Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    የድሮዎቹ ስብከቶች እንዲሰበኩ የቀረበ ጥሪ

    በአገልግሎት ውስጥ ነገሮች አዲስ ስርዓት ይዘው መጥተዋል፡፡ የሌሎች ቤተ ክርስቲያናትን ምሳሌ የመቅዳት ፍላጎት ስላለ ትህትናና ራስን ዝቅ ማድረግ የማይታወቁ ሆነዋል፡፡ ወጣት አገልጋዮች የራሳቸውን መልእክት ለማስተላለፍና ለሥራው አዳዲስ ሀሳቦችንና እቅዶችን ለማምጣት ይፈልጋሉ፡፡ አንዳንዶች የመነቃቃት ስብሳባዎችን ያዘጋጁና በዚህ መንገድ ብዙዎችን ወደ ቤተ ክርስቲያን ይጠራሉ፡፡ ነገር ግን መነሳሳቱ ሲያበቃ የተለወጡቱ የት ናቸው? የኃጢአት ንስሃና ኑዛዜ አይታዩም፡፡ ኃጢአተኛው ያለፈውን የኃጢአትን የአመጽ ሕይወት ከግምት ውስጥ ሳያስገባ በክርስቶስ እንዲያምንና እንዲቀበለው ይለመናል፡፡ ልብ አልተሰበረም፡፡ በነፍስ ውስጥ ለኃጢአት መጸጸት የለም፡፡ ተለውጠዋል የተባሉት በዓለቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አልወደቁም፡፡ {2SM 18.4}Amh2SM 18.4

    በብሉይና በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉት ጥቅሶች ይህ ሥራ መከናወን ያለበትን ብቸኛ መንገድ ያሳዩናል፡፡ በምድረ በዳ ከመጥምቁ ዮሐንስ አፍ ያስተጋባ የነበረው መልእክት ንስሃ ግቡ፣ ንስሃ ግቡ፣ ንስሃ ግቡ የሚል ነበር፡፡ ክርስቶስ ለሕዝቡ ያለው መልእክት ንስሃ ካልገባችሁ ሁላችሁም እንዲሁ ትጠፋላችሁ» (ሉቃስ 13፡ 5) የሚል ነበር፡፡ ሐዋርያትም ሰዎች ንስሃ እንዲገቡ በሁሉም ቦታ እንዲሰብኩ ታዘው ነበር፡፡ {2SM 19.1}Amh2SM 19.1

    ጌታ ዛሬ ያሉት አገልጋዮቹ የቀድሞውን የወንጌል አስተምህሮ፣ ለኃጢአት ማዘንን፣ ንስሃንና ኑዛዜን እንዲሰብኩ ይሻል፡፡ የድሮ ስብከቶችን፣ የድሮ ወጎችን፣ በእሥራኤል የነበሩ የድሮዎችን አባቶችና እናቶች እንፈልጋለን፡፡ ኃጢአተኛው የእግዚአብሔርን ሕግ እንደተላለፈ እና ለእግዚአብሔር ንስሃ መግባትንና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን መለማመድ እንደሚችል እስኪያይ ድረስ በትዕግሥት፣ በእውነተኛ ልብ፣ እና በጥበብ ሊሰራለት ይገባል፡፡ --Undated manuscript 111. {2SM 19.2}Amh2SM 19.2