Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሁሉም ፀጥ ያለ፣ የተረጋጋ፣ ማስመሰል የሌለበት ነው

    ጠላት ተአምራት በመስራት ኃይሉ መላውን ዓለም ለማታለል እየተዘጋጀ ነው፡፡ የብርሃን መላእክትን መስሎ ይመጣል፣ ኢየሱስ ክርስቶስን መስሎ ይመጣል፡፡ የወቅቱን እውነት የሚያስተምር ሁሉ ቃሉን መስበክ አለበት፡፡ በቃሉ ላይ የሚጣበቁ ሰዎች ትንቢት መናገርን፣ ሕልምን ወይም ራዕይን በተመለከተ ጥንቃቄ የጎደላቸውን ንግግሮች በመናገር ለሰይጣን በሮችን አይከፍቱም፡፡ የክርስቶስን ዳግም ምጻት ከጠበቅንበት ከ1844 ዓ.ም በኋላ ይብዛም ይነስም ሀሰተኛ መገለጦች እዚህም እዚያም ይመጡ ነበር፡፡… እነዚህ እየበዙ ስለሚሄዱ እንደ ታማኝ ዘቦች በጥበቃ ላይ መሆን አለብን፡፡ ያዩአቸውን ሕልሞች በተመለከተና ለሌሎች መንገር ግዴታቸው እንደሆነ ከሚሰማቸው ከብዙ ሰዎች ደብዳቤዎች እየመጡልኝ ናቸው፡፡ {2SM 21.4}Amh2SM 21.4

    እግዚአብሔር ትክክለኛ የሆነ የብርሃን መተላለፊያ መስመር ሲኖረው ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ሁልጊዜ ብዙ አስመሳይ መስመሮች አሉ፡፡ ሰይጣን በማንኛውም በተከፈተለት በር ይገባል፡፡ ሰይጣን ነፍሳትን ወደ ስህተት ለመምራት፣ አእምሮን ወደ ሰብዓዊ ፍጡራንና ወደ አባባሎቻቸው ለመመለስ እና «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” የሚለውን እውነት አጥብቀው እንዳይይዙ ለመከልከል የእውነት መልእክቶችን የራሱ ከሆኑ የእውነት ሀሳቦች ጋር በመቀላቀል ይሰጣል፡፡ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የሚኖረው ግንኙነት ሁሉ እርጋታ ያለበት ነው፤ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉም ነገር የተረጋጋ እና ማስመሰል የሌለበት ነው፡፡ የማይከብዱ፣ እውነተኛ የሆኑና መጽሐፍ ቅዱስን ከልባቸው የሚያምኑ አማኞች ይኖራሉ፣ እንዲሁም ቃሉን ሰሚዎችና አድራጊዎች የሆኑ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ትክክለኛ የሆነ፣ ቅንነት ያለበት እና ማስተዋል ያለበት እግዚአብሔርን መጠበቅ ይኖራል፡፡ --Letter 102, 1894. {2SM 22.1}Amh2SM 22.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents