Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በካሊፎርኒያ ላሉ ቤተ ክርስቲያናት የተሰጠ መልእክት

    በካሊፎርኒያ ላላችሁ ወንድሞቻችን፡-

    ባለፈው ሌሊት ለሕዝባችን የሚሆን መመሪያ ተሰጥቶኛል፡፡ ከወንድም ኤል እና ከሚስቱ እንግዳ ሥራ ውስጥ ገለጻዎች እየተደረጉ ባለበት ስብሳባ ውስጥ ያለሁ መሰለኝ፡፡ በማይኔ (Maine) ግዛት በ--- ውስጥ እና ከ1844 ማለፍ በኋላ በሌሎች በተለያዩ ቦታዎች ከተፈጸመው ሥራ ጋር ተመሳሳይ ሥራ እንደሆነ ትምህርት ተሰጠኝ፡፡ ይህን የወግ አጥባቂነት ስራ በጽናት በመቃወም እንድናገር ታዝዤ ነበር፡፡ {2SM 46.1}Amh2SM 46.1

    ወንድም ኤልን እና ባለቤቱን እየመራ ያለው የእግዚአብሔር መንፈስ እንዳልሆነ አሳይቶኛል፣ ነገር ግን እየመራቸው ያለው ሁልጊዜ ወደ ቅሬታዋ ቤተ ክርስቲያን ለመግባት እየፈለገ ያለው የወግ አጥባቂነት መንፈስ ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አጠቃቀማቸው የተሳሳተ ነው፡፡ ሰዎች በአጋንንት እንደተያዙ ከተናገሩ በኋላ ከእነርሱ ጋር በመጸለይ ክፉ መናፍስትን እንደሚያወጡ ማስመሰል ለእንደዚህ ዓይነት ሥራ ማረጋገጫ የሚሰጥን የማንኛውንም ቤተ ክርስቲያን ስም የሚያጎድፍ ወግ አጥባቂነት ነው፡፡ {2SM 46.2}Amh2SM 46.2

    እነዚህን የኃይማኖት ድርጅቶች ማበረታታት እንደሌለብን፣ ነገር ግን የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶችን ስም ከሚያጎድፍና ለዓለም ማድረስ ባለባቸው የእውነት መልእክት ላይ ሰዎች እምነት እንዲያጡ ከሚያደርግ ነገር ሕዝቡን በጽኑ ምስክርነት መጠበቅ እንዳለብን አሳይቶኛል፡፡ ጌታ ሕዝቡን ምቹ በሆነ ቦታ በማስቀመጥ ለእነርሱ ታላቅ ሥራ ሰርቷል፡፡ የሚኖራቸውን ተጽዕኖ መንከባከብ የቤተ ክርስቲያን ተግባር ነው፡፡ «መጻሕፍትን እሹ፤ በእነርሱ የዘላለም ሕይወት የምታገኙ ይመስላችኋል፣ እነርሱ ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው” (ዮሐ. 5፡ 39) የሚሉት ቃላት የከበሩ ናቸው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተጸፉ ቃላት በጥንቃቄ ከተጠኑና በጸሎት መንፈስ ሆነው ቢታዘዙአቸው ለመልካም ሥራ ሁሉ ያዘጋጃሉ፡፡ {2SM 46.3}Amh2SM 46.3

    እንደ ኃይማኖት ድርጅት እግዚአብሔር እንዲመራን ያለማቋረጥ መፈለግ ያስፈልገናል፡፡ እየኖርን ያለንበት ዘመን ክፉ ነው፡፡ የመጨረሻው ዘመን አደጋዎች በላያችን ናቸው፡፡ ክፋት ስለበዛ ከእግዚአብሔር ጋር በትህትና ለመሄድ በሞከሩና ራሳቸውን በማያምኑ ሰዎች ላይ ሰይጣን አታላይ የሆኑ ንድፈ-ሀሳቦችን በሙሉ ለማምጣት ይደፍራል፡፡ በራሳቸው የሚተማመኑ፣ ወግ አጥባቂ ሰዎች ወደ እነዚህ የዋህ ነፍሳት በመምጣት በክፉ መናፍስት እንደተያዙ በማረጋገጥ ከእነርሱ ጋር አብረው ከጸለዩ በኋላ አጋንንት እንደወጣ ያረጋግጣሉን? እንደ እነዚህ ያሉት የእግዚአብሔር መንፈስ መገለጫዎች ሳይሆኑ የሌላ መንፈስ መገለጫዎች ናቸው፡፡ {2SM 47.1}Amh2SM 47.1

    ራሳቸውን ስለማያምኑ ብቻ መንፈስ ቅዱስ የለንም ብለው ስለሚፈሩ ሰዎች ክፉ ወደማሰብ እንዳትመሩ ለቤተ ክርስቲያን አባላት ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ የእግዚአብሔርን መንገድ ከመከተል ይልቅ የራሳቸውን መንገድ የተከተሉ ሰዎች አሉ፡፡ በልግስና ለሰጣቸው ብርሃን እግዚአብሔርን አላመሰገኑትም፡፡ ከዚህ የተነሳ በጨለማና በብርሃን መካከል የመለየትን ኃይል አጥተዋል፡፡ መከተል ስላለባቸው መንገድ ብዙ የሰሙ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የሚጠብቅባቸውን ነገሮች ችላ የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡ ብርሃናቸው የእውነትንና የቅድስናን መርሆዎች በሚያሳይ ሁኔታ በርቶ በሥራ አይታይም፡፡ ፈተና ሲመጣ ውሸትንና የስህተት ንድፈ ሀሳቦችን እንደ እግዚአብሔር እውነት አድርገው የሚቀበሉ ክፍሎች እነዚህ ናቸው፡፡ {2SM 47.2}Amh2SM 47.2

    ለእግዚአብሔር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን ተሰጥቶ ነበር፡፡ ሕዝባችን ነቅቶ ወደ ፊት ወደ ፍጽምና ይሂድ፡፡ ለሰይጣን ወኪሎች የሀሰት ትምህርቶች ትጋለጣላችሁ፡፡ አስፈሪ የሆነ የወግ አጥባቂነት ማዕበል ይመጣል፡፡ ነገር ግን ጌታን ከሙሉ ልባቸው የሚሹትንና ራሳቸውን ለእርሱ አገልግሎት የሚቀድሱትን ሰዎች እግዚአብሔር ነጻ ያወጣቸዋል፡፡ --Pacific Union Recorder, Dec. 31, 1908. {2SM 47.3}Amh2SM 47.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents