Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    በመጽሐፍ ቅዱስ ኃይማኖት ውስጥ የሕብረተሰብ ወይም የቀለም ክፍፍል የለም

    የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይማኖት በመደብና በቀለም ለሚደረግ ክፍፍል እውቅና አይሰጥም፡፡ ለማዕረግ፣ ለሃብት፣ እና ለዓለማዊ ክብር ቦታ አይሰጥም፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን የሚያየው እንደ ሰዎች ነው፡፡ በእርሱ ዘንድ የአንድን ሰው ዋጋ የሚወስነው ባሕርይ ነው፡፡ የክርስቶስ መንፈስ በማንም ቢገለጥ እውቅና መስጠት አለብን፡፡-- Ibid., vol. 9, p. 223.Amh2SM 486.3

    ደቀ መዛሙርት የአዳኙን የፍቅር መልእክት ለማድረስ ወደ ሕዝብ ሁሉ ሲሄዱ በእግዚአብሔር መንግስት የወሰን መለያ መስመሮች፣ የህብረተሰብ ክፍፍል፣ ወይም መኳንንት እንደሌሉ ክርስቶስ ሊያስተምራቸው ፈለገ፡፡--The Acts of the Apostles, p. 20.Amh2SM 486.4