Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መታዘዝ ከጠንካራ ስሜት ወይም ከታላቅ የግለት መንፈስ ጋር ሲነጻጸር

    መንፈስ ቅዱስን መቀበልን በተመለከተ ከእኛ ጋር ያሉት ስህተት የመፈጸም አደጋ አለባቸው፡፡ ብዙዎች ጠንካራ ስሜትን ወይም የደስታ ስሜትን ለመንፈስ ቅዱስ መገኘት ማረጋገጫ እንደሆነ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ ትክክለኛ የሆኑ ስሜቶችን ያለመረዳት አደጋ አለ፣ «ያዘዝኳችሁን ነገር ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው» (ማቴ. 28፡ 20) ያለው የክርስቶስ ቃላት ጠቀሜታቸውን ያጣሉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ዘዴዎችና ጥንቆላዊ የሆኑ አስተሳሰቦች የቅዱሳን ጽሁፎችን ቦታ የመውሰድ አደጋ አለ፡፡ ለሕዝባችን «በቃሉ ውስጥ ያልተገለጸ ነገርን ለማምጣት ጉጉት አይኑራችሁ፡፡ ወደ ክርስቶስ ቅረቡ” ብላችሁ ንገሩ፡፡. . . {2SM 18.2}Amh2SM 18.2

    ክርስቶስ ለሕዝብ፣ ለነገድ፣ ለቋንቋ፣ ለወገን ሁሉ እንድንሰብክ ያዘዘን ቃል በመንፈስ ቅዱስ እንደተረጋገጠ እናስታውስ፡፡ ይህ የእግዚአብሔር የሥራ ዕቅድ ነው፡፡ ክርስቶስ በለውጥ አማካይነት እርሱ ያዘዛቸውን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ፈቃደኛ እንዲሆኑ በማድረግ ወንዶችንና ሴቶችን ወደ እውነት እና ማስተዋል ወዳለው እምነት በማምጣት ቃሉን የሚያጸና ታላቅ ኃይል ነው፡፡ ሰብዓዊ ወኪል፣ የሚታይ መሣሪያ፣ ቃሉን ሲሰብክ ጌታ ኢየሱስ፣ የማይታይ ወኪል በእርሱ መንፈስ ቅዱስ አማካይነት ቃሉን ውጤታማና በኃይል የተሞላ ያደርገዋል፡፡ --Letter 105, 1900. {2SM 18.3}Amh2SM 18.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents