Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ተአምራቶች መፈተኛ አይደሉም

    ዛሬ በእግዚአብሔር ሥራ ላይ የሚሰማሩ ሰዎች ጳውሎስ በሥራው ውስጥ የገጠሙትን ዓይነት ፈተናዎች ይጋፈጣሉ፡፡ ተመሳሳይ በሆነ የኩራትና የማታለያ ሥራው ሰይጣን የተለወጡ ሰዎችን ከእምነት ለማሳት ይፈልጋል፡፡ ልናስተናግዳቸው የማይገቡ ንድፈ ሀሳቦች ይመጣሉ፡፡ ሰይጣን ብልህ ሰራተኛ ስለሆነ አእምሮን ለማጨለምና ግራ ለማጋባት እና የድነት አስተምህሮዎችን ከሥራቸው ለመንቀል ብልጠት ያለባቸውን የስህተት ሀሳቦች ያመጣል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚነበበው አድርገው የማይቀበሉ ሰዎች በእሱ ወጥመድ ይጠመዳሉ፡፡ {2SM 52.2}Amh2SM 52.2

    ዛሬ እውነትን በቅዱስ ድፍረት መናገር ያስፈልጋል፡፡ በጌታ አገልጋይ ለቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን የተወሰደውን ምስክርነት በዚህ ጊዜ ሕዝቡ መስማት አለባቸው፡፡ «ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፣ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን” (ገላ. 1፡ 8)፡፡ {2SM 52.3}Amh2SM 52.3

    የተአምራት ሥራን የእምነቱ መፈተኛ የሚያደርግ ሰው ሰይጣን፣ በተለያዩ የማታለያ ዓይነቶች፣ እውነተኛ የሚመስሉ ተአምራቶችን መስራት እንደሚችል ያገኛል፡፡ እስራኤላውን ከግብፅ ነጻ በወጡ ጊዜ የመፈተኛ ጥያቄ ለማድረግ ተስፋ አድርጎ የነበረው ይህንን ነበር፡፡ --Manuscript 43, 1907. {2SM 52.4}Amh2SM 52.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents