Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ 46—በእግዚአብሔር ፈቃድ መመራት

    እግዚአብሔር መንገድ ሲከፍት፣ ቤተሰቦች ከተሞችን ለቀው የሚወጡበት ጊዜ መጥቷል፡፡ ልጆች ወደ ገጠር መወሰድ አለባቸው፡፡ ወላጆች ገቢያቸው በሚፈቅድላቸው መጠን ምቹ ቦታ ማግኘት አለባቸው፡፡ መኖሪያ ቤቱ ትንሽ ቢሆንም ከቤቱ ጋር የተገናኘ የእርሻ መሬት መኖር አለበት፡፡ Manuscript 50, 1903.Amh2SM 360.1

    ወላጆች በደም ቧንባዎች ውስጥ እየሄደ ያለውን የሕይወት ደም የሚያበላሸውን የስጋ ምግብ የሚተኩ አትክልቶችን እና ትንንሽ ፍራፍሬዎችን ማሳደግ የሚችሉበት የእርሻ መሬት ያላቸውን ትንንሽ ቤቶች በገጠር ውስጥ መያዝ ይችላሉ፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ቦታዎች ልጆች በሚያበላሽ የከተማ ኑሮ ተጽእኖ አይከበቡም፡፡ ሕዝቡ እንደ እነዚህ ያሉ ቤቶችን ማግኘት እንዲችሉ እግዚአብሔር ይርዳቸው፡፡ Medical Ministry, p. 310.Amh2SM 360.2

    ጊዜ ወደ ፊት በሄደ ቁጥር ሕዝባችን በብዛት ከተሞችን መልቀቅ ይኖርበታል፡፡ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፣ በተላይም ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦች፣ በፊታቸው መንገድ ሲከፈትላቸው ከተሞችን ለመልቀቅ ማቀድ እንዳለባቸው ለዓመታት መመሪያ ሲሰጠን ቆይቷል፡፡ መንገድ እንዲከፈት ለመርዳት ብዙዎች ተግተው መስራት አለባቸው፡፡ ነገር ግን እስካልወጡ ድረስ፣ ለመልቀቅ እስኪቻላቸው ድረስ፣ ተጽእኖ ማሳደር የሚችሉበት ክበብ ውስን ቢሆንም እንኳን ሚስዮናዊ ሥራን በመሥራት እጅግ በጣም ትጉህ መሆን አለባቸው፡፡ The Review and Herald, Sept. 27, 1906.Amh2SM 360.3