Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በራዕይ 18 ላይ የተጠቀሰችው ባቢሎን

    «ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች። በብርቱም ድምፅ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤ አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሳ ወድቀዋልና፥ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኃይል የተነሳ ባለ ጠጋዎች ሆኑ ብሎ ጮኸ። ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤ ኃጢአትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶአልና፥ እግዚአብሔርም ዓመፃዋን አሰበ። እርስዋ እንደ ሰጠች መጠን ብድራት መልሱላት፥ እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት፤ በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤ ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ሀዘን ስጡአት። በልብዋ ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ ባልቴትም አልሆንም ሀዘንም ከቶ አላይም ስላለች፥ ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ሀዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶቿ ይመጣሉ፥ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና” (ራዕይ 18፡ 1-8)፡፡ {2SM 67.3}Amh2SM 67.3

    የወደቀችው ባቢሎን ጌታ በመጀመሪያው፣ በሁለተኛውና በሶስተኛው መላእክት የተሰጡትን የማስጠንቀቂያ መልእክቶች የማይቀበሉ አብያተ ክርስቲያናት እንደሆኑ ምዕራፉ በሙሉ ያሳያል፡፡ እውነትን እምቢ ብለው ውሸትን ተቀብለዋል፡፡ የእውነት መልእክቶችን መቀበል እምቢ ብለዋል፡፡ 2ኛ ተሰሎንቄ 2፡ 1-12ን ይመልከቱ፡፡ በራዕይ ምዕራፍ 18 ላይ ያለው መልእክት በቀላሉ የሚስተዋልና ግልጽ ነው፡፡ «አህዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቁጣ ወይን ጠጅ የተነሳ ወድቀዋልና፣ የምድርም ነገሥታት ከእሷ ጋር ሴሰኑ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልናዋ ኃይል የተነሳ ባለጠጋዎች ሆኑ» (ቁጥር 3)፡፡ ይህን ምዕራፍ የሚያነብ ማንም ቢሆን መታለል የለበትም፡፡{2SM 68.1}Amh2SM 68.1

    ይህ መልእክት የሚመለከተው እግዚአብሔር የሕጉ ጠባቂዎች ያደረጋቸውን ሕዝብ ከሆነ ይህ መልእክት ሲሰራጭ ሰይጣን እንዴት ከፍ ከፍ ይላል፡፡ የባቢሎን ወይን ጠጅ ማለት ውሸትና ስህተት የሆነውን ሰንበት ያህዌ እግዚአብሔር ለሰው ጥቅም ከባረከውና ከቀደሰው ሰንበት በላይ ከፍ ከፍ ማለት ነው፣ ደግሞ ነፍስ አትሞትም የሚለው ትምህርትም ነው፡፡ እነዚህን የመሳሰሉ መናፍቅነቶች እና እውነትን አለመቀበል ቤተ ክርስቲያንን ወደ ባቢሎንነት ይለውጧታል፡፡ ነገስታት፣ ነጋዴዎች፣ ገዦች፣ እና የኃይማኖት መምህራን በሙሉ በአንድነት ረክሰዋል፡፡ {2SM 68.2}Amh2SM 68.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents