Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ለአእምሮ አጋዥ የሆኑ ሳይንሶች

    በአብዛኛው ተጠራጣሪነትና አረመኔነት ሳይንሳዊ ልብስ ለብሰው በሚታዩበት በእነዚህ ቀናት በሁሉም በኩል ጥበቃ ያስፈልገናል፡፡ በእነዚህ መንገዶች ታላቁ ጠላታችን በሺሆች የሚቆጠሩትን በማሳሳት እንደ ራሱ ፈቃድ ወደ ምርኮ እየመራቸው ነው፡፡ ለሰው አእምሮ ከሚመቹ ሳይንሶች የሚያገኘው ጥቅም ታላቅ ነው፡፡ በዚህ ቦታ በእባብ ተመስሎ የእግዚአብሔርን ሥራ ለማበላሸት ሳይታይ ተስቦ ይገባል፡፡Amh2SM 351.3

    ይህ ሰይጣን በሳይንሶች አማካይነት የመግባት ሥራ በደንብ የተቀየሰ ዘዴ ነው፡፡ በጭንቅላት መጠንና ቅርጽ ጥናት፣ በሥነ-ልቦና ጥናት እና አእምሮን በሰመመን ውስጥ በማስገባት ትምህርት አማካይነት በዚህ ትውልድ ወዳለው ሕዝብ በቀጥታ በመምጣት የምህረት በር በሚዘጋበት ጊዜ አቅራቢያ ጥረቶቹን አጉልቶ በሚያሳይ ኃይል ይሰራል፡፡ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎች አእምሮዎች ተመርዘው ወደ አረመኔነት ተመርተዋል፡፡ የአንድ ሰው አእምሮ እንደዚህ በሚያስደንቅ ሁኔታ በሌላ አእምሮ ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር የሚታመን ሲሆን ጥረት እያደረገ ያለው ሰይጣን በእያንዳንዱ አጋጣሚ ራሱን አሹልኮ ለማስገባት በግራና በቀኝ በኩል ይሰራል፡፡ ለእነዚህ ሰይንሶች ራሳቸውን የሰጡ ሰዎች የሚሰጡአቸው ታላላቅና ጥሩ ሥራዎች በእነዚህ ሳይንሶች አማካይነት የተሰሩ ስለሆኑ ወደ ሰማይ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እየተናገሩ ሳለ እንዴት ያለ የክፉ ኃይል እየተንከባከቡ እንደሆነ የሚያውቁት ትንሽ ነው፤ ነገር ግን ይህ በምልክቶችና በውሸት ተአምራቶች ሁሉ በኃጢአት መታለል ሁሉ የሚሰራ ኃይል ነው፡፡ ውድ አንባቢ ሆይ፣ በክርስቶስና በሰይጣን መካከል ያለው ጦርነት ገና ስላልተፈጸመ የእነዚህን ሰይንሶች ተጽእኖ ልብ በል፡፡Amh2SM 351.4

    ጸሎትን ችላ ማለት ሰዎች በራሳቸው ብርታት እንዲደገፉ ከማድረጉም በላይ ለፈተና በር ይከፍታል፡፡ በብዙ አጋጣሚዎች ሀሳብ በሳይንሳዊ ምርምር በመጠመዱ በራሳቸው ኃይሎች ንቃት ተታለዋል፡፡ እነዚህ የሰውን አእምሮ የሚያሳዩ ሳይንሶች እጅግ በጣም ከፍ ያለ ቦታ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነዚህ ሳይንሶች በቦታቸው ጥሩ ናቸው፤ ነገር ግን ነፍሳትን ለማታለል እና ለማጥፋት ሰይጣን እንደ ኃይለኛ ወኪሎቹ አድርጎ ይዞአቸዋል፡፡ የሰይጣን ሥራዎች ከሰማይ እንደሆኑ ተደርገው ተቀባይነት ስላገኙ ለእርሱ ገጣሚ የሆነ አምልኮን ይቀበላል፡፡ ከጭንቅላት ትምህርትና ከእንስሳት መሳሳብ ብዙ ጥቅም ማግኘት የነበረበት ዓለም በፍጹም የአሁኑን ያህል ተበላሽቶ አያውቅም፡፡ በእነዚህ ሳይንሶች አማካይነት መልካም ተግባር ተበላሽቷል፣ መናፍስትን የመጥራት መሰረቶችም ተጥለዋል፡፡ The Signs of the Times, Nov. 6, 1884.Amh2SM 352.1