው ማታለያ የእግዚአብሔር መንፈስ ምስክርነትን ዋጋ ቢስ ማድረግ ነው፡፡ «ራዕይ ባይኖር ሕዝብ መረን ይሆናል» (ምሳሌ 29፡18)፡፡ የእግዚአብሔር ቅሬታ ሕዝብ በእውነተኛው ምስክርነት ላይ ያላቸውን መታመን ለማናጋት ሰይጣን በብልጠት፣ በተለያዩ መንገዶች በተለያዩ ወኪሎች አማካይነት ይሰራል፡፡ ወደ ስህተት ለመምራት የሀሰት ራዕዮችን ያመጣና ውሸትን ከእውነት ጋር ይቀላቅላል፣ በዚህ ሁኔታ ሰዎች ማንኛውንም ራዕዮች የሚል ስም ያለውን ነገር የወግ አጥባቂነት ዝሪያ አድርገው በመመልከት እንዲጠሉት ያደርጋል፤ ነገር ግን ታማኝ የሆኑ ነፍሳት እውነትንና ውሸትን በማወዳደር ልዩነቱን እንዲያውቁ ይደረጋሉ፡፡... {2SM 78.2}Amh2SM 78.2