ሁል ጊዜ ወደ ኢየሱስ ተመልከቱ
በኋለኛው ዝናብ ስር የሰው ፈጠራዎች እና ሰብአዊ ዘዴዎች አንዳንድ ጊዜ ተጠራርገው ይወሰዱና የሰው የስልጣን ወሰን እንደ ተሰበሩ መቃዎች ይሆናል፣ መንፈስ ቅዱስ በሚያሳምን ኃይል በሕያው ሰብዓዊ ወኪል አማካይነት ይናገራል፡፡ ያኔ ማንም ቢሆን አረፍተ ነገሮቹ በደንብ የተሟሉ፣ ሰዋሰው ደግሞ እንከን የለሽ መሆኑን ለማየት እንቅልፍ አያጣም፡፡ ሕያው ውኃ በራሱ በእግዚአብሔር መተላለፊያዎች ይፈሳል፡፡ {2SM 58.4}Amh2SM 58.4
ነገር ግን አሁን ሰዎችን፣ የእነርሱን አባባሎችና ድርጊቶች ከፍ ከፍ እንዳናደርግ እንጠንቀቅ፤ ማንም ሰው ቢሆን ለሌሎች የሚነግረው አስደናቂ ልምምድ ቢኖረው ያንን እንደ ትልቅ ነጥብ አድርጎ አይመልከት፤ በዚህ ቦታ በማይገባቸው ላይ እምነት የሚጣልበት ፍሬያማ መስክ አለ፡፡ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ከፍ ከፍ ይሉና በአስደናቂ ሁኔታ ተቀባይነት እንዳገኙና የሆነ ታላቅ ነገር ለማድረግ እንደተጠሩ አድርገው ራሳቸውን ይቆጥራሉ፡፡ ልዩ ሥርዓትን በተከተለ መንገድ ብዙ የሚለወጡ ሰዎች ይኖራሉ፣ ነገር ግን መለኮታዊ ፍርማ ያላረፈባቸው ናቸው፡፡ የሥነ ምግባር ጉድለትና አባካኝነት ይገቡና የብዙዎች የእምነት መርከብ ይሰበራል፡፡ {2SM 59.1}Amh2SM 59.1
ያለን ብቸኛው ደህንነታችን ኢየሱስን አጥብቀን መያዝ ነው፡፡ በፍጹም ዓይናችንን ከእርሱ ማንሳት የለብንም፡፡ «ያለ እኔ አንዳች ማድረግ አትችሉም” (ዮሐ. 15፡ 5)፡፡ የራሳችንን ብቁ አለመሆንና ረዳተ ቢስነት ስሜት በማሳደግ ሙሉ በሙሉ በኢየሱስ መደገፍ አለብን፡፡ ይህ በግላችን በቃላቶቻችንና በባሕርያችን የተረጋጋን እና የጸናን ሊያደርገን ይገባል፡፡ ለመዳን የእግዚአብሔር ኃይል የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት፣ ወንጌልን፣ ለማቅረብ ጽናትና ጉልበት አስፈላጊ ናቸው፡፡... {2SM 59.2}Amh2SM 59.2
ብዙዎች የመስመጥ አደጋ ውስጥ ያሉበት የሚከዱ አሸዋዎች አሉ፡፡ ሰማያዊ ያልሆነ ኃይልና ድፍረት ካልቀላቀልን በስተቀር የእግዚአብሔርን መንፈስ በቅንነት መሻት ሁል ጊዜ ደህንነት አለው፡፡ አንዳንድ ኃይለኛ ፀባይ ያላቸው ምስኪን ነፍሳት ራሳቸውን እውቀት የሌለው ቅንዓት ውስጥ እንዳያስገቡ በንግግሮቻችን ሁሉ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንዲጠቀምባቸው፣ እንዲቀርጻቸውና በመለኮታዊ ምሳሌ እንዲሰራቸው ከመፍቀድ ይልቅ መንፈስ ቅዱስን የመጠቀም ሥልጣን እንዳላቸው ይሰማቸዋል፡፡ ከክርስቶስ ቀድሞ የመሮጥ አደጋ አለ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ወደሚመራን በመከተል ልናከብረው ይገባናል፡፡ «በራስህ ማስተዋል አትደገፍ” (ምሳሌ 3፡ 5)፡፡ ለሌሎች እውነትን የሚያስተምሩ ሰዎች ያለባቸው አንዱ አደጋ ይህ ነው፡፡ ክርስቶስ ወደሚመራን መከተል ለእግራችን አደጋ የሌለበት መንገድ ነው፡፡ ሥራው ጸንቶ ይቆማል፡፡ እግዚአብሔር የሚለው ነገር ሁሉ እውነት ነው፡፡ {2SM 59.3}Amh2SM 59.3
ነገር ግን ለወደቁ ሰዎች የመጨረሻውን የምህረት መልእክት የሚያደርሱ አገልጋዮች ምንም ዓይነት ቃል እንደመጣላቸው መናገር የለባቸውም፣ ሰይጣን ወደ ሰብአዊ አእምሮዎች የሚገባበትን በር መክፈት የለባቸውም፡፡ መነሳሳትን የሚፈጥርን አዲስና አስገራሚ ነገር መሞከርና ማጥናት የእኛ ሥራ አይደለም፡፡ ሰይጣን ለማታለል የሚጠቀምባቸውን ነገሮች ለማምጣት የዚህ ዓይነት ባሕርይ ያላቸውን ነገሮች ለመጠቀም ዕድሎችን ነቅቶ እየጠበቀ ነው፡፡ በሰብአዊ ወኪሎች ላይ የመንፈስ ቅዱስ አንቀሳቃሽነት አእምሮ ሚዛናዊ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ስሜታቸውን በመግለጽ የሚከተሉት የተፈጠረ መነሳሳት አይኖርም፡፡ {2SM 60.1}Amh2SM 60.1
ሰይጣን እያንዳንዱን ሥርዓት የለሽ ንግግር የሚጠቀመው ተናጋሪውን ብቻ ለመጉዳት ሳይሆን የተናጋሪውን መንፈስ በመያዝ ሌሎች እንዲጎዱበት በዚያ ውስጥ የሚያስገቡአቸውንም ጭምር ለመጉዳት ነው፡፡ እርጋታና ጨዋነት መጎልበት አለባቸው፤ እኛ የምንነጋገርባቸው ከበድ ያሉ እውነቶች ጥልቅ የሆነ ቅንነትን እንድናሳይ ይመሩናል፡፡ እየሞቱ ላሉ ነፍሳት ልናደርስ ያለውን እጅግ ቅዱስ የሆነ መልእክት ተሸክመን፣ የአዳኛችን መምጫ ቅርብ የመሆኑ ስሜት ክብደት እየተሰማን፣ ከዚህ የተለየ ነገር እንዴት ማድረግ እንችላለን፡፡ {2SM 60.2}Amh2SM 60.2
ሁል ጊዜ ወደ ኢየሱስ እየተመለከትን እና መንፈሱን እየተቀበልን ከሆነ ግልጽ የሆነ እይታ ይኖረናል፡፡ ያኔ በሁሉም አቅጣጫ ያሉትን አደጋዎች በመለየት ሰይጣን በማታለያዎቹ ውስጥ ለመሸመን እድል እንዳያገኝ የምንናገረውን እያንዳንዱን ቃል እንቆጣጠራለን፡፡ የሰዎች አእምሮዎች እንዲረበሹ አንፈልግም፡፡ እንግዳና ድንቅ ነገሮችን ለማየት የመጠበቅ ሁኔታዎችን ማደፋፈር የለብንም፡፡ ነገር ግን ኢየሱስን ደረጃ በደረጃ እንዲከተሉ አስተምሯቸው፡፡ የዘላለማዊ ሕይወት ተስፋችን ማዕከል የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ስበኩ፡፡ --Letter 102, 1894. {2SM 60.3}Amh2SM 60.3