Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሰማይ ማረጋገጫ (ፊርማ) የለውም

    በዚህች የምድር ታሪክ መዝጊያ አቅራቢያ በመኖር ላይ እንገኛለን፤ አስደናቂ ክስተቶች ለመታየት እየተዘጋጁ ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን እና መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ እንደ እምነታችን መሠረት አድርገህ ስታቀርብ ሙሉ በሙሉ ከአንተ ጋር እስማማለሁ፡፡ ሰይጣን ብልሃተኛ ጠላት ስለሆነ ብዙዎች ባልጠበቁት ቦታ ይሰራል፡፡ ለአንተ መልእክት አለኝ፡፡ የአና ፊሊፕስን ራዕዮች የማቅረብን፣ በሕዝብ ፊት የማንበብን እና ጌታ ወዶ ከሰጠኝ ምስክርነቶች ጋር አንድ የማድረግን ሸክም እንድትወስድ ጌታ እንደሰጠህ ትገምታለህን? አይደለም፣ ጌታ ይህን ሸክም በአንተ ላይ አላስቀመጠም፡፡ ይህን ሥራ እንድትሰራው አልሰጠህም፡፡---ሥራውን አዎንታዊ የሆነ ማስረጃ ከሌላቸው ምርቶች ጋር በመቀላቀል ከሕይወትና ከክብር ጌታ ነው በማለት አታቅልለው፡፡. . .{2SM 85.1}Amh2SM 85.2

    ውድ ወንድሜ፣ በአሁኑ ጊዜ ለሥራው አስጊ የሆኑ አደጋዎችን በተመለከተ አንዳንድ ነገሮችን በፊትህ አቀርባለሁ፡፡ የአና ፊሊፕስ ሥራ የሰማይ ፊርማ የለውም፡፡ ስለምን እንደምናገር አውቃለሁ፡፡ ይህ ሥራ በእንጭጭነት ደረጃ እያለ በነበረን የመጀመሪያው ልምምድ ውስጥ ተመሳሳይ የሆኑ መገለጦችን መጋፈጥ ነበረብን፡፡ የዚህ ዓይነት ብዙ ራዕዮች ተሰጥተው ስለነበር ይህን ነገር በመጋፈጥና ቦታ ባለመስጠት ላይ እጅግ ደስ የማይል ሥራ ነበረብን፡፡ በእነዚህ ራዕዮች የተነገሩ አንዳንድ ነገሮች ስለተፈጸሙ አንዳንዶች ትክክለኛ እንደሆነ አድርገው እንዲቀበሉት መራቸው፡፡. . . {2SM 86.1}Amh2SM 86.1

    አና ፊሊፕስ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጣቸውን ምስክርነቶች እየተከታተለች ፍሬ ነገሩን እንድትደግም እግዚአብሔር አልጠራትም፡፡ ነገር ግን የእሷ ሥራ ይህ ነበር፡፡ በዚህ ሥራ የመጀመሪያ ልምምድ ውስጥ ግለሰቦች ልክ ተመሳሳይ የሆነ ነገር አድርገው ነበር፡፡ እነዚህን የውሸት ራዕዮች በተለያየ መልካቸው መጋፈጥ ነበረብን፡፡ {2SM 86.2}Amh2SM 86.2

    ወንድሜ ሆይ፣ እነዚህን ግንኙነቶች ወስደህ እግዚአብሔር ለሚስስ ኋይት ከሰጣቸው ምስክርነቶች ጋር በመሸመን በሕዝብ ፊት ያቀረብከው እንዴት ነው? እነዚህ ነገሮች ከእግዚአብሔር ለመሆናቸው ማስረጃ ያገኘኸው ከየት ነው? እንዴት እንደምትሰማ፣ እንዴት እንደምትቀበል፣ እንዴት እንደምታምን በጣም መጠንቀቅ አልቻልክም፡፡ ትንቢት ስለመናገር ስጦታ እንዴት እንደምትናገርና ይህን ጉዳይ በተመለከተ እኔ ይህን ወይም ያን ብያለሁ ብለህ ስለመናገር በጣም ልትጠነቀቅ አልቻክልም፡፡ እነዚህ ዓይነት አረፍተ ነገሮች ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች እንዲህ ያለ ብርሃን ሳይቀበሉ ከእግዚአብሔር በመጡ ራዕዮች ውስጥ የተለየ ብርሃን እንዳላቸው እንዲገምቱ እንደሚያደፋፍራቸው በደንብ አውቃለሁ፡፡ ይህ ከሰይጣን የማታለያ ድንቅ የፈጠራ ሥራዎች መካከል አንዱ እንደሚሆን አሳይቶኛል፡፡ ለሥራው እየሰጠህ ያለው ቅርጽ የእግዚአብሔርን ሥራ ከሌላ የአክራሪነት ችግር ለማዳን ውድ ጊዜንና ለማስተካከል አድካሚ የሆነ ልፋትን የሚጠይቅ ነው፡፡. . . {2SM 86.3}Amh2SM 86.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents