በስህተት ጥቅም ላይ የዋሉ ጥቅሶች አስፈሪነት
የወቅቱን እውነት እናምናለን በሚሉ ሰዎች ልምምድ ውስጥ የአይሁድ ሕዝብ ታሪክ እንዲደገም ሰይጣን እየሰራ ነው፡፡ አይሁዶች የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ስለነበሩአቸው እነርሱን እንደሚያውቋቸው አድርገው ራሳቸውን ቆጠሩ፡፡ ነገር ግን የሚያሳዝን ስህተት ሰሩ፡፡ በግርማ የተሞላውን የክርስቶስን በሰማይ ዳመና ዳግም ምጻት የሚያመለክቱ ትንቢቶችን የመጀመሪያ ምጻቱን እንደሚያመለክቱ አድርገው ወሰዱ፡፡ እነርሱ እንደጠበቁት ስላልመጣ ለእርሱ ጀርባቸውን ሰጡ፡፡ ሰይጣን እነዚህን ሰዎች በመረቡ ውስጥ እንደሚያስገባቸውና አሳስቶ እንደሚያጠፋቸው አወቀ፡፡. . . {2SM 111.1}Amh2SM 111.1
ያው ሰይጣን አሁን ያለውን የእግዚአብሔርን ሕዝብ እምነት ለመሸርሸር በሥራ ላይ ነው፡፡ እያንዳንዱን አዲስ ሀሳብ ለመያዝ ዝግጁ የሆኑ ሰዎች አሉ፡፡ የዳንኤልና የራዕይ ትንቢቶች የስህተት ትርጉም ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ይህን የተለየ ሥራ እንዲሰሩ እግዚአብሔር ይመራቸው በነበሩት ሰዎች እውነት በተወሰነው ሰዓት እንደቀረበ አድርገው አይቀበሉም፡፡ እነዚህ ሰዎች የትንቢቱን መፈጸም ደረጃ በደረጃ ተከታተሉ፣ በዚህ ሥራ ውስጥ ልምድ ያልነበራቸው ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሊቀበሉና የመጀመሪያውን፣ የሁለተኛውንና የሶስተኛውን መላእክት መልእክቶች በሚያውጁበት ወቅት በተመሩ ሰዎች «ቃል” ሊያምኑ ነው፡፡ እነዚህ መልእክቶች ተቀባይነት አግኝተው ሥራ ላይ በዋሉበት ሁሉ በታላቁ የእግዚአብሔር ቀን የሚቆሙ ሰዎችን ለማዘጋጀት ሥራቸውን እየሰሩ ናቸው፡፡ ባሪያዎቹ ለዓለም እንዲያስተላልፉ እግዚአብሔር የሰጠውን እውነት ለማረጋገጥ ቅዱሳን መጻሕፍትን ከመረመርን የመጀመሪያውን፣ የሁለተኛውንና የሶስተኛውን መላእክት መልእክቶች እያወጅን እንገኛለን፡፡ {2SM 111.2}Amh2SM 111.2
ገና የሚፈጸሙ ትንቢቶች መኖራቸው እውነት ነው፡፡ ነገር ግን በትንቢቶች ውስጥ አዲስ ብርሃን ለማግኘት በሚሹና እግዚአብሔር አስቀድሞ ከሰጠው ብርሃን በመለየት በሚጀምሩ ሰዎች በተደጋጋሚ የስህተት ሥራ ተሰርቷል፣ ወደፊትም ተመሳሳይ ስህተት መፈጸሙ ይቀጥላል፡፡ የራዕይ 14 መልእክቶች ዓለም የሚፈተንባቸው መልእክቶች ናቸው፣ ዘላለማዊ ወንጌል ስለሆኑ በሁሉም ቦታ መስተጋባት አለባቸው፡፡ ነገር ግን በቅዱስ መንፈሱ አማካይነት ትንቢቶችን እንዲያብራሩ የተመረጡ ባሪያዎቹን ያንቀሳቀሰው ጌታ በሥራው ውስጥ ልምድ የሌላቸው ሰዎች በትንቢቶች ላይ አዲስ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሸክም አይጭንባቸውም፡፡ {2SM 111.3}Amh2SM 111.3
እግዚአብሔር በሰጠኝ ብርሃን መሰረት ወንድም ኤፍ ልትሰራ እየሞከርክ ያለኸው ሥራ ይህ ነው፡፡ አመለካከቶችህ በአንዳንዶች ዘንድ ተቀባይነት አግኝተዋል፤ ነገር ግን ይህ የሆነበት ምክንያት እነዚህ ሰዎች የምታቀርባቸውን መከራከሪያዎች እውነተኛ አቋም ለይተው ማየት ስላልቻሉ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለዚህ ጊዜ ባለው ሥራ ላይ የነበራቸው ልምድ ውስን ስለሆነ አመለካከቶችህ ወዴት እንደሚመሩአቸው አያዩም፣ አንተ ራስህም ወዴት እንደሚመሩህ አታይም፡፡ አንተ ከምትሰጣቸው መግለጫዎች ጋር ለመስማማት ዝግጁ ናቸው፤ በአባባሎችህ ውስጥ ትክክል ከሆነው ነገር ሌላ ምንም ነገር አያዩም፡፡ ነገር ግን ንድፈ ሀሳብህን ስትመሰርት ብዙ ጥቅሶችን ስላደራህባቸው ወደ ስህተት ተመርተዋል፡፡ ለእነርሱ መከራከሪያዎችህ ወሳኝ ይመስሉአቸዋል፡፡ {2SM 112.1}Amh2SM 112.1
ነገር ግን በዚህች የምድር ታሪክ የመጨረሻ ጊዜ ስለሚሆን እውነት በተግባር የተፈተነ እውቀት ያላቸው ሰዎች እንዲህ አይደሉም፡፡ አንዳንድ ውድ የሆኑ እውነቶችን እንደያዝክ ቢያዩም መጽሐፍ ቅዱስን በስህተት ማዕቀፍ ውስጥ በማድረግ፣ መገኘት በሌለበት ቦታ በማስቀመጥና የወቅቱ እውነት ላልሆነው ነገር ኃይል እንዲሰጥ በማድረግ በስህተት እንደተጠቀምክበት ደግሞ ያያሉ፡፡ አንዳንዶች የጻፍከውን ነገር ስለሚቀበሉ ደስተኞች አይሆኑም፡፡ አንተን ለሚወዱህና እንደ ክርስቲያን ለሚተማመኑብህ ወንድሞችህ የሚያስከትለው ታላቅ ውጤት እንደሚኖረው ያሰብከውን የመከራከሪያ መረብ በአሁኑ ጊዜ እንዲሰብኩት እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጠው የእውነት ንድፈ ሀሳብ አይደለም ብለው መናገር እጅግ ፈታኝ ነው፡፡ {2SM 112.2}Amh2SM 112.2
እግዚአብሔር የሰጠኝ ብርሃን አንድ ላይ ያደራሃቸው ጥቅሶች አንተ ራስህ ሙሉ በሙሉ የማታስተውላቸው እንደሆኑ ነው፡፡ ብታስተውል ኖሮ ንድፈ ሀሳቦችህ የእምነታችንን መሰረት የሚንዱ መሆናቸውን ለይተህ ታውቅ ነበር፡፡ {2SM 112.3}Amh2SM 112.3
ወንድሜ ሆይ፣ አሁን አንተ እየሄድክበት ባለህበት መንገድ መሄድ የጀመሩ ሰዎችን ለማረም ብዙ ምስክርነቶች ነበሩኝ፡፡ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔር እንደመራቸው እርግጠኛ የሆኑ ይመስላሉ፣ እውነትን እየሰበኩ ወደነበሩ አገልጋዮች ከተለያዩ ንድፈ ሀሳቦቻቸው ጋር መጥተዋል፡፡ ለእነዚህ አገልጋዮች እንዲህ አልኳቸው፣ «በዚህ ውስጥ ጌታ የለም፤ አትታለሉ፣ ሌሎችን የማታለል ኃላፊነትም አትውሰዱ፡፡” በስብሰባዎች ላይ ሰዎችን ከትክክለኛው መንገድ ወደ ስህተት መንገድ እየመሩ የነበሩትን በተመለከተ በግልጽ መናገር ነበረብኝ፡፡ በጽሁፍም ሆነ በቃል «አትከተሏቸው» የሚለውን መልእክት አድርሻለሁ፡፡ {2SM 112.4}Amh2SM 112.4