Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሰይጣንና ወኪሎቹ እንዴት እንደሚሰሩ

    ወደ ፊት ታላቅ የሆነ ነቅቶ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ እንድናገር ታዝዣለሁ፡፡ በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል መንፈሳዊ ደደብነት መኖር የለበትም፡፡ ክፉ መናፍስት የሰብአዊ ፍጡራንን አእምሮዎች ለመቆጣጠር በመፈለግ ሥራ ላይ ተግተው ተሰማርተዋል፡፡ ሰዎች በመጨረሻው ቀናት እሳት ለመቃጠል በክምር እየሆኑ እየተጠረዙ ናቸው፡፡ ክርስቶስንና ጽድቁን የማይቀበሉ ሁሉ ዓለምን እያጥለቀለቀ ያለውን የሀሰት ማታለያ ይቀበላሉ፡፡ ክርስቲያኖች የሚውጠውን ሰው እየፈለገ እንደሚያገሳ አንበሳ እየዞረ ያለውን ጠላት ዲያብሎስን ጸንተው በመቃወም የተረጋጉና ሁል ጊዜ የነቁ መሆን አለባቸው፡፡ በአጋንንት ተጽእኖ ሥር ያሉ ሰዎች ተአምራት ያደርጋሉ፡፡ በአስማታቸው እያሰሩ ሰዎችን እንዲታመሙ ያደርጋሉ፣ ከዚያም የታመሙት በተአምራዊ ሁኔታ ድነዋል ብለው ሌሎች እንዲናገሩ ለመምራት አስማታቸውን ያነሳሉ፡፡ ሰይጣን ይህን በተደጋጋሚ አድርጓል፡፡ --Letter 259, 1903. {2SM 53.2}Amh2SM 53.2

    መታለል የለብንም፡፡ ሰይጣን በቅርበት ግንኙነት የሚፈጥርባቸው አስደናቂ እይታዎች በቅርቡ ይፈጸማሉ፡፡ ሰይጣን ተአምራቶችን እንደሚሰራ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል፡፡ ሰዎችን እንዲታመሙ ያደርግና ከእነርሱ ላይ በድንገት ሰይጣናዊ ኃይሉን ያነሳል፡፡ ያኔ እንደተፈወሱ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ እነዚህ ግልጽ የፈውስ ሥራዎች የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶችን ወደ ፈተና ያመጣሉ፡፡ ታላቅ ብርሃን የነበራቸው ብዙዎች ከክርስቶስ ጋር አንድ ስላልሆኑ በብርሃን መሄድ ያቅታቸዋል፡፡ --Letter 57, 1904. {2SM 53.3}Amh2SM 53.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents